Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 August 2011 12:49

የጋዳፊ መጨረሻ አላማረም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጋዳፊ አሁንም እየዛቱ ነው - አይጦችንና ከሃዲዎችን እንግደላቸው በማለት
አማፂዎቹ በቦርሳ ውስጥ የምትገባና 2 ኪሎ የማትመዝን ሄሊኮፕተር ተጠቅመዋል
ጋዳፊ ከቤተመንግስት ስር 4 ሚ. ሰዎችን አመት ሙሉ የሚቀልብ ምግብ አከማችተዋል
ተማርከዋል የተባሉት የጋዳፊ ልጆች እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም
ሲአይኤ እና የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት በየፊናቸው ሊቢያ ውስጥ ተወጥረዋልየጋዳፊ ቤተመንግስትና መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የወርቅ ሽጉጥና  ወርቅ ቅብ ጋሪ በመሳሰሉአስገራሚ ነገሮች የተሞሉ ቢሆኑም፤     ከህንፃዎቹ በታች ምድር ስር የተገኙት ዘመናዊ ቤቶችና መጋዘኖች ግን ብዛታቸውና ውስብስብነታቸው ከተጠበቀው በላይ አስደናቂ ሆኗል፡፡

ዋሺንግተን ፖስት እንደገለፀው፤ ከግዙፉ የጋዳፊ ቤተሰብ መኖሪያ ህንፃ ስር ወደ ታች ምድር ውስጥ የተገነባው ህንፃ በጣም ሰፊ ነው፤ ይህን የሚያስጠረጥር ምልክት ግን የለም፡፡ ወደ ምድር ስር የሚወስድ መግቢያ የትም አይታይም፡፡ አሻራ የሚመረምር መሳሪያ የተገጠመለት የግቢ በር አለ፡፡ ያንን አልፈው፤ በአትክልት ስፍራው አቋርጠው፤ በጥንቃቄ በተከረከሙት ተክሎች ጀርባ፤ ድብቅ መግቢያ ተዘጋጅቷል - ወደ ምድር ስር የሚያዘልቅ፡፡ በሚስጥራዊው መግቢያ፤ ወደ ታች የሚያወርዱ ደረጃዎችን ያገኛሉ - የሁለት ፎቅ ያህል ርዝመት ወደ ታች እንደወረዱ፤ እንደገና ጠንካራ በር ያገኛሉ - በጣም ወፍራም የብረት በር፡፡ የብረቱ ውፍረት አንድ ክንድ ያክላል፡፡ ከዚህ በር ወዲያ ነው፤ ተአምረኛ የመሬት ስር ዘመናዊ ቤቶችና መጋዘኖች የሚገኙት - የጄምስ ቦንድ ፊልም የምመለከት መሰለኝ ብሏል የዋሺንግተን ፖስት ጋዜጠኛ፡፡
የብዙዎቹ ቀልብ - ባዙቃ
ከሽጉጥና ከክላሺንኮቭ እስከ መትረየስና ባለማነጣጠሪያ ጠመንጃዎች፤ ከጥይት እስከ ቦምብ ክምር፤ ከፈንጂ እስከ ሮኬት፤ ... የምድር ስር መጋዘኖች ውስጥ ያልተከማቸ ነገር የለም፡፡ አራት ሚሊዮን ሰዎችን አመት ሙሉ የሚቀልብ የእህልና የምግብ ክምችት፤ የአገሪቱን የመድሃኒት ፍጆታ ለአንድ አመት የሚሸፍን የመድሃኒት ክምር... በምድር ስር መጋዘኖች ውስጥ እንደተገኘ አንድ የአማፅያኑ ኮማንደር ተናግሯል፡፡
