Saturday, 03 September 2011 12:23

..መዝናናት መዝናናት! አሁንም መዝናናት!.. ጓድ ሌኒን (ያልተጮኸ ውስጣዊ መፈክር)

Written by  ስብሃት ገ/ እግዚያብሔር.
Rate this item
(1 Vote)

ገድለ ጊልጋሜሽ  
The Epic of Gilgamesh

የተከበራችሁ  አንባብያን
ይህ ታሪክ የተፃፈው Akkadian በሚባል፣ እንደ አማርኛ Semitic ተብሎ በሚፈረጅ ቋንቋ ነበር፡፡ የተደረሰው ከክርስቶስ ልደት ሁለት ሺ አምስት መቶ አመት በፊት፡፡ ይህም እኛ በምናውቀው አለም ታሪክና ባህል የመጀመርያው Epic Poem (ገድላዊ r?M Qn¤) ያሰኘዋል፡፡ እንዲህ  የይተረካል
የመላው አለም እምብርት በሆነችው ከተማ የነገሰ፣ ጊልጋማሽ የሚባል ጉብል ነበረ፡፡  ያገር ጉዳይ የማካሄዱን ጣጣ ለባለሟሎቹ እየተወላቸው እሱ ቀኑን የሚያሳልፈው ወደ ጫካ ምንም መሳርያ ሳይዝ ዘምቶ፣ አደገኛ አራዊት በማደን ነበር፡፡ የሁለት ሳምንት ስንቅ አስጭኖ ይመርሻል!
ጊልጋሜሽ መልኩም ቁመናውም እንደ አማልክቱ ያማረ በመሆኑ፣ የፍቅር አማላክት (Astarte (Ishtar, አስቴር) አፈቀረችው፣ ነሆለለችለት!

ከሰማይ ቤት ወርዳ ..አፍቅሬሀለሁ.. ብትለው፣ ንግግርዋን ለመቀጠል እንኳ ጊዜ ሳይሰጣት ..ቸኩያለሁ፡፡ ለሴት ፍቅር ጊዜ የለኝም.. ብሏት በፈጣን እርምጃ ወደ ጫካው ሄደ፡፡
አስታርቴ ተቆጣችም፣ ተቀየመችም፡፡ ይህን ንቀቱን ለመበቀል ኤንኪዱን ፈጠረችና ጊልጋሜሽ እሚያድንበት ጫካ ውስጥ አኖረችው፡፡ ኤንኪዱ እንደኛ ኦሪት ዘፍጥረት ኤሳው የአውሬ ፀጉር ያበቀለ፣ ግን አእምሮው እንደ ሰው የሚያስብ ነው፡፡
ኤንኪዱ እንደ ብልጥ አውሬ መሸሽ፣ መደበቅ፣ ማድፈጥ ብቻ ሳይሆን እሱም አፀፋውን ጊልጋሜሽን እያደነው ነው፡፡
ጊልጋሜሽ ባለ አራት ፎቁን ህንፃ እንደ ሸህላ ጡብ ብድግ አድርጎ ሲወረውርበት፣ ኤንኪዱ ትልቁን ዛፍ እንደ ሰንሰል በቀላሉ ነቅሎ እንደ ገል እቃ ይፈረካክሰዋል ያንን ህንፃ፡፡
...ሲፋለሙ ውለው ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር፣ ጊልጋሜሽ ጮክ ብሎ ..ስማኝ ጐበዝ፣ ና እኔ ግቢ እደርና ነገ ጧት ተነስተን ፍልሚያው ይቀጥላል..
