Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:18

ዓለማዊ ህይወት በሃይማኖታዊ አተያይ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. ሲዳሰስ
ባለፈው ሳምንት ቢሮዬ የመጣልኝ    መሃፍ ለየት ያለ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ ጉጉት የሚፈጥር     ዓይነት ነው፡፡ ..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. ስለሚል ምስጢሮቹ     ምን ይሆኑ በሚል ለንባብ ይገፋፋል፡፡ መሃፉ በዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ተፈራ የተዘጋጀነው፡፡ በርግጥ ደራሲው መጽሐፍ ለማሳተም አዲስ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም ያሳተማቸው ስምንት መፃህፍት ያሉት ሲሆን በቅርቡ የሚያሳትማቸውን ሰባት መፃህፍት ዝርዝር በዚህኛው መሃፍ ጀርባ ላይ አስፍሯል፡፡ ቀደም ሲል ካሳተማቸው መካከል ..ክርስቲያናዊ ጋብቻ.. ቁጥር አንድና ሁለት፣ ..እውነተኛ ፆምና መንፈሳዊነት..፣ ..ነቅዕ ገነት (የነፃነት ምን´ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በቅርቡ ከሚያሳትማቸው ውስጥ አንደኛው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሆን |Football and Spiritual life´ ይሰኛል፡፡

ከመፃህፍቱ  መረዳት
እንደምንችለው ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ መንፈሳዊ መፃህፍት አዘጋጅ (ፀሐፊ) ነው፡፡ ዲያቆንነቱ (ሰባኪነቱ) እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው፡፡ መጽሐፉን ገለጥ  ስታደርጉት የምታገኟቸው ርዕሶች ቀልብን የሚስቡ ናቸው፡፡ ርዕሰ ጉዳዮቹም በመንፈሳዊ መፃሕፍት ያልተለመዱ ይመስላሉ፡፡ ይሄም ሌላው ለንባብ የሚገፋፋ ጉዳይ ነው፡፡
ዳሰሳችንን ፀሐፊው በመግቢያው ላይ ካሰፈረው እንጀምር፡፡ ..ከካይሮ ተነስቼ ወደ እስክንድሪያ
የሚወስደውን መንገድ
Y¢½ QÇS ¥R¸Â ገዳም እየሄድኩ ነው . . . ከሹፌሩ አጠገብ ነው
የተቀመጥኩት፡፡ ሹፌሩ ወሬ ጀመረ፡፡ ጥቂት እንደተጓዝን የአባይ ወንዝ ካይሮን መሃል ለመሃል ሰንጥቆ ሲያልፍ መኪናው በድልድዩ ላይ ያልፋል፡፡ በወሬያችን መሃል አንድ ጥያቄ ለሹፌሩ አቀረብኩለት፡፡ ይሄ ውሃ የሚመጣላችሁ ከየት ነው? አልኩት፡፡ የመለሰልኝ መልስ ግን በድንጋጤ አፌን ነው ያስያዘኝ.. የሚለው ፀሃፊያችን፤ ከስዊዝ ካናል ነው የሚነሳው ሲል እንደ መለሰለትና መረገሙን እሱም እንደተገረመ ገልል፡፡
ደግነቱ ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ የነገረውን አስታወሰና ተረጋጋ፡፡ ..አሁን ግብፆች ጂኦግራፊ ሲማሩ ዓባይ ከስዊዝ ካናል እንደሚነሳ ይነግሯቸዋል.. ነበር ያለው ያ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ፡፡ አንዳንድ ግብፃውያን ይሄንን ጊዜ በቀል ትምህርት እንደ እውነት መቀበላቸውም ያስገርመኛል የሚለን ፀሃፊው፤ ለትውልድ የማይሆን ትምህርት ማስተማሩ ለምን አስፈለገ፤ ሲል በልቡ እንዳሰበ ገልል፡፡