አማፂያኑና የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ከረቡዕ ጀምረው ውስብስቦቹን የምድር ስር ህንፃዎች እያሰሱ ቢሆኑም፤ ገና ሙሉ ለሙሉ አላዳረሱትም፡፡ በርካታ ነዋሪዎች፤ ጦርነቱ ጋብ ከማለቱ በፊትም ጭምር የምድር ስር መጋዘኖቹ ውስጥ እየገቡ፤ ያገኙትንና እጃቸው የነካውን ነገር፣ ቀልባቸው ያረፈበትን እቃ እያነሱ ሲወስዱ ሰንብተዋል፡፡ በእርግጥ የጋዳፊ የወርቅ ሽጉጥና የመሳሰሉ ልዩ እቃዎች በአማፂዎቹ ተይዘዋል፡፡ ሌላው ሌላው ግን...  ፍላትስክሪን ቴሌቪዢኖችን ተሸክመው የሚሮጡ፤ የወርቅ ጌጣጌጦችን ለማግኘት የሚበረብሩ፤ ውድ የመሰላቸውን እቃ ለመውሰድ የሚሻሙ ጥቂት አይደሉም፡፡
የብዙዎቹ ቀልብ ያረፈው ግን፤ የጦር መሳሪያ ላይ ነው ይላል የስካይኒውስ ጋዜጠኛ፡፡ ግን ሽሚያ አያስፈልግም - የጦር መሳሪያው ክምር ለሁሉም ይበቃል፡፡ የማማረጥ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ወጣት ሊቢያዊ፤ ባለመነጣጠሪያ ትልቅ መሳሪያ አንስቶ ትከሻው ላይ ለማሳረፍ ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ መሳሪያውን በአድናቆት የሚያሻሸው፤ ተራ መሳሪያ እንዳልሆነና የአነጣጥሮ ተኳሽ ኮማንዶዎች መሳሪያ እንደሆነ ስላወቀ አይደለም፡፡
መሳሪያው ለአይን ያምራል - ልሙጥ ወርቃማ ቀለሙ፡፡ ከትንሽ ሙከራና ትግል በኋላ ነው፤ እንዴት መተኮስ እንደሚችል ያወቀበት፡፡ መሳሪያውን ወደ ላይ ደግኖ አከታትሎ ተኮሰ፡፡ ሌላኛው ወጣት ግን፤ ወደ ላይ ለመተኮስ አልሞከረም፡፡ ከምድር ስር መጋዘን ውስጥ ያገኘው መሳሪያ ባዙቃ ነው፡፡ ባዙቃውን ትከሻው ላይ አሳርፎ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡ ባዙቃውን ምን ላይ ይሞክረው? ከጎን ያለው ህንፃ የወጣቱን ትኩረት ስቧል፡፡ የህንፃው አናት በመስተዋት የተሰራ ጉልላት ነው፡፡ ባዙቃውን አነጣጥሮ ተኮሰ፡፡ ህንፃው ተንቀጠቀጠ፡፡ የወስተዋት ጉልላቱ ብትንትኑ ወጥቷል፡፡
ከቤት ቤት መልቀም፤ ጓዳ ጎድጓዳውንም
ከትሪፖሊ ቤተመንግስታቸው የተባረሩት ሙአመር ጋዳፊ እንደወትሮው የዛቻ ዲስኩርና የጦርነት ትእዛዝ ከማስተጋባት ወደኋላ አላሉም፡፡ ሲቆጣጠሩት የነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያ፤ በአማፂዎች እጅ ገብቷል፡፡ የጋዳፊን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩት የመንግስት ጋዜጠኞችም ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡ በቲቪ ጋዳፊን በማወደስ ፕሮፓጋንዳ ከማራገብና መፈክሮችን ከመለፈፍ በተጨማሪ፤ ክላሺንኮቭ እያወዛወዙ እስከመፎከር የደረሱ አንዳንድ የመንግስት ጋዜጠኞችም ነበሩ፡፡ ዛሬ የሉም፡፡ ጋዳፊ ለዘላለም ይኑር፤ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ከጋዳፊ ጋር ነኝ እያለ ከነክላሽንኮቩ በቲቪ ሲፎክር የነበረው አንጋፋ ጋዜጠኛ ሃላ ሚስራቲ ግን፤ በአማፂዎቹ ተይዞ ወደ እስር ቤት ሲወሰድ ታይቷል - በዚያው ቲቪ፡፡