እራት እየበሉ ወይን - ፀጅ እየጠጡ፣ ስለዋሉበት ግጥሚያ በዝርዝር ሲያወሩ፣ ለእርስ በርሳቸው ያደረባቸው አድናቆትና ፍቅር እየበዛ ሄደ፡፡
በነጋታው ተነስተው፣ ሊፋለሙ ሳይሆን አብረው አንድ አዳኝ ሆነው ደስታ ፍስሀ ውስጥ ለመዋል አቅደው፣ ሩቅ ወደ ሆነ አዲስ ጫከ መረሹ፡፡ ሶስት ቀን ሰንብተው ተመለሱ፡፡
ኢሽታር ይህን አይታ ተቀየመች፡፡ በቀል ላከችባቸው፡፡ በነጋታው ጧት ጊልጋሜሽ ለአደን ሲዘጋጅ፣ ኤንኪዱ ..አንተ ሂድ፡፡ እኔ አሞኛል.. አለው፡፡
ጊልጋሜሽ ጓደኛውን ሲያስታምም ዋለ፡፡ ኤንኪዱ ምግብ እየተወ፣ ቀን በቀን እየከሳ፣ እየመነመነ ሄደ፡፡ በንጉስ ጊልጋሜሽ ትእዛዝ ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ፣ ቅጠላ ቅጠል የሚበጥሱ፣ ስራስር የሚምሱ፣ ጠጠር የሚቆጥሩ፣ የበግ አንጀት የሚመረምሩ፣ አስማት ድግምት የሚያውቁ፣ እና ሌሎችም መጡ፡፡ ማናቸውም ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ ኤንኪዱ እየመነመነ ሰንብቶ ሞተ...
...ጊልጋሜሽ ከድሮው ተለወጠ፡፡ አደን ሄዶ አራዊት ሲገድል መሞታቸውን ያውቅ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እንኳ ..ሞት.. ቃል ብቻ ነበረ፡፡ ዛሬ ግን እውነት ሆኖ ታየው፡፡ ..እኔም እንደ ኤንኪዱ መሞት አይቀርልኝም!..
ኤንኪዱን ለማዳን አስጠርቷቸው የነበረውን መድሀኒት አዋቂዎች ሁሉ ዛሬ ለራሱ ጉዳይ ሰበሰባቸው፡፡ ..የሞት መድሀኒት አለ ወይ?.. አላቸው
..አይታወቅም.. አሉት
..ከሞት ያመለጠ ሰው ታውቃላችሁ ወይ?..
አናውቅም አሉት፣ ስብሰባው ተበተነ፡፡ በኋላ ግን አንድ አዛውንት መጥተው ታሪካዊ መዛግብትና የሀይማኖት መፃህፍት ወደ ተቀመጡበት አዳራሽ ወስደው ኡት-ናፒሽቲም የጻፈውን አስነበቡት፡፡ (ፀሐፊው ንጉስ ከጊልጋሜሽ ጀምረን ወደ ኋላ ስንቆጥር አሥራ አራተኛው ንጉስና ቀጥተኛ ቅድመ አያቱ መሆኑ ነው፡፡)
..እኔ ኡት-ናፒሽቲም የፍቅር አምላክ ኢሽታሮ ከሰማይ ወርዳ ወደደችኝ፣ እኔም ህይወቴን ሰዋሁላት፡፡ አስራ አራት ዓመት ሙሉ በፍቅር ተገዛሁላት፣ አገለገልኳት፡፡ እና ጊዜው ደርሶ መለያየት ሊኖርብን ሆነ፡፡
..ለቅን ትጉህ አገልግሎቴ የህይወት ዛፍ ወደበቀለችበት አገር በመርከብ እሄድ ዘንድ መንገዱን ከነምልክቱ አሳየችኝ፡፡ እንዲህ ተናገረችኝ ትንቢት አለ፡፡ እንኳን እናንተ ሟቾች ቀርቶ እኛ አማልክት ከትንቢቱ ዝንፍ ማለት አንችልም፣ እንዳይፈም ብንፈልግም፡፡
..ትውልዶች ካለፉ በኋላ ከልጅ ልጆችህ ከአንዱ ጋር ፍቅር ይይዘኛል፡፡ እሱ ግን ይንቀኛል፡፡ ስለዚህ ከሞት ጋር አጋፍጠዋለሁ፡፡ ባንተ መንገድ እንዳንተ የሞት መድኃኒትን ለማግኘት ሁሉን ጥሎ ይጓዛል፡፡
