Saturday, 03 September 2011 12:18

በአዲስ አበባ ..የውሻ በሽታ.. እየጨመረ ነው - ፓስተር

Written by  ሂሮዬ ሺማቡኩሮ
Rate this item
(1 Vote)
  • በጃፓን ውሻን ከግቢ ውጪ መልቀቅ ያስጠይቃል
  • - በውሻ ተነክሼ 12 ሺ ብር ለህክምና ተጠይቄአለሁ
  • - በአዲስ አበባ ..የውሻ በሽታ.. እየጨመረ ነው - ፓስተር

ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደመጣሁ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ውሾች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩባቸው ስመለከት     እደነግጥ ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ
ውሾቹ አለመቆጣታቸው ነው፡፡ በጃፓን ውሻ ላይ ድንጋይ መወርወር እንስሳትን በማሰቃየት ወንጀል ያስጠይቃል - ያሳስራልም፡፡ ያን ጊዜ ድንጋይ የተወረወረባቸው ውሾች ህመሙ ተሰምቷቸው ሲያለቅሱ ልቤ እየታመመ ኢትዮጵያውያኑን እወቅስ ነበር - ምን ዓይነት ጨካኞች ቢሆኑ ነው እያልኩ፡፡

አሁን ግን ቢያንስ ለምን ሰዎች ውሾች ላይ ድንጋይ እንደሚወረውሩ ገብቶኛል - ምክንያቱም ብዙ አስፈሪ ገጠመኞች አሳልፌአለሁና፡፡ በየመንገዱ ብዙ ኃይለኛ ተናካሽ ውሾች ገጥመውኛል - አደገኛውን የራቢ ቫይረስም ሊያሲዙኝ እንደሚችሉ አውቃለሁ፡፡ ስለራቢ ሰምታችሁ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ ግን አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለዚህ ቫይረስ እምብዛም የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ በዓለም ላይ በየዓመቱ ከ55ሺ ሰዎች በላይ በራቢ የሚሞቱ ሲሆን በኢትዮጵያም ብዙዎች በቫይረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ወደራሴ ገጠመኝ ከማለፌ በፊት እስኪ መጀመሪያ ስለዚህ አደገኛ ቫይረስ ትንሽ ነገር ልበል፡፡ ራቢስ ባለበት ውሻ ከተነከሳችሁና ቫይረሱ ወደ ሰውነታችሁ ከገባ እናም ወደ ህክምና ካልሄዳችሁ ዕጣ ፈንታችሁ ሞት ይሆናል፡፡ የመዳን ተስፋ የለውም - ያለ ህክምና፡፡ ቫይረሱ አዕምሮ ላይ ሲወጣ ነው ሞት የሚከሰተው፡፡ ነገር ግን ወደ አዕምሮ የሚወጣው ቀስ በቀስ ነው፡፡ ሰዎች እንደ ሁኔታው በ10 ቀናት ውስጥ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ግን ከአንድ ዓመት በላይም ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ቫይረስ ዝርዝር ጉዳዮችን አላነሳም፡፡ ነቄ የአዲስ አድማስ አንባቢዎች ግን ቫይረሱ የቱን ያህል አደገኛ እንደሆነ ከድረ ገፆች ላይ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ራቢስ በአማርኛ ..የውሻ በሽታ.. እንደሚባል ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን ማንኛውም እንስሳት ራቢስ ሊኖርባቸውና ሰዎችን በቫይረሱ ሊያሲዙ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ግን የራቢስ ቫይረስ በአብዛኛው የሚመጣው ከውሾች እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ስለዚህ ከዚህ ቫይረስ መከላከያው አስተማማኙ መንገድ ውሾችን ማስከተብ ብቻ ነው፡፡ ውሻችሁን ክትባት ካስከተባችሁ በራቢስ አይያዝም፡፡ ጃፓንን በመሳሰሉ አገራት ቤቱ ውስጥ ውሻ ያለው ማንኛውም ሰው ማስከተብ ግዴታው ነው፡፡ ጉዳዩ እንደቀላል የሚታይም አይደለም፡፡ ለምሳሌ ውሻችሁ ሰው ቢነክስና ሰውዬው በራቢስ ቢያዝ በቁጥጥር ስር ትውላላችሁ፡፡
