Saturday, 27 August 2011 13:59

ሉሲ ከባናያና - ክፍል 1

Written by  ሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ዛሬ የሉሲ ልጆች የለንደን ኦሎምፒክ ጉዟቸውን በ90 ደቂቃ ለማሳጠር ከባናያናዎች ጋር ከሜዳቸው W ይፋለማሉ፡፡ በስዌቶ ግዛት በሚገኘው በኦርናልዶ ስታዲም የሚደረገው ወሳኝ ፍልሚያው ሲሆን ምናልባትም በሱፐር ስፖርት ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኮሚዩኒክሸን ክፍል ከስፍራው በላከልን መግለጫ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ  ቡድን ረቡዕ ታምቦ ኢንተርናሸናል ኤርፖርት ሲደርስ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ  ደማቅ  አቀባበል ተደርጎለታል፡፡25 አባላትን የያዘው ልዑካን ቡድኑ ጆሀንሰበርግ ኢስት ጌት በሚገኘው ጋርደን ኮርት ሆቴል ማረፉ ያመለከተው መግለጫ የዚያኑ ቀን ማምሻውን በጆሞ ኮስሞስ እግር ኳስ አካዳሚ ልምምድ መስራቱንና ከትናንት በስቲያ በተደረገለት ግብዣ በሶከር ሲቲ ስታዲየም ልምምድና ጉብኝት ማድረጉን ገልጿል፡፡

የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ 40ሺ ተመልካች በሚይዘው ኦርላንዶ ስታድዬም  ባናያናዎች ከሉሲ ጋር ለሚያደርጉት ፍልሚያ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ቀስቅሷል፡፡ ፌዴሬሽኑ በመግለጫው በደቡብ አፍሪካ ወሩ የሴቶች መታሰቢያ መሆኑን በማመልከት በተለይ ሴቶች ስታድዬም እንዲገቡ ጥሪ በማቅረብ 30ሺ ነፃ መግቢያ ትኬት xs‰aL””
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋናና ዲሞክራቲክ ኮንጎን ጥሎ በማለፉ ለደቡብ አፍሪካ አቻው ከባድ ፈተና ሊሆን እንደሚችል  ሲዘገብ ሰንብቷል፡፡ ደቡብ አፍሪካ አራት ብሔራዊ የሴቶች ቡድን ያዘጋጀች ሲሆን ሁለቱን ምርጥ በሞዛምቢክ ለሚካሄደው የኦል አፍሪካን ጌምስ እንዲሁም የተቀሩትን ደግሞ ከኢትጵያ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ለማሰለፍ ነው፡፡ በርካታ ጨዋታ እያለብን ኢትዮጵያ ፕሮግራሙን አላራዝምም አለችን በማለት በየሚዲያው ላይ ምክንያት መደርደራቸውና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚደርጉት ጥረት ስኬታማ አልሆነም ያለው የፌዴሬሸ.ኑ ኮሚዩኒክሸ.ን ክፍል የላከልን ዘገባ ጨዋታውን የቶጎ ዜግነት ያላቸው ዳኞች እንደሚመሩትና የጋና ዜጋ በኮሚሽነርነት መመደባቸውን አመልክቷል፡፡
የደቡብ አፍሪካው  አሰልጣኝ ጆሴፍ ማክሆሃ  ኢትዮጵያን ለማሸነፍ ብቁ አቋም ይዘናል ብለው ቢናገሩም የኦሎምፒክ ማጣርያውና የኦልአፍሪካን ጌምስ ተሳትፎ የፈጠረው የውድድር መደራረብ ጫና ውስጥ እንደከተታቸው አልሸሸጉም፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን እኛን እንደሚያውቀው እኛም እናውቃቸዋለን ያሉት አሰልጣኙ፤ ወደ ለንደን ኦሎምፒክ የማለፍ እድሉን በ180 ደቂቃዎች እውን የምናደርገው በሜዳችን ከፍተኛውን ድል ካስመዘገብን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ የእግር ኳስ ፌደሬሽን በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው የመልስ ጨዋታ በኦልአፍሪካን ጌምስ ከጋና ጋር ከሚፋለሙበት የጨዋታ ፕሮግራም ጋር በመገናኘቱ አሳስቦት ቆይቷል፡፡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባቀረበው ማመልከቻም የፕሮግራም ሽግሽግ እንዲደረግለት ጠይቆ ነበር፡፡
አሰልጣኝ ጆሴፍ ማክሆሃ ባናያናን ከያዙ ወዲህ 13 ጨዋታዎችን አድርገው 11 ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ጨዋታ በፊት ከሞዛምቢክ ጋር ያደረጉትን የአቋም መፈተሻ ግጥሚያ 5ለ0 እንዳሸነፉ ተዘግቧል፡፡

 

Read 3037 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 14:02