..አሁን ላንተም ለሱም መንገዱን ላመላክታችሁ፡፡ በወንዙ በውሃም በጊዜም እየተንሳፈፉ ይወስዱዋችኋል፡፡ የናንተ ፀሐይ የምታበራበትን ዓለም አልፈህ ሌላ ፀሐይ የምታበራበት አለም ትደርሳለህ፡፡ የምታሞቅህ፣ የምታስደስትህ፣ ለሥራ የምታነሳሳህ ናት፡፡ እዚያ ወደብ ስትደርስ ..የኢሽታር እንግዳ ነኝ.. ትላቸዋለህ፡፡ ሦስት ሳምንት አስተናግደው እስከሚቀጥለው ዓለም የዓለም ወደብ የሚያደርስ ስንቅ ጭነውልህ ይሸኙሃል፡፡ የሚቀጥለው አለም ስትደርስ ፀሀያቸው የተስያት ናት፡፡ ታቃጥልሀለች፣ ላብ ያጠምቅሀል፡፡ አገሬው ሰው ግን እዚያ ለመኖር የተፈጠረ በመሆኑ ካልሮጠ አያልበውም፡፡ ሶስት ሳምንት ሰንብተህ፣ ወደሚቀጥለው አለም ሳትቀጥል በቂ ተሰንቆልህ ..ምስጋና ለኢሽታር.. ተባብላችሁ ትሸኛለህ፡፡
የሚቀጥለው የጉዞህ ምእራፍ ስትደርስ ፀሃይዋ የወደ ዘጠኝ ሰአት ላይ ብርሀንና ሙቀት አላት፡፡ እዚያም መልህቅ ጥለህ ሶስት ሳምንት ሰንብተህ ጉዞህን ትቀጥልና፣ ፀሃይዋ ልትጠልቅ በቋፍ ተንጠልጥላ የምትውልበት አለም ትደርሳለህ፡፡
የህይወት ዛፍ የምትበቅለው እዚያ ነው፡፡ በኔ በኢሽታር ፍቅር አይን ስትሻት አውቃ ትታይሀለች...
...ጊልጋሜሽ እዚያ አለም ወደብ ደርሶ መልህቅ ሲጥል በብርድ እየተንቀጠቀጠ ነበር፡፡ ለኢሽታር ፍቅር ስለሌለው የህይወት ዛፍ እንደማትታየው ያውቃል፡፡ ስለዚህ መጀመርያ ያገኘውን ሰው በኢሽታር እንግዳነት ስም ..ኡት-ናፒሽቲም እዚህ ይኖራልን?.. ሲል ጠየቀው፡፡  
|xþT-ናፒሽቲም እንደነዚህ እንደምታያቸው ተራራዎች ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ነበር ይባላል፡፡ አምላክ ነው እንዳንል ምንም ተአምር ሲሰራ አላየንም፡፡ አይሞትም እንጂ ይርበዋል፣ ያንቀላፋል.. ብሎ የኡት-ናፒሽቲምN መኖሪያ አመላከተው፡፡
ሲገናኙ ሁለቱም እኩል ተደሰቱ፡፡ እየበሉ እየጠጡ ሲጫወቱ ኡት - ናፒሽቲም ..እኔ ወዲህ ከመጣሁ በኋላ በአገራችን የተሰራውን ታሪክ አንድ በአንድ አውራልኝ.. አለው፡፡ ነገረው፡፡
ቀጥሎ ጊልጋሜሽ ..አንተ ደሞ ተራህን እስካሁን ስለኖርከው ንገረኝ.. ሲለው፣ bdS¬ ብሎ እንደሚቀጥለው አጫወተው...
ያገራችን ፀሀይ የምታበራበትን አለም አልፈህ እዚህ ስትደርስ እኔና አምስተኛው አለም ተቀበልንህ (ሲል ጀመረ ኡት - ናፒሽቲም) አራት ሌሎች አለማት አሉ፡፡
አንደኛው አለም ውስጥ አንድ አይናዎች ይኖሩበታል፡፡ እዚያ እነ ቱሀን እኛን ያክላሉ፣ ሰዎቹ ቱሀን ያክላሉ፡፡  
የቱሀን ፈስ ግማቱ መኖርህን ያስጠላሀል፡፡ ውስጥህ ያለውን ሁለመናህን እያስታወክከው እንደሆነ እርግጠኛ ነህ፡፡ እዚያ ያልሞትኩት፣ ኢሽታር በምስጢራዊ ፍቅርዋ ስለጠበቀችኝ ነው እላለሁ፡፡
ሁለተኛው የእስስትነት አለም ነው፣ ሁለት አይናዎች ይኖሩበታል፡፡ አንተም ያየኸውን ሰው ትመስላለህ፣ እሱም አንተን ይመስላል፡፡ አንተ ነህ ወይስ እሱ ነው እውነት እና ሌላው ማስመሰል?
