Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:41

የአፍሪካ ሥነሑፍ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀበሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኮድ ኢትዮጵያ ባስተባበረውና ኮድ ካናዳ ድጋፍ ያደረገለት በርት የአፍሪካ ሥነ ሑፍ ሽልማት አሸናፊዎች ባለፈው እሁድ ሽልማታቸውን የካናዳ ኤምባሲ አንደኛ ፀሃፊ ሚስ ማጋን ካየርስ ባሉበት ከትምህርት ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም እጅ ተቀበሉ፡፡  በውድድሩ አንደኛ የወጣው |Young Crusaders´ የሚል መሐፍ የፃፈው ጋዜጠኛና መምህር ሰለሞን ኃይለማርያም ሁለት መቶ ሰባት ሺህ ሃምሳ አራት ብር፣ ሁለተኛ የወጣው የ |Escape´ ፀሃፊ ደራሲ ገበየሁ አየለ አንድ መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሰባት ብር፣ ሦስተኛ የወጣው ሜሮን ተክለብርሃን የፃፈችው |The Letter´ መሐፍ ሃምሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ብር ከሃምሣ ሳንቲም ተሸልሟል፡፡

ሦስቱ ፀሐፍት ከሃያ ስድስት ፀሃፍት መካከል በዳኛ ውሳኔ የተመረጡ ሲሆን ስልጠና ተሰጥቷቸው በስድስት ወር ጊዜ ጽፈው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ የኮድ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ዱባለ፤ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ የሥነ ጽሑፍ ውድድር ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልው፣ ሦስቱ መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በአምስት ሺህ ቅጅ እንደተዘጋጁና ለዩኒቨርስቲዎችና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በነጻ እንደሚሰራጩና ከነዚህ የተረፉት በተመረጡ መጻሕፍት መደብሮች በዝቅተኛ ዋጋ ለሕብረተሰቡ እንደሚዳረሱ በተለይ ለአዲስ አድማስ ገልዋል፡፡
ከ15-18 ዓመት ያሉ ወጣቶችን ታሳቢ በማድረግ የተጻፉትን የእንግሊዝኛ መጻሕፍት እንደገና የማሳተምና የመሸጥ መብት የደራሲያኑ ሲሆን ይህን ሲያደርጉ ግን ለኮድ ኢትዮጵያና ለበጎ አድራጊው ለሚስተር ቢል በርት እውቅና እንዲሰጡ ከስምምነት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም፤ ኮድ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ሲናገሩ፤ በገጠር ንባብ ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ1994 የተቋቋመው ኮድ ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት እስካሁን 1.5 ሚሊዮን መጻሕፍት ያሰራጨ ሲሆን ላቋቋማቸው 82 የማህበረሰብ ቤተ መፃሕፍት መፃህፍት ገዝቶ በማሟላትና አዳዲስ ቤተ መጻሕፍት በማቋቋም ይታወቃል፡፡

 

Read 4038 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:43