ቢሆንም ግን፤ ባዶ እጃቸውን የቀሩት ጋዳፊ አዲስ የጦርነት ጥሪ ማስተላለፋቸው አልቀረም - በሶሪያ ቴሌቪዥን፡፡ አምባገነን ከዘመዱ፣ አህያ ከአመዱ ይባል የለ! አመፅ የተነሳባቸው የሶሪያው አሳድ፤ በአመፅ ከስልጣን ለተባረሩት ጋዳፊ፤ የእርዳታ እጃቸውን ቢዘረጉ አይገርምም፡፡ ጋዳፊ በዚሁ የሶሪያ ቲቪ ባተስተላለፉት ዲስኩር፤ ሊቢያውያን እንደገና ለጦርነት እንዲነሱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ትሪፖሊን ለአማፅያኑ አስረክባችሁ መቀመጥ የለባችሁም ሲሉ የተናገሩት ጋዳፊ፤ እነዚህ አይጦችን ውጓቸው፤ እነዚህ ከሃዲዎችን ግደሏቸው በማለት አዝዘዋል፡፡ከወራት በፊት፤ ገና ከቤተመንግስታቸው ሳይባረሩ በፊትም፤ አማፂዎቹን አንድ በአንድ እንደሚጨርሷቸው ጋዳፊ ዝተው ነበር - ከቤት ቤት እያሰስን፤ ጓዳ ጎድጓዳውን እየበረበርን አይጦቹን እናጠፋቸዋለን በማለት፡፡ ይህንኑን ነው አሁንም የደሰኮሩት፡፡ ለሊቢያዊያን ግን መቀለጃ ሆነዋል፡፡ ጋዳፊ ከቤተመንግስታቸው በተባረሩበት ሰአት፤ ገና ጥይቶች በየአቅጣጫው እያፏጩ፤ ግራ ቀኙ በፍንዳታዎች እየተናወጠ በነበረበት ሰአት፤ አማፂዎቹ ብቻ ሳይሆኑ፤ የአካባቢው ነዋሪዎችም ጭምር ቤተመንግስቱን መበርበር ጀምረዋል - ከቤት ቤት፤ ጓዳ ጎድጓዳውንም ብለው እየዘመሩ፡፡
የተማረኩት የጋዳፊ ልጆች የት ገቡ?
የሳምንቱ መግቢያ ላይ አማፂዎቹ ወደ ትሪፖሊ ዘመቻቸውን እንደጀመሩ ነበር፤ ብዙም ሳይቆይ የጋዳፊ ልጆች ተማርከዋል የሚል ዘገባ የተሰራጨው - ከአማፂዎቹ በመጣ ወሬ መነሻነት፡፡ ቀናት ቢያልፉም፤ የተማረኩትን የጋዳፊ ልጆች አይቻለሁ የሚል ሰው አልተገኘም፡፡ የልጆቹ ድምፅም አልተሰማም፡፡ በአማፂዎች እጅ ውስጥ እንደገቡ ሲነገርላቸው ከነበሩት የጋዳፊ ልጆች መካከል አንዱ የሆነው ሰአዲ ግን፤ ሮብ እለት አለሁ አለሁ የሚል መልእክት አስተላልፏል፡፡
አገሬንና ትሪፖሊን ከደም ጎርፍ ማዳን እፈልጋለሁ በማለት ለሲኤንኤን ኢሜይል የላከው ሰአዲ፤ እርቅ እንዲወርድ ማድረግ እፈልጋለሁ ብሏል፡፡ ጋዳፊን ከአሜሪካ ጋር እንዲሁም የጋዳፊን ጦር ሲደበድብ ከከረመው ኔቶ ጋር ማደራደርና ሰላም ማውረድ እችላለሁ ብሏል ሰአዲ፡፡ ምናልባት፤ እሱና ቤተሰቦቹ  በምርኮ እንዴት እጅ መስጠት እንደሚችሉ መደራደር ካላሰበ በቀር፤ የሰአዲን የድርድር ጥሪ እንደቁምነገር ይቆጠራል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው፡፡ እንዲያውም፤ ከሰአዲ ኢሜይል የተገኘ አንድ ቁምነገር ቢኖር፤ በአማፂያኑ እጅ ውስጥ እንዳልገባና እንዳልተማረከ በግልፅ እንዲታወቅ ማድረጉ ነው ተብሏል፡፡ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ እንዳለው፤ ሰይፍ እና መሃመድ የተባሉት የጋዳፊ ልጆችም ገና አልተማረኩም - እንደተማረኩ በአማፂያኑ ተወርቶ የነበረ ቢሆንም፡፡ መች ይሄ ብቻ?