ከዚህም ጋር ያ አለም ራሱ መመሳሰል እንጂ መኖር አይታይበትም፡፡ የለም ማለት ነው? ከሌለማ ከየት መጥቶ ያስመስላል?
ሶስተኛው የፍቅርና የምህረት አለም ነው፣ ሶስት አይናዎች ይኖሩበታል፣ ሶስተኛ አይናቸው ግምባራቸው ላይ ነው፡፡ (አለ ሲቀጥል ኡት-ናፒሽቲም) ኢሽታር ስለተቀየመችህ ትኖርበት ዘንድ አይሆንልህም እንጂ በሀሳብ ደረጃ ላቀብልህ እችላለሁ፡፡ ከአማልክቱ ጋር በፍቅር ከመዋሀዳችን የነተሳ፣ እነሱ ለኛ ምስጢር የሚሆኑብንን ያህል፣ እኛ ምስጢር የምንሆንባቸው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜማ እነሱ ፈጠሩን ወይስ እኛ ፈጠርናቸው? ብዬ አስባለሁ፣ ኢሽታር በምህረት ይቅርታ ከክፉ ትጋርደኝ እንጂ፡፡
አራተኛው የእውቀትና የጥበብ አለም ነው፤ ባለ አራት አይኖች ይኖሩበታል፡፡ ሁለቱ አይን ፊት ለፊት ያያል፣ ሁለቱ የኋሊት ይታየዋል፡፡ ስለዚህ መደባበቅ አይቻልም፡፡ ማለትም ሀቅ በሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ GT QQ የለም፡፡ ጦርነትማ ታስቦም አያውቅ፡፡
ኡት - ናፒሽቲም ነግሮት ሲጨርስ፣ ጊልጋሜሽ ..ከዚህ የሚቀጥለውን አለም ጐብኝቼ ብመለስ ምን ይመስልሀል?.. አለው
..እኔ እስካለሁበት አለም እንድትመጣ ኢሽታር የፈቀደችልህ ትንቢቱን ልትቃወመው ስልጣን ስለሌላት ነው እንጂ ወደ ጐረቤታችን አለም ብትሄድ ትሞታለህ፡፡ እዚያ ልትኖር ስላልተፈጠርክ አገሩ ይጣላሀል፣ ትሞታለህ..
በሌላ ጊዜ ጊልጋሜሽ ..ልጠይቅህ  እስቲ.. አለው ..ይህን ሁሉ ዘመን ስትኖር አይሰለችም? እንድያውም፣ እንቅልፍ ተኝተን እንደምንነሳ ሞተን መነሳት ቢቻል ኖሮ፣ በአመት ሁለት ሳምንት ሞቼ እነሳ ነበር፡፡ አስበው፣ ሁለት ሳምንት ሙሉ አእምሮህ ከሀሳብ ሲገላገል፡፡ ካልሞትን ለደቂቃ እንኳ ላለማሰብ አንችልም፡፡..
..መተንፈስማ ሁልጊዜ ይመቻል፡፡ መብላትም ያስደስታል፡፡ ግን ሁልጊዜ  መብላት ቢኖርብህስ? ኩነኔ አይደለምን? ይሄ የሆድ ነው፡፡ የአእምሮ ኩነኔ ግን ከዚያም ይብሳል..
..እንዴት?.. ጠየቀ ጊልጋሜሽ
..ከሁሉ የምትፈራውና የምትጠላው ቅዠት የለህም..
