Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 December 2012 14:19

ቢበር በአሜሪካ ሚውዚክ አዋርድ ነገሰ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ሰሞኑን በተካሄደው 40ኛው የአሜሪካ ሚውዚክ አዋርድ ላይ “የዓመቱ ምርጥ አርቲስት” በሚል የተሸለመው ካናዳዊው ድምፃዊ ጀስቲን ቢበር፤ በሌሎች ሁለት ዘርፎችም ለመሸለም በቅቷል፡፡ በአራት ሽልማት ዘርፎች ታጭተው የነበሩት ተፎካካሪዎቹ - ሪሃና እና ኒኪ ማናዥ ሁለት ሽልማቶችን በነፍስ ወከፍ አግኝተዋል፡፡ የዓመቱ ምርጥ አርቲስት ተብሎ ለመሸለም የበቃው የ18 አመቱ ጀስቲን ቢበር፤ ከታዋቂዎቹ ድምፃውያን ድሬክ፤ ኬቲ ፔሪ፤ ሪሃና እና ማሩን ፋይቭ ጋር ተወዳድሮ እንዳሸነፈ ታውቋል፡፡ ሌሎች ሁለት ሽልማቶቹ በ“ምርጥ ፖፕ እና ሮክ ሙዚቀኛነት” እንዲሁም “ቢልቭ” የተባለው አልበሙ “ምርጥ የሮክ እና የፖፕ አልበም” በሚል በመመረጥ ያገኛቸው ናቸው፡፡

ቴይለር ስዊፊት የዓመቱ ተወዳጅ የካንትሪ ሙዚቃ አርቲስት ተብላ 11ኛውን የአሜሪካ ሙዚክ አዋርድ ሽልማት ስትወስድ፤ ኒኪ ማናጅ በራፕ እና ሂፖፕ ምርጥ አርቲስት እና ‹ፒንክ ፍራይደይ፣ ሮማን ሪሎድድ› በተባለው አልበሟ ምርጥ አልበም ሰርታለች ተብላ ሁለት ሽልማቶችን እንዲሁም ሪሃና ደግሞ “ቶክ ዛት ቶክ” በተባለው አልበሟ ተወዳጅ የሶል እና አርኤንድቢ አልበም እና አርቲስትነት ክብሮችን ተሸልመዋል፡፡ ከሌሎች ተሸላሚዎች መካከል አሸር እና ቢዮንሴ በየፆታቸው በምርጥ የሶል እና አርኤንድቢ አርቲስትነት፤ ሻኪራ በምርጥ የላቲን አርቲስትነት መሸለማቸው ይጠቀሳሉ፡፡

Read 3474 times