Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 01 December 2012 13:47

ቢዮንሴ በቅርቡ የራሷን ጥናታዊ ፊልም ትሠራለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ዝነኛዋ አሜሪካዊት አቀንቃኝ ቢዮንሴ ኖውልስ፤ በግል ህይወቷ ላይ ያተኮረ ልዩ ጥናታዊ ፊልም በቅርቡ እንደምትሰራ “ዘ ሆሊዉድ ሪፖርተር” አስታወቀ፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኤችቢኦ ጣቢያ የሚሰራጨው ፊልሙ፤ የቢዮንሴን ስብእና ግልጥልጥ አድርጎ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ፊልም ላይ ቢዮንሴ በተዋናይነት፤በዲያሬክተርነት እና በኤክዝኪዩቲቭ ፕሮዱዩሰርነት ትሰራለች ተብሏል፡፡ በታዋቂው የኤችቢኦ ጣቢያ የሚተላለፉ በርካታ ፕሮግራሞችን እንደምትከታተል የተናገረችው ቢዮንሴ፤ በዚህ ጣቢያ የሚሰራጭ ፊልም ለመስራት መብቃቷን እንደታላቅ ዕድል እንደምትቆጥረው ገልፃለች፡፡

በጥናታዊ ፊልሙ ውስጥ ቢዮንሴ በመድረክ ላይና ከመድረክ ውጭ ስለምታከናውናቸው ተግባራት፣ ስለልጅነቷና ስለእድገቷ፤ ስለትዳር ህይወቷ እና በፈረንጆች አዲስ አመት የ1ኛ ዓመት ልደት በዓሏን ስለምታከብረው ልጇ የሚያሳዩ ትዕይንቶች እንደሚካተቱ ታውቋል፡፡ ቢዮንሴ ራሷ የቀረፀቻቸው ፊልሞች የጥናታዊ ፊልሙ አካል እንደሚሆኑና በራሷ ልዩ ቃለምልልሶች እንደሚታጀብም “ዘ ሆሊዉድ ሪፖርተር” ጠቁሟል፡፡ ከሙዚቃ ሙያዋ ባሻገር በፊልም ስራዎች የመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጐት እንዳላት የምትናገረው ቢዮንሴ፤ ለዚሁ ያግዘኛል ብላ ያሰበችውን “ፓርክውድ ኢንተርቴይመንት” የሚባል ድርጅት እንዳቋቋመች ታውቋል፡፡ በሙዚቃ፤ በፊልም፤ በፋሽንና ሌሎች የቢዝነስ ስራዎች ላይ የተሰማራችው ቢዮንሴ፤ ከ350 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሃብት ያካበተች የፖፕ እና የአር ኤንድ ቢ ስልቶች ምርጥ ሙዚቀኛ ናት፡፡

Read 3124 times

Latest from