..አለኝ $r ልጅ ሆኜም መሮጥ እወድ ነበር፣ በጉርምስናዬም አደን የማፈቅረው የእለት ስራዬ ነበር፡፡ ከኡር መዲናችን እስከዚህ የተጓዝኩት ደግሞ እንደ አበባ ወይ እንደ ምሽት ዳመና ያምር ነበር፡፡ እነ ኢሽታር በዚህ በራሪ ወፍ በመሰለ ነፃነት የቀኑብኝ ይመስል፣ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ጊዜ ያንኑ አንድ ቅዠት እየላኩ ይቀጡኛል፡፡  
..አሁን ስነግርህ እንኳ ፍርሀቱ እየተሰማኝ ነው፡፡ የደረቀ ባዶ ውሀ ጉድጓድ ውስጥ ቆሜአለሁ፡፡ ምንም ያህል ብዘል፣ አፋፉን ደርሼበት ተቆናጥጬ መውጣት አልችልም፡፡ ግን መውጣት አለብኝ፡፡ እዘላለሁ አልደርስም፣ እዘላለሁ አልደርስም፡፡ እንዲህ እያለ ቅዠቱ ዝንታለሙን የሚያበቃ አይመስልም፡፡ አንተስ ቅዠት ሳይኖርህ ይቀራል?.. ..አይቀርልኝም፣ እኔም ሰው በመሆኔ፡፡ ቅዠቴ አንተና የዘላለም ህይወት ዛፍ ቀምበጥ ናችሁ.. ..እንዴት?.. ጠየቀ ጊልጋሜሽ፣ የልቡ ፈጣን ምት ደረቱን እያስጨነቀው፡፡ ..ቀምበጤ የት ሄደች?.. እያልክ፣ ፍለጋ አገሩን ታተራምሰዋለህ፣ ግን አታገኛትም፡፡ ቅዠቱ በቂ አሰቃይቶኝ ስነቃ ..እውነታው አለም.. በምንለው ውስጥ አንተ ወደዚህ ለመቅዘፍ ገና አልተነሳህም..
ጊልጋሜሽ ከኡት - ናፒሽቲም ጋር አምስት አመት ኖረ፡፡ ወደ አገሩ ሊመለስ ሲሰነባበቱ፣ አስተናጋጁ ..በጣም እድለኛ ነህ፡፡ እቺ የህይወት ዛፍ በመቶ አመት አንድ ጊዜ ብቻ አንዲት ተቀጥፋ የምትበላ ቀምበጥ ታበቅላለች፡፡ ይኸው፣ አንተ መጥተህ አበቀለች፡፡ ቀጠፍኩዋት.. እያለ በቁመት መሀል ጣት የምታክል፣ እንደ ቅጠልያ ብርሀን ቀምበጥ ሰጠው. . .
. . . ጊልጋሜሽ ቀምበጥዋን እንደጨበጠ መርከቡን ወደ ተወበት ወደብ ሲራመድ rM ሰአታት አለፉ፡፡ ውሀ ጥሙ ከውሀ ሌላ ሀሳብ እንኳ ከለከለው፡፡ በመጨረሻ አንዲት MN አገኘ፡፡ ሮጦ በሁለት እጁ እያፈሰ ጠጥቶ፣ ፊቱንና ራሱን ታጠበ፡፡ ..ቀምበጥዋን የት ጣልኳት ስስገበገብ?.. እያለ ቢመለካከት፣ እባብ በአፉ ነክሷት ወደዚያ እየተንሸራተተ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባ፣ ተሰወረ፡፡ ኤሽታር ልካው መሆን አለበት
ጊልጋሜሽ ወደ ኡት - ናፒሽቲም ሊመለስ ከጀመረ በኋላ ..ዛሬ ባላሳዝነው ይሻላል.. አለ ለራሱ ..አገሬ ገብቼ አርጅቼ ስሞት፣ ኢሽታር ከፈለገች ታረዳዋለች.. የጊልጋሜሽ ገድል እንደዚህ በትራጀዲ ይፈፀማል፡፡ የሁላችንም ትራጀዲ ነው፡፡ ሰአሊለነ  ቅድስት
ምእራፍ ሁለት
ከርታታው ይሁዲ  