ያልተጨበጡ ወሬዎችን በመንዛት ጋዳፊን የሚፎካከር ባይኖርም፤ ከአማፂያኑ በኩል የተናፈሱ ያልተጨበጡ ወሬዎችም ጥቂት አይደሉም፡፡ እንደብዙዎቹ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ሁሉ፤ ሊቢያም ከባድ ኋላቀርነት ውስጥ እንደሆነች የሚያመላክት ክስተት ነው፡፡ ጋዳፊና ልጆቹ በትሪፖሊ የመኖሪያ አፓርታማዎች ውስጥ ተደብቀው ተከበዋል የሚለውን ዘገባ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ቀላል ዘገባ አይደለም፡፡ ለዚያውም በዜና አዘጋገብ ጥንቃቄው እንዲሁም በጋዜጠኝነት ብቃቱ ከፍተኛ ከበሬታ የተጎናፀፈው ሮይተርስ ነው፤ ዜናውን የዘገበው፡፡
በእርግጥም፤ አማፂያኑ ረቡእ እለት የጋዳፊን ቤተመንግስት ሙሉ ለሙሉ ቢቆጣጠሩም፤ ሃሙስ ድረስ የትሪፖሊ ውጊያ ጋብ አላለም ነበር፡፡ ብዙ ሳይርቅ ወደ ዋናው ኤርፖርት አቅጣጫ፤ እጅብ ብለው በሚታዩት የመኖሪያ አፓርትመንቶች አካባቢ ከባድ ውጊያ ተጧጥፏል፡፡ የጋዳፊን ቤተመንግስት ከተቆጣጠሩ በኋላ፤ እንዲህ አይነት ጠንካራ ውጊያ እንደሚገጥማቸው አልጠበቁም - አማፂዎቹ፡፡ ይበታተናሉ ተብለው የተጠበቁት የጋዳፊ ታጣቂዎች፤ አቡ ሳሊም በተሰኘው አካባቢ አስር ያህል የመኖሪያ አፓርትመንቶች ውስጥ መሽገዋል፤ ወጥረውም እየተዋጉ ነው፡፡ እንዴት ተስፋ ቆርጠው አልተበታተኑም? ምክንያት መኖር አለበት፡፡ አፓርትመንቶቹ ውስጥ ጋዳፊ ከነልጆቹ ተደብቋል ማለት ነው የሚል ያልተጨበጠ ሃሳብ ላይ የደረሱት አማፂዎች፤ ጋዳፊና ልጆቹን ለመያዝ የመጨረሻ ውጊያ እያካሄድን ነው፤ ስለከበብናቸው የትም አያመልጡም በማለት በወቅቱ ተናግረዋል፡፡ እንዳሰቡት አልሆነም፡፡ በውጊያ አፓርትመንቶቹN ከተቆጣጠሩ በኋላ እንደተረጋገጠውም፤ ጋዳፊም ሆኑ የጋዳፊ ልጆች በአካባቢው አልነበሩም፡፡
ወሬው በዚሁ ቢያበቃ መልካም ነበር፡፡ ግን ሌላ አዲስ ወሬ ተጨመረበት፡፡ እዚያው አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ሆቴልስ? የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡ በሆቴሉ አካባቢ በርካታ የጋዳፊ ታጣቂዎች ከባድ ጥበቃ እንደሚያካሂዱ ታይቷል፡፡ ምናልባት ጋዳፊና ልጆቹ ሆቴሉ ውስጥ ተደብቀው ቢሆንስ የሚል ጥርጣሬ የተፈጠረባቸው አማፂያን፤ እንደገና ወደ ተሳሳተ ሃሳብ ለማምራት ተጣደፉ፡፡ በሆቴሉ ውስጥኮ አንድም የጋዳፊ ባለስልጣን አልነበረም፡፡ እንዲያውም በርካታ የውጭ ጋዜጠኞች ናቸው በሆቴሉ ውስጥ በጋዳፊ ታጣቂዎች አማካኝነት ታግተው እንዲቀመጡ የተደረጉት - ጦርነቱን እንዳይዘግቡ፡፡ ጦርነቱ ውስጥ ሆነው፤ ጦርነቱን ማየትና መዘገብ ሳይችሉ የቆዩት የአለማቀፍ ሚዲያ ጋዜጠኞች ከእገታ የወጡት ሃሙስ ማታ ነው፡፡ በጋዳፊ ታጣቂዎች ወደ እስር ቤት ተወርውረው የነበሩ ጋዜጠኞችኮ፤ እስር ቤቱ ተሰብሮ ነፃ የወጡት ረቡእ እለት መሆኑ ሲታሰብ፤ ከመታገት ይልቅ መታሰር ይሻላል እንዴ ያሰኛል፡፡