አሁን ወደ ኢትዮጵያ ልመለስና SlኢትዮጵያêEa ጐረቤቴ ልንገራችሁ፡፡ ጐረቤቴ ሦስት ውሾች ሲኖሯት እነዚህ ውሾች ከግቢዋ ውጪ እየተለቀቁ እንዳሻቸው የሚሮጡ ናቸው፡፡ አንድ ቀን መንገድ ላይ ከእነዚህ ውሾች አንዱ ነከሰኝና እግሬ ደማ፡፡ ወዲያው ወደ አዕምርዬ የመጣው የ..ራቢስ.. ቫይረስ የሚለው ነበር፤ እናም ፈራሁ፡፡ የውሾቹ እመቤት ከቤቷ ወጥታ የተነከስኩትን አየች፡፡ ..ወይኔ´ ስትልም ሃዘኔታዋን ገለችልኝ፡፡ ከዚያም ..አይዞሽ ይሄ ውሻ ጤነኛ ነው.. አለችኝ - ከራቢስ ቫይረስ ማለቷ ነው፡፡ ተናድጄ አንድ ነገር ልናገራት አሰብኩና ትቻት ወደ ቤቴ ሄድኩኝ፡፡ ምክንያቱም ራቢስ አለበት ተብሎ በሚጠረጠር ውሻ የተነከሰ ሰው በመጀመሪያ ማድረግ ያለበት ነገር ቢያንስ ለ15 ደቂቃ የተነከሰውን የሰውነቱን ክፍል በውሃና በሳሙና ማጠብ ነው፡፡ እኔም እንደዛው አደረኩኝ፡፡በነጋታው ወደ ሴትዮዋ ቤት ሄድኩኝና ውሻዋን ያስከተበችበትን ማስረጃ እንድታሳየኝ ጠየኳት፡፡ ውሻው ከሦስት ወር በፊት መከተቡን ነገር ግን ማስረጃ ወረቀት እንደሌላት ነገረችኝ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ውሻቸውን እንደማያስከትቡ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ጐረቤቴን ማስረጃ ሳታሳየኝ ላምናት አልቻልኩም፡፡ በዚያ ላይ ግዴለሽ ሰው መሆኗን አውቄአለሁ፡፡ ግዴለሽ ባትሆንማ ውሾቿን መንገድ ላይ እየለቀቀች መንገደኞችን ለአደጋ አታጋልጥም ነበር፡፡ ያ የነከሰኝ ውሻ ክትባት ያልተከተበ ከሆነ በመንገድ ላይ ካሉት ውሾች ራቢስ ሊይዘው ይችላል፡፡ እናም እኔም በራቢስ ቫይረስ ተጠቅቼ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለህክምና ወደ ክሊኒክ ከመሄድ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ ለህክምናው የተጠየኩት ክፍያ አስደንጋጭ ነበር፡፡ 12ሺ ብር አስከፈሉኝ፡፡ ክሊኒኩ የነከሰኝን ውሻ ለ10 ቀናት ያህል እንድከታተለው ነግሮኝ ነበር፡፡ ውሻው ራቢስ ካለበት ምልክቶቹ ይታይበትና በመጨረሻም ይሞታል ብለውኛል፡፡ አያችሁ ውሻው ሲነክሳችሁ ጤናማ ሊመስል ይችላል፤ ምክንያቱም ምልክቶቹ ወዲያውኑ xY¬†M””ክሊኒኩ ለህክምናው ካስከፈለኝ ገንዘብ የበለጠ ያስደነገጠኝ ግን እኔም ከተነከስኩ በኋላ እንኳን ውሻውን መንገድ ላይ ማየቴ ነው፡፡ ፈጽሞ ማመን አቃተኝ፡፡ የውሻው መንገድ ላይ መለቀቅ ብቻ ሳይሆን የባለቤቱ አስተሳሰብም አስፈራኝ፡፡ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋለች? እሺ ስለ ራቢስ ምንም የምታውቀው ነገር የለም እንበል፡፡ ቢያንስ  ግን ውሻው ሰው መንከሱን አሳምራ ታውቃለች፡፡ ጤናማ አዕምሮ ያለው ሰው መቼም ውሻው ሌላ ሰው በድጋሚ እንዲነክስ አይፈቅድም፡፡ በጣምም ይጠነቀቃል፡፡ይህች ጐረቤቴ ጃፓን ብትሆን ኖሮ ውሻው የፈለገውን ያህል ጤናማ ቢሆንም በፖሊስ ትያዝ ነበር - ውሻ ባለማሰሯ ብቻ፡፡ ውሻ አለማስከተብ ደግሞ ሌላ ቅጣት አለው፡፡ በጃፓን የውሻ ባለቤቶች ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ኃላፊነት ስለሚሰማቸው በመንገድ ላይ በውሻ የተነሳ አደጋ የገጠማቸው አይቼ አላውቅም፡፡ ስለዚህም ራቢስ ጃፓን ውስጥ ታሪክ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ በራቢስ የሚሞቱ ሰዎች የሉም፡፡ በኢትዮጵያ ግን ከዕውቀት ማነስም ይሁን ከቸልተኝነት አንዳንዴም እንደ ጐረቤቴ በራስ ወዳድነት ብዙ ሰዎች በመንገድ ላይ ውሾች ይነከሳሉ፤ ለበሽታም ይጋለጣሉ - ያውም ለሞት በሚዳርግ፡፡ ምስኪኖች ውሾች ላይም ድንጋይ ይወረወራል፡፡ የዛሬ አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያ የጤናና የምግብ ምርምር ተቋም በአዲስ አበባ ..የእብድ ውሻ.. በሽታ (ራቢስ) እየጨመረ መምጣቱን አስታውቆ ነበር፡፡ ተቋሙ እንደሚለው አብዛኛውን ጊዜ ለበሽታው የሚጋለጡት ህፃናት ሲሆኑ ህብረተሰቡ ውሾቹን እንዲያስከትብና ቤቱ እንዲያስር ማስተማር አስፈላጊ እንደሆነ ገልዋል - የተቋሙ ኃላፊዎች፡፡ በዚህም መሠረት የጐረቤቴን ጉዳይ ለፖሊሰ ለመጠቆም ወሰንኩ፡፡ ውድ አንባቢያን- ለፖሊስ ማመልከቴን ስነግራችሁ ..አላበዛሽውም እንዴ. . . ውሻ ነከሰኝ ብለሽ ለፖሊሲ. . ... ካላችሁኝ የራቢስን አደገኛነት በተመለከተ ብዙ ግንዛቤ አልጨበጣችሁም ማለት ነው፡፡ ወዳጆቼ ነገርዬው እኮ አደገኛ nW
ደግነቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለጥቆማዬ ፈጣን ምላሽ ሰጥቶኛል፡፡ ባለቤቷ ውሻዋን የራቢስ ክትባት ማስከተቧን የሚገልጽ ማስረጃ እንዳታቀርብ፣ ውሻዎቿንም እንድታስር ነግሯታል፡፡ እስካሁን የተለወጠ ነገር ግን የለም፡፡ ፖሊስ ከነገራት ከአንድ ሳምንት በኋላም ጐረቤቴ ማስረጃውን አላቀረበችም፤ ውሾቿንም አላሰረችም፡፡ ስለዚህ እንደገና ወደ ፖሊስ መሄድና ተጨማሪ እርምጃ እንዲወሰድባት ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ ለራሴና ለህብረተሰቡ ስል መታገሌን አላቆምም፡፡
በየትኛውም ጐዳና ውሾች ሲያጋጥማችሁ ድንጋይ አትወርውሩባቸው፡፡ ውሾች ስታዩም መፍራት የለባችሁም፡፡ ይልቁንም የውሻዎቹን ባለቤት ስለአደጋውና ኃላፊነት እንዲሰማቸውም አስተምሯቸው፤ ምከሯቸው፡፡
ከውሾች አደጋ ለመከላከል የሚጠቅሙ ነጥቦች
- ውሾችን በእጃችሁ አትንኳቸው (ሌሎችም እንስሳት ቢሆኑ) የትኛውንም ያህል ጤናማ ቢመስሉና ቢያምሩም በራቢስ የተያዙ ሊሆኑ ይችላሉ
- ስለራቢስ በቂ ዕውቀት ይኑራችሁ፡፡ ከሃኪማችሁ፣ ከእንስሳት ሃኪሞች ወይም ከኢንተርኔት ብዙ መረጃዎች ታገኛላችሁ፡፡ ለልጆቻችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ስለ ራቢስ አስተምሯቸው፡፡
ለውሻ ባለቤቶች
- ውሻችሁን አስከትቡ፡፡ ውሻችሁ ከግቢ የማይወጣ ቢሆንም ወደ ግቢያችሁ ከሚገቡ ድመቶች ወይም ሌሎች እንስሳት ራቢስ ሊይዘው ይችላል፡፡ በአሜሪካ በሌሊት ወፎች ራቢስ ውሾችና ሰዎች ሞተዋል፡፡
- ውሻችሁ ከግቢ በሚወጣ ጊዜ በሰንለት እሰሩት፡፡ ውሻው የተከተበ ቢሆንም ጐዳና ላይ ያለ ሰንሰለት አትልቀቁት፡፡ ውሻው ሰው ሊነክስ ይችላልና፡፡ (ባለቤት የሌላቸው ውሾች በከተማዋ አስተዳደር ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል፡፡)

 

Read 6226 times Last modified on Thursday, 15 September 2011 08:08