እንደማናጀሩ ክስ የፍቅር ግንኙነታቸው ከተቋረጠ በኋላ፤ ከእሷ ሊያገኝ ይገባው የነበረውን ክፍያ ከልክላዋለች፡፡ የ35 ዓመቷ ሻኪራ ከሁለት ዓመት በፊት ከላ ሩዋ ጋር የነበራትን የፍቅር ግንኙነት ያቋረጠች ሲሆን ከባርሴሎናው እግር ኳስ ተጫዋች ጄራርድ ፒኬ ጋር የጦፈ ፍቅር እንደያዛት ይታወቃል፡፡ ሻኪራ ከዚሁ ፍቅረኛዋ ያረገዘችውን የመጀመርያ ልጇን ለመውለድ የመጨረሻ ወራቶቿ ላይ ትገኛለች፡፡ ስምንት ጊዜ የላቲን አሜሪካ ግራሚ አዋርድን እንዲሁም ለ28 ጊዜያት የቢልቦርድ ላቲን አዋርድን ያሸነፈችው አርቲስቷ፤ በመላው አለም 50 ሚሊዮን ያህል የአልበሞቿን ቅጂዎች በመሸጥ በላቲን ሙዚቃ ታሪክ የላቀ ስኬት አስመዝግባለች፡፡ ስምንተኛውን አልበሟን በመስራት ላይ የምትገኘው ሻኪራ፤ ከላቲን ሙዚቀኛነቷ ባሻገር በፖፕ ሙዚቃዎቿም ተወዳጅ ናት፡፡ ሻኪራ በዘፈን ደራሲነት እና በፕሮዱዩሰርነት ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማካበት ተሳክቶላታል፡፡