ቤተመንግስትም ሆነ የምድርስር ህንፃዎች ውስጥ፤ ሆቴልም ሆነ የአቡ ሳሊም አፓርትመንቶች ውስጥ ያልተገኙትን ጋዳፊ ለመያዝ፤ አደኑ ቀጥሏል፡፡ ጋዳፊን ከነህይወታቸው ወይም አስከሬናቸውን ይዞ የሚመጣ ሰው እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ሽልማት እንደሚያገኝ በይፋ ቢታወጅም፤ አማፂዎቹ እና ኔቶ አደናቸውን ቸል አላሉም፡፡ በአፋጣኝ ጋዳፊን መያዝ ወይም መግደል፤ አገሪቱ ቶሎ እንድትረጋጋ ያግዛል ብለው ያስባሉ፡፡ ዴይሊ ቴሌግራፍ እንደዘገበው ከሆነ፤ የጋዳፊ አደን ላይ የኔቶ ድርሻ አከራካሪ ቢሆንም፤ የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችንና ከፍተኛ የስለላ ባለሙያዎችን በመጠቀም አሰሳውን ተያይዞታል፡፡
አማፂዎቹ ግን፤ ይህ ነው የሚባል የመረጃ ቴክኖሎጂና የሙያ አቅም የላቸውም፡፡ ከኔቶ በኩል የሚያገኙት መጠነኛ የሳተላይት መረጃና የምክር እገዛ በእጅጉ የሚጠቅማቸው ቢሆንም፤ በቂ ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡ ግን አርፈው አልተቀመጡም፡፡ ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበው ከሆነ፤ አማፂዎቹ የአቅማቸውን ያህል አዲስ የስለላና የመረጃ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሞክረዋል - ሚኒÿlþ÷PtR በመግዛት፡፡
ሚኒÿlþ÷PtR - ቦርሳ ውስጥ
የሄሊኮፕተሯ ክብደት ሁለት ኪሎ አይሞላም፡፡ አራት ተሽከርካሪ ክንፍ ያላት ይህችው የስለላ አውሮፕላን፤ ትንሽ በመሆኗ ተጣጥፋ ቦርሳ ውስጥ ልትያዝ ትችላለች ብሏል ኒውዮርክ ታይምስ፡፡ የሊቢያ አማፂዎች የስለላ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው ቢያውቁም፤ ትልቅ የስለላ አውሮፕላን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አልነበራቸው፡፡ በኢንተርኔት መፍትሄ ሲያፈላልጉ ነው፤ ካናዳ ውስጥ በአንድ ኩባንያ የተሰራች የስለላ ሚኒÿlþ÷PtR በ120ሺ ዶላር መግዛት እንደሚችሉ የተገነዘቡት፡፡
ቀን ከማታ በርቀት መቆጣጠሪያ እየበረረች ጥራት ያለው ምስል መቅረፅ ትችላለች፡፡ በተለይም የትሪፖሊ አካባቢዎችን ለመሰለልና ለመከታተል አማፂዎቹ ሚኒ ሄሊኮፕተሯን እንደተጠቀሙ ኒውዮርክ ታይምስ ይገልፃል፡፡ ትሪፖሊን ለማረጋጋት ወይም የጋዳፊ የትየጋዳፊ ቤተመንግስትና መኖሪያ ቤቶች ውስጥ
የወርቅ ሽጉጥና  ወርቅ ቅብ ጋሪ በመሳሰሉ
አስገራሚ ነገሮች የተሞሉ ቢሆኑም፤
ከህንፃዎቹ በታች ምድር ስር የተገኙት
ዘመናዊ ቤቶችና መጋዘኖች ግን ብዛታቸውና ውስብስብነታቸው ከተጠበቀው በላይ አስደናቂ ሆኗል፡፡

ቀን ከማታ በርቀት መቆጣጠሪያ እየበረረች ጥራት ያለው ምስል መቅረፅ ትችላለች፡፡ በተለይም የትሪፖሊ አካባቢዎችን ለመሰለልና ለመከታተል አማፂዎቹ ሚኒ ሄሊኮፕተሯን እንደተጠቀሙ ኒውዮርክ ታይምስ ይገልፃል፡፡ ትሪፖሊን ለማረጋጋት ወይም የጋዳፊ የትውልድ ከተማ የሆነችውን ሲርትን ለመቆጣጠር አልያም ጋዳፊን አስሶ ለመያዝ፤ አማፂዎቹ 1.4 ኪሎ የማትሞላዋን ሚኒÿlþ÷PtR መጠቀማቸው አይቀርም፡፡
በእርግጥ አማፂዎቹ ፤ ጋዳፊን ከቤተመንግስት ካባረሩ በኋላ፤ የጋዳፊ ታጣቂዎች ለምን ተስፋ እንዳልቆረጡና ለምን ወጥረው እንደሚዋጉ ለማወቅ ከፈለጉ ያለ ሄሊኮፕተርም ማወቅ ይችላሉ፡፡ የጋዳፊ መንግስትና ታጣቂዎች፤ በሊቢያዊያን ላይ ጅምላ ግድያ ሲፈፅሙ እንደነበር የሚያረጋግጡ መረጃዎች መገኘታቸውን የዘገበው ዴይሊቴሌግራፍ፤ ከጋዳፊ ግፍ ጋር የሚመጣጠን ባይሆንም አማፂዎችም ምርኮኞችን የመግደል ወይም የማሰቃየት ጥፋት እንደሚፈፅሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብሏል፡፡ እጃቸው እንደታሰረ በጥይት የተገደሉ ሁለት የጋዳፊ ታጣቂዎች በቤተመንግስት አቅራቢያ መገኘታቸውም፤ ይህን መረጃ ያጠናክራል፡፡
