Saturday, 03 September 2011 11:52

ከግል ት/ቤቶች የክፍያ እየናረ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)
  • በዓመት 380ሺ ብር የሚከፈልባቸው ት/ቤቶች አሉ
  • ዘንድሮ ሁሉም ት/ቤቶች ከ10% እስከ 105% የክፍያ ጭማሪ  አድርገዋል
  • ትዮጵያውያን ተማሪዎችን የማይቀበሉ ት/ቤቶችም አሉ
  • ወላጆች ልጆቻቸውን ከግል ት/ቤቶች እያስወጡ ነው

በአዲስአበባከተማውስጥባሉየግል     ትምህርትቤቶችዘንድሮከወትሮየተለየጭማሪተደርጓል፡፡አብዛኛዎቹየግልና     የኮሚዩኒቲ  የሚደርስ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ bኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የውጭ አገር ዜጐች ከኢትዮጵያውያኑ ዓመታዊ የትምህርት ቤት ክፍያ በአምስት እጥፍ የበለጠ ይከፍላሉ፡፡ አንዳንድ ኢንተርናሽናል ት/ቤቶች ኢትዮጵያዊ ተማሪዎችን አንቀበልም ማለት ጀምረዋል፡፡

በአገሪቱ ካሉ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ክፍያ በማስከፈል የመጀመሪያ የሆነው ICS ኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ት/ቤት፤ ዘንድሮ ለጀማሪ ተማሪዎች (ለነርሰሪ) በዓመት 118ሺ ብር ወይም 6900 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን ክፍያው በትምህርት ደረጃው እያደገ ይሄዳል፡፡ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚከፈለው በዓመት 380ሺህ ብር ገደማ ወይም 22310 ዶላር ያስከፍላል፡፡ ትምህርት ቤቱ ለመጪው የትምህርት ዘመን የ10% ጭማሪም አድርጓል፡፡
ሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ለጀማሪ ወይንም ለነርሰሪ ተማሪዎቹ፣ ለኢትዮጵያውያን በዓመት 18420 ሲሆን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዓመታዊ ክፍያው በዓመት 42669 ደርሷል፡፡ ት/ቤቱ ለውጪ አገር ዜጐች የኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ዓመታዊ የክፍያ መጠን በ5 እጥፍ የሚያስከፍል ሲሆን፣ ለጀማሪ የውጭ ዜጋ ተማሪዎች በዓመት 92445፣ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በዓመት 205122 ብር ያስከፍላል፡፡ ት/ቤቱ በዘንድሮው ዓመት የ15% ጭማሪ ማድረጉም ታውቋል፡፡ ይኸው ትምህርት ቤት ለኢትዮጵያዊ ተማሪዎች የመመዝገቢያ 24344 ብር ሲያስከፍል ለውጭ አገር ዜጐች ደግሞ ብር 48144 ብር የመመዝገቢያ ያስከፍላል፡፡ የግሪክ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት በበኩሉ፤ ለመጪው የትምህርት  ዘመን የ40% የክፍያ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን ለነርሰሪ/ለጀማሪ ተማሪዎቹ 16470፣ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ 41280 ብር ያስከፍላል፡፡ የመመዝገቢያ ክፍያውም 2500 ብር ደርሷል፡፡
እነዚህ ት/ቤቶች በአብዛኛው የኑሮ ደረጃቸው ከፍተኛ ለሆነና የውጭ አገር ዜጎች ልጆች ለሆኑ ተማሪዎች የሚያገለግሉ ሲሆን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልጆቹን በሚያስተምርባቸው አነስተኛ የግል ትምህርት ቤቶችም የክፍያ መጠኑ ለመጪው የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ተዘዋውረን በተመለከትናቸዉ አልፋ፣ አሲና፣ ባሸዋም፣ ጂቫ፣ ኦሜጐኒያ፣ ራዲካል በተባሉ የግል ትምህርት ቤቶች ከ10% እስከ 105% የሚደርስ ጭማሪ ለመጪው የትምህርት ዘመን አድርገዋል፡፡ በአብዛኛዎቹ ት/ቤቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆችም በክፍያ መጠኑ ጭማሪ ሲማረሩና ክፍያው ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መምጣቱን ሲናገሩ ተመልክተናል፡፡