ፀሐፊው ይሄን ገጠመኙን ያመጣው ለብልሃቱ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተKRStEÃN መሰረቱን ልማድ ላይ ያደረገ ትምህርት እንደሚሰጥ የጠቀሰው ፀሐፊው፤ ይሄም ከግብፁ ለትውልድ የማይሆን ትምህርት ጋር ተመሳሳይ ነው ባይ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በቂና ከበቂ በላይ ልብ የሚሰብሩ፣ መሠረታቸው ወንጌል የሆኑ ትምህርቶች ያሏት ስርጉት ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች የገለፀው ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ፣ የሚያሳዝነው የወንጌልን ሚዛን የማይደፉ የልማድ ትምህርቶችና ሁፎች መስፋፋታቸውና ህዝቡም ይሄንን ልማዳዊ ትምህርቶች እንደ እውነት ተቀብሎ፣ ሁላችንም በድንግዝግዝ መጓዛችን ነው ይላል፡፡ ይሄ ደግሞ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያንን ሊቅ እንደ¸ö«qÜ«W ሁሉ እኔንም ያስቆጨኛል ብሏል፡፡ እንደሚመስለኝ ..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. የተወለደውም ከዚህ መቆጨት ውስጥ ነው፡፡  ..ቡና የሰይጣን ደም ነው.. እያሉ የሚያስተምሩ የሃይማኖት ሰዎችን የሚተቸው ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ፤ እንዲህ ዓይነት በርካታ ልማዳዊ ትምህርቶች መስፋፋታቸውን ይጠቁማል፡፡ እምነት፤ ልማድና ባህልን መሰረት አድርገው የሚያንፀባርቁት ሳይሆን ወንጌልን መሰረት አድርገው የሚያምኑት ህይወት የሚለው ደራሲ፡ መጽሐፉ የተዘጋጀው  ይሄንን ለማጥራት ነው ብሏል፡፡ እኔን በተለይ የሳበኝ ደግሞ ከሃይማኖት ውጭ የሚመስሉና የሥነልቦና መነጽር ወይም ትንተና የሚፈልጉ ርዕሰ ጉዳዮች መነሳታቸው ነው፡፡ ለዚህም ነው የዚህን ዳሰሳ ርዕስ ..ዓለማዊ ህይወት በሃይማኖታዊ አተያይ.. ያልኩት፡፡
ትኩረት የሚስቡ ጥያቄዎችና ትንተናዎች
በሦስት ምዕራፎች ተደራጅቶ የቀረበው መጽሐፉ፤ የተለያዩ ጥያቄዎችና መልሶችን ይዟል፡፡ በተለያዩ የስብከት መድረኮች ህዝቡ ያቀረባቸውን ጥያቄዎች በመድረክ ብቻ መመለሱ በቂ አልመሰለኝም የሚለው ፀሐፊው፤ ልማዳዊ አመለካከቶችንና ትንሽ ወጣ ያሉ ያልተዳሰሱ ምስጢሮችን ለይቼ ለምን በጽሑፍ መልስ አልሰጥበትም? አልኩኝ ብሏል - በመግቢያው ላይ፡፡ በመሃፉ ውስጥ እንደ ጥያቄ ቀርበው ፀሃፊው ምላሽና ሃይማኖታዊ ትንተና ከሰጠባቸው መካከል ጥቂቶቹን ልዳስሳቸው እሞክራለሁ - በተለይ ትኩረቴን የሳቡትንና ለየት ያሉ የመሰሉኝን በመምረጥ፡፡ ..በአንድ ሰው ቁንጅና ሰዎች ቢሰናከሉ ያ ሰው ተጠያቂ ነውን?.. ለሚለው ጥያቄ ዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ሲመልስ፤ ውበት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የተፈጥሮ ፀጋ ነው፤ ማንም ሰው በራሱ ውብ ሊሆን አይችልም ይልና አንድ ፈላስፋ ስለውበት የተናገረውን ይጠቅሳል፤ ..በምድር ላይ ያሉ ውበቶች ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያሳዩ ስስ መረጃዎች ናቸው.. እንግዲህ ቆንጆን ቆንጆ አድርጐ የሰራው የእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እናም ያ ቆንጆ ሰው ገና ለገና ሰው ተሰናከለበትና ለምንድነው ተጠያቂ የሚሆነው? ሲል ይጠይቃል - ፀሃፊው፡፡ በፀሃይ ግለት ራሱን የታመመ ሰው ፀሃይዋን ተጠያቂ ማድረግ ይችላል? አይችልም፡፡ ለምን ቢሉ? ጥላ ፈልጐ መሄድ የራሱ ፈንታ nWÂ ፀሃይ የተፈጠረችው ሰውን ለማሳመም እንዳልሆነው ሁሉ ቆንጆም ሰው ሌላውን ላሰናክል ብሎ አልተፈጠረም ባይ ነው - ፀሐፊው፡፡ ለነገሩ ቆንጆ ሆኖ መፈጠር የሰው ምርጫ ሳይሆን የእግዚአብሔር ውሳኔ ነው ወይም የተፈጥሮ ክስተት፡፡ ፀሐፊው የሰውን ቁንጅና - ያበጃጀው የእግዚአብሔር እጅ ነው - ይለናል፡፡ ስለዚህ መልከመልካም ወንዶችም ሆኑ ቆነጃጅት ሴቶች ..