Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 03 September 2011 12:47

እሹሩሩ.. ቪሲዲ ዛሬ፤ ..የትሮይ ፈረስ.. ሰኞ ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

..ዘመን ሲሽር.. አርብ ይመረቃል
በመላኩ ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀው ..እሹሩሩ.. የተሰኘ የኮሜዲ ቪሲዲ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 በአዲስ አበባ ባህልና ትያትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መላኩ ገብሩ ጽፎ ፕሮዲዩስ ያደረገውን የአንድ ሰዓት ኮሜዲ ቪሲዲ ያዘጋጀው ታደሰ ንጉሥ (አቡ) ነው፡፡በፊልሙ ፋንቱ ማንዶዬ፣ ፍቅርተ ጌታሁን፣ ተመስገን መላኩ፣ ፀጋዬ ዘርፉ፣ ሰብለ ተፈራ፣ ወንድወሰን ብርሃኑና ሌሎችም ተውነዋል፡፡በሌላም በኩል በአሳምነው ባረጋ ልቦለድ ድርሰት ላይ ተንተርሶ የተሠራው ..የትሮይ ፈረስ.. ፊልም ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይመረቃል፡፡

በ100 ደቂቃ ፊልሙ ላይ ፍቃዱ ከበደ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ይገረም ደጀኔ፣ ዕፀሕይወት አበበ፣ ¹êf‰hù ደሳለኝ፣ ጌታሁን ሰለሞን ተውነዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ..ዘመን ሲሽር.. የተሰኘ የግጥም ሲዲ (audio) በመጪው አርብ በጎንደር ከተማ ይመረቃል፡፡ በከተማዋ ቋራ ሆቴል የሚመረቀውን 34 ግጥሞች የያዘ ሲዲ የደረሰው ዘላለም ጌጡ ነው፡፡ ዘላለም ካሁን ቀደም ..ሳላይሽ.. እና ..እንጎቻ.. የተሰኙ የግጥም ሲዲዎች አሳትሟል፡፡በካሳሁን ዓለሙ የተዘጋጀው ..ሀልዎተ እግዚአብሔር.. መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ 267 ገፆች ያሉት መጽሐፍ ዋጋ 40 ብር ነው፡፡

Read 3806 times

Latest from