ሁለት ልጆቻቸውን ለአመታት ባስተማሩበት ት/ቤት እንዲቀጥሉ ማድረግ ባለመቻላቸው ከት/ቤቱ መልቀቂያ ሲያወጡ በአልፋ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ያገኘናቸው አንዲት ወላጅ፤ ሁለቱ ልጆቻቸው ጥሩ መሰረት ይዘው እንዲያድጉና ወደፊት የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ እየከፈሉ ቢቆዩም ለመጪው የትምህርት ዘመን የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ ለመቋቋም እንደማይችሉ በማመናቸው፣ ልጆቹን ከት/ቤቱ ለማስወጣት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡ የሰባተኛና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለሆኑ ልጆቻቸው በየወሩ ይከፍሉት በነበረው የሁለት መቶ ሃያ አምስት ብር ወርሃዊ ክፍያ ላይ ከእጥፍ በላይ የሆነ ጭማሪ ተደርጐ፣ 500 ብር በመድረሱ ጭማሪውን ሊቋቋሙት አልቻሉም፡፡ ያላቸው ብቸኛ አማራጭም ልጆቹን ከት/ቤት በማስወጣት፣ በዋጋ ክፍያቸው ዝቅተኛ ወደሆኑ ት/ቤቶች ማስገባት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ልጆቹ ጥሩ መሰረት የያዙላቸው በመሆኑ ከዚህ በኋላ በመንግስት ት/ቤቶች እንኳን ቢማሩ የተሻሉ ተማሪዎች ሊሆኑላቸው እንደሚችሉም ይናገራሉ፡፡
ለመጪው የትምህርት ዘመን በከተማይቱ ባሉ ሁሉም የግል ት/ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ በተደረገው የዋጋ ጭማሪ ላይ ት/ቤቶቹ የሚሰጧቸው ምክንያቶች የተሻለ አስተማሪዎችን ከገበያ ውስጥ ለመሳብ ከፍተኛ ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅባቸውና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለመተግበር የሚያስፈልጉ የመማሪያ መፃህፍትና ሌሎች ቁሳቁሶች ከፍተኛ ጭማሪ ማስከተላቸውን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ት/ቤቶቹ ከሌሎች ት/ቤቶች ጋር ተወዳድሮ ብልጫ ለማሳየትና በርካታ ተማሪዎችን ለመቀበል እንዲችሉ የተሻሉ ፋሲሊቲዎችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ለዚህም ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ነው፡፡የመጪው የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ አንዳንድ የህዝብ ት/ቤቶችንም መንካቱ አልቀረም፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ፣ በጨርቆስ ክፍለ ከተማ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ተዘዋውረን ያየናቸው አንዳንድ የህዝብ ት/ቤቶች በክፍያቸው ላይ ከ5-12% ጭማሪ አድርገዋል””yGLÂ የኮሚዩኒቲ ት/ቤቶቹም ሆኑ የህዝብ ት/ቤቶቹ የዋጋ ጭማሪ ከማድረጋቸው ጐን ለጐን ለመጪው የትምህርት ዘመን ሊሰጡ በታቀዱት ትምህርቶች ጥራትና ደረጃ ላይ ምን መሻሻልና ለውጦችን አድርገዋል የሚለው የብዙሃኑ ጥያቄ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ትምህርት ቤቶችን የትምህርት አሰጣጥ ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አዲስ አሰራር በመጪው የትምህርት ዘመን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመውናል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ብንሄድም አልተሳካልንም፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ በመጪው ዓመት መግቢያ ላይ በቂ መረጃ ሊሰጠን እንደሚችል ገልፆልናል፡፡ ሆኖም ይህ ከዓመት ዓመት እየጨመረ ሄዶ ጣራ የነካው የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ መጠን መድረሻው የት ይሆን?

 

Read 3126 times Last modified on Tuesday, 06 September 2011 14:04