ይህ በእንዲህ እንዳለ በጠንቋይ፤ የኮሚክ መሃፍት ጀግኖች እና ክፉ ተናጋሪ ሴት ገፀ-ባህርያትን የሚተርኩ የሆሊውድ ፊልሞች የክረምቱን ገበያ በማሟሟቅ የገቢ ክብረወሠን ሊሰበር እንደሆነ ሎስአንጀለስ ታይምስ አመለከተ፡፡ በሰሜን አሜሪካ የትኬት ሽያጭ በ5 ፐርሰንት፤ የተመልካች ብዛት በ2.8 ፐርሰንት እድገት ያሳየ ሲሆን አጠቃላይ ገቢም 3.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልል፡፡ የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ፊልም ፤ ትራንስፎርመርስና፤ 4ኛው የፓይሬትስ ኦፍ ካረቢያን ፊልም በዓለም ዙርያ ገቢያቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተመዘገበላቸው የዘንድሮ ትርፋማ ፊልሞች ናቸው፡፡