Saturday, 10 September 2011 12:28

አትሌቲክስ አዳዲስ ጀግኖች ያስፈልጉታል..

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ኃይሌ ከሁለት ሳምንት በፊት በስፔን የፕሪንስ ኦስትዋሬስ የስፖርት    ሽልማትን የምንግዜም የረጅም     ርቀት ሯጭ ተብሎ ተሸለመ፡፡
ሽልማቱን የወሰኑለት ዳኞች  መግለጫ ለሁለት አስር ዓመታት በሚከፈለው መስእዋትነትና ራሱን ለማሻሻል
በሚያደርገው ጥረት  ለዓለም ተምሳሌት ነው ብለው  ኃይሌ አድንቀውታል፡፡ ሽልማቱ ዲፕሎማ፤ ልዩ የመታሰቢያ የዋንጫ ቅርና የ71ሺ ዶላር ጉርሻን ያካተተ ነው፡፡

የዓለም ማራቶን ሪኮርድን የጨበጠው ኃይሌ ገብረስላሴ ከፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌኤኪውፔ ጋር ከወር በፊት ባደረገው ቃለምልልስ ለአትሌቲክስ ስፖርት አዳዲስ ጀግኖች ያስፈልጉታል ሲል ተናግሯል፡፡ ቦልት፤ ኢዘነባዬቫና ቀነኒሳ የአትሌቲክስ  ሞገስ የያዙ ናቸው በሚል ያደነቀው ኃይሌ አሁን ያሉት የአትሌቲስ ጀግኖች ለዓመታት ያስመዘገቡትን ስኬት ለመድገምና ለማሻሻል የሚችል ትውልድ m አለበት ብሏል ፡፡ ብዙዎቹ የአትሌቲክስ ውድድሮች በአውሮፓ ከተሞች ሲካሄዱ የአፍሪካውያን አትሌቶችን የተሳትፎ እድል እያመናመኑ መምጣታቸውን የነቀፈው ሃይሌ ስፖርቱ በአትሌቶች ብርታት የቆመ መሆኑን በመግለ በውድድሮች ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡
በሌላ በኩል  በፓስፖርቱ የተፃፈ እድሜው 38 ቢሆንም የዓለም የማራቶን ሪከርድን የያዘው  ኃይሌ ገብረስላሴ እድሜ መጭበርበሩን በበቂ ምክንያት ማረጋገጥ ይቻላል በሚል የተሰራ ሰፊ ዘገባ በኮምፒውተተር መሄት ላይ ቀርቧል፡፡ የመሄቱ ፀሃፊ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማህበረሰብ ለረጅም ግዜ ሚስጥር ሆኖ የቆየው የኃይሌ ትክክለኛ እድሜ ነው ብሎ፤ ከ3 ዓመት በፊት ኃይሌ በበርሊን ማራቶን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ59 ሰኮንዶች በመግባት የዓለም ሪኮርድ ሲይዝ በወቅቱ በይፋ ከተገለፀው እድሜ ከ6 ዓመት በላይ እድሜ  ነበረው ሲል ያስረዳል፡፡
በዚህም ዘገባው ምናልባትም የማራቶን ፈጣን ሰዓትን ያስመዘገበው በ35 ዓመቱ ሳይሆን በ40 ዓመቱ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ብዙዎቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው የተወለዱበትን ቀን በአግባቡ ስለማያውቁ፤ አንዳንዶች ደግሞ ያለ እድሚያቸው በዓለም አቀፍ ወድድር ተሳትፎ ለማድረግ ሲሉ ትክክለኛ እድሜያቸው ተዛብቶ እየቀረበ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል- የኮምፒውተተር ዘገባ፡፡

 

Read 2482 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:30