Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 August 2011 13:33

.ራይዝ ኦፍ ዘ ፕላኔት ኤፕስ.. እየመራ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለዕይታ ከበቃ ሁለት ሳምንት የሆነው የትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ አዲስ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ..ራይዝ ኦፍ ዘ ፕላኔት ኤፕስ.. በሳምንታዊ ገቢ የቦክስ ኦፊስን የገበያ ሰንጠረዥ እየመራ ነው፡፡ በ93 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሠራው ፊልም ባለፉት 15 ቀናት  በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ገቢ ከ180 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፡፡ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 3961 ሲኒማዎች በመታየት ላይ ያለው ይኸው ፊልም ላይ ጀምስ ፍራንኮ እና ፍሪዳ ፒኒቶ ይተውናሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጠንቋይ፤ የኮሚክ መሃፍት ጀግኖች እና ክፉ ተናጋሪ ሴት ገፀ-ባህርያትን የሚተርኩ የሆሊውድ ፊልሞች የክረምቱን ገበያ በማሟሟቅ የገቢ ክብረወሠን ሊሰበር እንደሆነ ሎስአንጀለስ ታይምስ አመለከተ፡፡ በሰሜን አሜሪካ የትኬት ሽያጭ በ5 ፐርሰንት፤ የተመልካች ብዛት በ2.8 ፐርሰንት እድገት ያሳየ ሲሆን አጠቃላይ ገቢም 3.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልል፡፡ የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ፊልም ፤ ትራንስፎርመርስና፤ 4ኛው የፓይሬትስ ኦፍ ካረቢያን ፊልም በዓለም ዙርያ ገቢያቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተመዘገበላቸው የዘንድሮ ትርፋማ ፊልሞች ናቸው፡፡

 

Read 3851 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:35