አሳሳች.. ወይም ..አሰናካይ.. ከሚለው የአንዳንዶች ልማዳዊ ወቀሳ ነፃ ይወጣሉ ማለት ነው፡፡
ቁንጅና ሰውን የማሰናከሉ ነገር ያስጠይቃል ወይ የሚለውን ጥያቄ ፀሐፊው  ከመሃፍ ቅዱስ ምሳሌ በመጥቀስም ያብራራል፡፡ በመሃፍ ቅዱስ ውስጥ በአብርሃም ሚስት በሳራ ውበት ሰዎች ተሰናክለዋል፤ ነገር ግን ሣራ ተጠያቂ አልሆነችም ይላል - ምናልባት ተጠያቂ የሚሆኑት ራሳቸው የተሰናከሉት እንደሆኑ በመግለጽ፡፡ በእርግጥ ሰዎች በእኛ ውበት እንዳይሰናከሉ ልንጠነቀቅላቸው ያስፈልጋል የሚለው ፀሐፊው፤ የመሃፍ ቅዱሷን ሶስና በምሳሌነት ይጠቅሳል፡፡ ሶስና መልኳን ትሸፍን የነበረው በእኔ ምክንያት ሰዎች እግዚአብሔርን እንዳያጡ ከሚል ቀና አስተሳሰብ እንጂ ተጠያቂ እሆናለሁ ብላ አይደለም በማለት፡፡
በተረፈ አንድ ሰው ሰውን ለማሳሳት ሆን ብሎ እስካልተነሳሳ ድረስ በተፈጥሮ ቁንጅናው ሰው ስለተሰናከለ ብቻ ተጠያቂ አይሆንም ነው - የዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ድምዳሜ፡፡
በመሃፉ ውስጥ ያገኘሁት ሌላው ትኩረቴን የሳበው ትንተና ..ውስጤ በሩካቤ ስሜት ይቃጠላል.. በሚል ርዕስ የቀረበው ነው፡፡ እና ምን ይጠበስ እንዳትሉ፡፡ ጉዳዩ በዚህ መልኩ ይቅረብ እንጂ ከመልሱ መንፈስ እንደተረዳሁት ጥያቄው ይሄ ስሜት ሃጢአት ነው ወይ ለማለት ይመስላል፡፡ ፀሃፊው ሲመልስም የሰው ልጅ ከአራቱ ባህርያት ከነፋስ፣ ከእሳት ከውሃና ከመሬት ተፈጥሯል፤ ከእነዚህ ባርያት እንደ መፈጠራችን እሳታዊ ስሜት በውስጣችን ሊኖር ግድ ነው በማለት ይንደረደርና ሲቀጥልም ..አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ ስሜት በውስጣቸው ብቅ ባለ ቁጥር ራሳቸውን እንደ ውዳቂ ይቆጥሩታል፤ ነገር ግን ይህ ተፈጥሮን መርሳት ነው፡፡ አንድ ሰው የሩካቤ ስሜት ትዝ ስላለው ብቻ ኃጢያተኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ እንደውም ይህ የጤነኛ ሰው ማንነት ምልክትም ምር ነው፡፡ ይህ ስሜት ከስሜት አልፎ ኃጢዓት የሚሆነው ስሜታችንን በተሳሳተና እግዚአብሔር ባልፈቀደው ጐዳና ለማርካት ስንጓዝ ነው.. ይላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው የስጋ ስሜቱን የትዳር አጋሩ ካልሆነች ሴት ጋር ለማርካት ቢሞክርና እግዚአብሔር ባልፈቀደው በየትኛውም አቅጣጫ ተጠቅሞ የሚፈም ከሆነ ኃጢአቱ ያኔ ነው . . . ሲል ማብራሪያውንና ትንተናውን በማስረጃ እያጣቀሰ በስፋት ያስረዳል፡፡
አሁን ደግሞ ..አገልጋይ እንዴት ነው የሚዝናናው?.. በሚል  የሰፈረውን ጥያቄና የተሰጠውን ምላሽ ቀንጨብ አድርጌ ላስቃኛችሁ፡፡
_Ãq½:- ከኢትዮጵያ ከወጣሁ ጀምሮ bW የሚኖሩ አንዳንድ የቤተክርስትያን አገልጋዮች የአኗኗ ዘይቤ ሀገር ቤት ከማውቀው የተለየ ነው፡፡ ሲዝናኑም XNd²W ይህ ነገር ህሊናዬን ይጠይቀኛል፡፡ ይሄም ይፈቀዳል እንዴ እላለሁ፡፡ ለመሆኑ አገልጋይ እንዴት ነው የሚዝናናው?