የካርታታው ይሁዲ እጣ-ፈንታ የጊልጋሜሽ ተቃራኒ ነው፡፡ እንዲህ ይተረካል - ያቺ አርብ ተስያት ላይ ጌታ ኢየሱስን ከገረፉት በኋላ እየተሳለቁበት ሊሰቅሉት መስቀሉን አሸክመው ግርፋቱን እየቀጠሉ እያለ፣ አንድ ሱቅ ስር ጥላ አይቶ፣ ለአንድ አፍታ ለመጠለል የቅበት እረፍት እየናፈቀ ሊቆም ሲል፣ ሂደቱን ቆሞ ሲመለከት የነበረው ባለ ሱቅ ወደ ፀሀዩ እየገፈተረወ:- ..ወንጀለኛ አናስተናግድም፡፡ መንገድህን q_ልቀጥል´ አለው ጌታም በቀረችው ትንፋሽ ..እኔስ እየሄድኩ ነው.. አለው ..አንተ ግን እስክመለስ እዚህ ትጠብቀኛለህ.. ያን ጊዜ ሰውየው በግምት የሰላሳ አመት ጐልማሳ ነበረ፡፡
ጊዜ አለፈ፡፡ ጌታ ሲሰቀል ህፃናት የነበሩት አደጉ፣ ጐረመሱ ሸመገሉ፡፡ እና መንከራተት የተፈረደበትን ሰውዬ ..እኛ ተወልደን አረጀን፡፡ አንተ ግን እንኳን አርጅተህ ልትሞት፣ እስከ ዛሬ አንዳች ለውጥ አላየንብህም፡፡ ምን ማለት ነው?.. ጠየቁት ወደ ሌላ ከተማ ለመሰደድ ተገደደ፡፡ እዚያ ንግዱን እየቀጠለ ወዳጆች አበጀ፡፡ እነዚህ እያረጁ እያለፉ፣ ልጆቻቸው ተተክተው አድገው ማርጀት ሲጀምሩ ..እኛ እያየኸን ተወልደን አረጀን፡፡ አንተ ግን -.. ሲሉት፣ ወደ ሌላ ከተማ ሲሰደድ . . . የትም ቢሄድ የትም፣ ያው የመኖር ቀምበር  እየሰለቸው፣ መሞት እየተመኘ ሄደ፡፡ ቀጥሎ ሞትን ለማግኘት አደን ጀመረ፡፡ The Black Death የተባለው በሽታ የኤውሮፓን ህዝብ ሶስት አራተኛውን ፈጀ፡፡ ከርታታው ይሁዲ ሞትን ፍለጋ እዚያ ሄዶ፣ ተላላፊውን ገዳይ በሽታ በመፍራት ወላጆቻቸው ወይም ልጆቻቸው በባዶ ቤት ጥለዋቸው የሸሹትን ታማሚዎች እንደ ዘመናችን እማሆይ ቴሬዛ አቅፎ ደግፎ እያስታመማቸው ለሞት ሲያስረክባቸው፣ ሞት ከርታታውን ይሁዲ ተፀይፎት ያልፋል፡፡ ጦርነት ወደ ተነሳበት አገር እንደ ቅዱስ ገብርኤል ፈጥኖ ይደርስና፣ ደካማ በመሰለው ወገን ተሰልፎ፣ ግምባር ቀደም ሆኖ ይዋጋል፣ ይጨፈጭፋል ሆን ብሎ ለጦር፣ በሚቀጥለው ዘመንም ለጥይት ደረቱን ይሰጣል፡፡ ሞት ተፀይፎት ሳይጨርፈው ያልፋል፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን፣ ይሁዲያችን የማያውቀው ሀይል አስገድዶ በየሀምሳ አመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይወስደዋል፡፡ ..ዛሬ ጌታ ኢየሱስ ወደዚያች ነጃሳ ሱቄ ተመልሶ ብንገናኝስ?.. እያለ ይመኛል፣ ይፀልያል፡፡ እስከ ምአት ድረስሰአሊ ለነ ቅድስት
ቸር ይግጠመን!!

Read 3980 times