ፀሃፊው የዚህን ጥያቄ መልስ የሚጀምረው በማስጠንቀቅያ ወይም በማሳሰቢያ ነው፡፡ ..ሁልጊዜ አገልጋዮች ማለት ሰዎች መሆናቸውን መርሳት የለብንም፡፡ ይህን ከረሳን በቀላሉ ልንሰበር እንችላለን፡፡ ሰዎች መሆናቸውን ካልተረዳንላቸው ስህተት መስሎ በታየን ነገር ሁሉ ስንሰናከል ልንኖር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንድንሰራው ባልተሰጠን የቤት ሥራ አንጐላችንን መበጥበጥ ነው.. ይላል፡፡ በሃገራችን ስለ ቤ/ክርስትያን አገልጋይ ያለው አመለካከት ከልማድና ከባህል ጋር እንጂ በእውቀት የተደገፈና መሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም የሚለን ደራሲው፤ ..ብዙዎች አገልጋይ ጥሩ ጥሩ ልብሶችን ሲለብስ፣ ዘመናዊ መኪና ሲነዳ፣ ዘመናዊ ቤት ውስጥ ሲኖር፤ የአገልጋዩም ሚስት ዘመናዊ ልብስ ስትለብስ ከተመለከቱ አገልጋዩም ሚስቱም መንፈሳዊ ዝለት ውስጥ እንደሆኑ አድርገው የሚያስቡ አሉ.. ይለናል፡፡ ይሄ ግን ልማድ የሚሉት ያልተነቀለ አረም የተከለብን እንጂ ቤተክርስቲያን እንዲህ ዓይነት አስተምህሮት የላትም፤ ክርስትና እኮ የግዞት ኑሮ አይደለም ይላል ደራሲው፡፡ ..ያልተዳሰሱ ምስጢሮች.. በተሰኘው የዲያቆን ኃይለጊዮርጊስ ተፈራ መሃፍ ውስጥ የተነሱት ርዕሰ ጉዳዮችና ትንተናዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ ..በዓይን ፍቅር ተይዤአለሁ..፣ ..በህልሜ ያየሁትን ልጅ ላግባውን?.. ..ህግ ለፃድቃን አልተሰራም ሲባል ምን ማለት ነው?.. ..ባህል kእግዚአብሔር ሕግ ጋር ምን ግንኙነት አለው?.. እና ሌሎችም በመሃፉ ተካተዋል፡፡ እኛ ግን ወደ ሌላው የመጽሐፉ ክፍል እንለፍ፡፡
ማህበረሰባዊ ትችቶች
..ክፉ ልማዶቻችን.. በሚለው ክፍል በቀላሉ መቅረት ያለባቸው ያላቸውን ነገሮች bx„ አስቀምጧል፡፡ አንዳንዶቻችን ለፈረንጆች ያለን አመለካከት ከልክ በላይ የተመረዘ እንደሆነ የሚገልፀው ፀሃፊ፤ ለሰው ያለን ፍቅር በወንዝ የተከለለ ሆኗል ሲል ይተችና  ወንጌል ..ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሮ ነው.. የሚለው፤ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔር የለውም ይላል፡፡ አንዳንድ አስተማሪዎች ለፈረንጆች ካላቸው ጭፍን ጥላቻ የተነሳ |nÅ ሰይጣኖች.. እያሉ ያስተምራሉ በማለት የሚነቅፈው ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ፤ ይሄንን ባሉበት አንደበታቸው፣ ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይና ሰው አክባሪ እንደሆነች ይሰብኩናል ብሏል፡፡ ከሁሉም የባሰው ደግሞ ይሄንኑ በህፃናቱ አዕምሮ ውስጥ ለመሳል መታተራቸው ነው ሲል ትዝብቱን ገልል፡፡
በትምህርትም ይሁን በማንኛውም ነገር በጣም ጐበዝ ሰው ሲገኝ ..እሱ እኮ ሰይጣን ነው.. የሚል አባባል መለመዱን በማውሳትም፣ ጥሩ ሰርቶ የጐበዘን ሰው ለምን በሰይጣን እንመስለዋለን ሲል ይጠይቃል - በመሃፉ፡፡ ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ምዕመናንናም ሆነ የሃይማኖት መምህራንን ከመንቀፍ ወደ ኋላ አይልም፡፡ አንዳንድ ምዕመናን ሃይማኖታዊ ትምህርት ሲሰጥ ከልብ አይከታተሉም የሚለው ፀሐፊው፤ ነገር y¸Ã=bbù እንዳሉ ፏል - አንዱ ባልደረባዬ (ወንድሜ) የነገረኝ ያለውን እንደምሳሌ በመጥቀስ፡፡ ይኸ ወንድሙ ለምዕመኑ ስለ ሳምራዊቷ ሴት እያስተማረ ..የመጀመሪያ ባሏ ሞተ.. ሲል ህዝብ ዕልልታውን አቀለጠው፡፡ በመቀጠልም ..ሁለተኛ ባሏ ሞተ.. ሲል አሁንም ዕልል አለ፡፡ በነገሩ ተገርሞ ትምህርቱን አቁሞ መዘመር ጀመረ፡፡ ህዝቡ በዝማሬው መሃል ..እልል.. አለ፡፡ ይሄኔ መምህሩ በትክክል ዕልል ያላችሁት አሁን ነው ብሎ ወደ ትምህርቱ ተመለሰ፡፡
..ብላበት.. በሚል ርዕስ ያሰፈረው አስተያየት ደግሞ ህፃናትን ክፋት የምናስተምራቸው በዘዴ ሆኗል የሚል ስላቅ ያዘለ ነው፡፡ ..አሁንማ ህፃናትን ክፋት የምናስተምራቸው በዘዴ ሆኗል፡፡ ህፃናት አልበላም ሲሉን ወላጆች አጠገቡ ወዳለው ህፃን ጣታችንን እየቀሰርን ..ብላበት፣ እንዳይበላብህ.. ነው የምንላቸው፤ ህፃናቱን ገና kXNn¬cW ከሰው ይልቅ ራስ ወዳድ፣ ጨካኝ፣ የራሱን ጥቅም እንዲመርጥ አድርገን እንቀርፃቸዋለን፡፡ ታዲያ ይሄ ልጅ ሲያድግ ራስ ወዳድ፣ ስግብግብና ስስታም ቢሆን በማን ይፈረዳል? ከዚህ ሁሉ ህፃኑን ስለምግብ ጥቅም እየነገርነው እንዲበላ ብናደርገው ምናለበት?..
..ያነብ ነበር.. በሚል ርዕስ ስር የሰፈረው ሌላው ጽሑፍ፤ የንባብ ባህላችን ደካማ መሆኑን የሚጠቁም (የሚተችም) ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ ..የኢሳያስን መሃፍ ያነብ ነበር.. (ሐዋ.8፤28) የሚለው ደራሲው፤ በተለይ መንፈሳዊ ሁፎችን የሚያነቡ ሰዎች እግዚአብሔርን የተጠሙ ሰዎች መገለጫ ነው ይላል፡፡ bWW ዓለም ማንበብ ባህላቸው መሆኑን የሚናገረው ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ፤ የእኛ ሃገር ሰዎችን በተለይ ሴቶችን ባለማንበብ YwQúL:-
... . . እንደ ጃንደረባው ፈረንጆቹ በጉዞም ላይ እያሉ ማንበብ፣ ባቡር ውስጥ ማንበብ፣ ፕሌን ውስጥ ማንበብ፣ የትም ቦታ ከመሃፍ ጋር አይላቀቁም፡፡ የእኛ ሀገር ሴት ቦርሳዋ ውስጥ ሽቶና ሊፕስቲክ ይገኝ ይሆናል፡፡ በእነርሱ ቦርሳ ውስጥ ግን መሃፍ ነው የሚገኘው፡፡..
ፀሃፊው የአገራችን ህዝብ (እኛ) መቼ ይሆን አንባቢ የምንሆነው? መቼ ይሆን ደራሲያን አዕምሮአቸውን ጨምቀው የጋገሩልንን ምግብ ተሻምተን የምንበላላቸው? መቼ ይሆን እኛ አገር እንደ WW ዓለም መሃፍ በሰልፍ የሚሸጠው? መች ይሆን አለማንበባችን እንደጐዳና የሚሰማን? ሲልም የጥያቄ ዶፍ ያወርዳል፡፡ መጽሐፉ ሌሎችንም በመንፈሳዊ መጽሐፍ የማይደፈሩ ጥያቄዎችን እያነሳ ይተነትናልና ቢነበብ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!

 

Read 4626 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:23