የጋዳፊ መንግስት በሊቢያውያን ላይ የሚፈፅመውን ግድያና ግፍ ሲቃወሙ የነበሩት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የአማፂዎቹ ቡድንም ህገወጥ ግድያና ግፍ ከመፈፀም እንዲታቀብ አሳስበዋል፡፡ በምርኮ የተያዙ የጋዳፊ ታጣቂዎችና የጋዳፊ ቤተሰቦች ወደ ህጋዊ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚገባ ገልፀው፤ ከህግ ውጭ ግድያም ሆነ የስቃይ ድርጊት ሊፈፀምባቸው አይገባም ብለዋል - ሁለቱ የሰብአዊ መብት ተቋማት፡፡ ምርኮኞችን የሚያሰቃዩና የሚገድሉ ከሆነ፤ እስከ መጨረሻው መዋጋት ይሻለኛል ብለው የሚያስቡ የጋዳፊ ታጣቂዎች ቢያጋጥሙ አይገርምም፡፡ አማፂዎቹ አገሪቱን ለመቆጣጠርና ለማረጋጋት፤ ጋዳፊንም በፍጥነት ለመያዝ፣ በአጠቃላይ አላማቸውን ለማሳካት ይበልጥ የሚያግዛቸው ስልጡን የሆነ መንገድ ቢከተሉ ነው - የሰብአዊ መብት ተቋማት እንደሚሉት፡፡        
ሚሳየልን በሚሳየል
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ጭንቀት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ የጋዳፊ መንግስት በምድር ስር አሽጎ ያስቀመጣቸው መርዛማ ኬሚካሎች በአንዳች መንገድ አሸባሪዎች እጅ ውስጥ እንዳይገባ እርምጃ ወስደዋል የተባሉት የሲአይኤ ኤጀንቶች፤ ሌላ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ገጥሟቸዋል - የተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ጉዳይ፡፡
የጋዳፊ ታጣቂዎች አራት የስከድ ሚሳየሎች መተኮሳቸው፤ ለጊዜው የትሪፖሊና የሚዝራታ ነዋሪዎችን ቢያስበረግግም ያን ያህል አሳሳቢ አልሆነም፡፡ የተተኮሱት ሚሳይሎች ጉዳት አላደረሱም፡፡ አቅመቢስ ስለሆኑ አይደለም፡፡ በራሺያ የተሰሩት ሚሳየሎች ኢላማቸውን በትክክል የመምታት አቅም ባይኖራቸውም፤ ትሪፖሊና ሚዝራታ ወደመሳሰሉ ከተሞች ከተተኮሱ ከፍተኛ ጥፋት ማድረስ ይችላሉ፡፡ አራቱ ሚሳይሎች የተተኮሱትም ከተማ ላይ እንዲያርፉ ነበር፡፡ ደግነቱ አላረፉም፡፡ አየር ላይ እንዲከሽፉ ተደርገዋል - በአሜሪካ ክሩዝ ሚሳየል እየተመቱ፡፡
በእርግጥ የስከድ ሚሳየሎቹ የከሸፉት ምድር ለመድረስ ትንሽ ሲቀራቸው ነው፡፡ የፍንዳታው ሃይልም ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ ቢሆንም፤ አራት ስከድ ሚሳየሎች ተተኩሰው አራቱንም ማክሸፍ ስለተቻለ፤ የስከድ ሚሳኤል ጉዳይ ብዙም አያሳስብም ብሏል ዘ ጋርዲያን፡፡ በጣም አሳሳቢው ነገር... ከትከሻ ላይ የሚተኮሱና አውሮፕላኖችን ለመምታት የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ የጋዳፊ ሚሳየሎች አሸባሪዎች እጅ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ የሚለው ስጋት እንደሆነ አንድ የሲአይኤ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡ በጥቁር ገበያ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ዋጋ ዝቅ እያለ መምጣቱ የተዘገበ ሲሆን፤ ምናልባት የጋዳፊ ተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ለሽያጭ በመቅረባቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡
አገራዊ የሽግግር ምክርቤት በሚል ስያሜ ተሰባስበው ጊዜያዊ መንግስት ያቋቋሙት የሊቢያ አማፂ ቡድኖች፤ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ከቤንጋዚ ወደ ትሪፖሊ አዛውረናል ብለዋል፡፡ ትሪፖሊን ጨምሮ በርካታ የሊቢያ ከተሞች በጦርነት ቀውጢ ባይወጡም፤ የጊዜያዊው መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ግን፤ በጦርነት ማሸነፍ ብቻ በቂ እንዳልሆነ የሚያስቡ ይመስላሉ፡፡ ገንዘብ ፍለጋ ወደ ጣሊያን ያመሩት ጠ/ሚ፤ የተመድ፣ የአሜሪካ፣ የአውሮፓና አንዳንድ የአረብ መንግስታትን ሲያነጋግሩና ሲማፀኑ ሰንብተዋል፡፡ እርዳታው ቢቀር እንኳ፤ ሊቢያ የገንዘብ እጥረት የለባትም - በበርካታ አገራት ውስጥ የተቀመጠ 150 ቢ. ዶላር የሚገመት ሃብት እንዳላት ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን፤ ጋዳፊ በዚህ ሃብት እንዳይጠቀሙ ለመከልከል ሲባል፤ ያ ሁሉ ሃብት በአውሮፓና በአሜሪካ መንግስታት እንዲሁም በተመድ ውሳኔ ታግዶ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ሃብት ውስጥ ነው፤ ለጊዜው 1.5 ቢ. ዶላር ለጊዜያዊው መንግስት እንዲተላለፍ ትናንት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተወሰነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች ለወራት ደሞዝ አልተከፈላቸውም፡፡ የውሃና የኤሌክትሪክ፣ የመንገድና የስልክ አገልግሎቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆኑት የነዳጅ ተቋማትም እንዲሁ፤ ተዳክመዋል፡፡ በርካታ የአገሪቱን ችግሮች ለማቃለልና የተረጋጋ የዲሞክራሲ ሽግግር ለማስጀመር፤ አሁን 5 ቢ. ዶላር ያስፈልገናል ብለዋል - ጊዜያዊው የፋይናንስ ሚኒስትር አሊ ታርሁኒ፡፡ ተመሳሳይ የህዝብ አመ ያስተናገዱት የግብፁ ሁስኒ ሙባረክ የፍርድ ውሳኔያቸውን ለመስማት ፍ/ቤት እየተመላለሱ ነው የቱኒዝያው መሪ ደግሞ አገር ጥለው በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡የሊቢያው ጋዳፊ እጣ ፋንታ ባይታወቅም መጨረሻቸው እንዳላማረ ግን ከወዲሁ ግል ሆኗል- እንደአብዛኞቹ አምባገነን መሪዎች””ውልድ ከተማ የሆነችውን ሲርትን ለመቆጣጠር አልያም ጋዳፊን አስሶ ለመያዝ፤ አማፂዎቹ 1.4 ኪሎ የማትሞላዋን ሚኒÿlþ÷PtR መጠቀማቸው አይቀርም፡፡
በእርግጥ አማፂዎቹ ፤ ጋዳፊን ከቤተመንግስት ካባረሩ በኋላ፤ የጋዳፊ ታጣቂዎች ለምን ተስፋ እንዳልቆረጡና ለምን ወጥረው እንደሚዋጉ ለማወቅ ከፈለጉ ያለ ሄሊኮፕተርም ማወቅ ይችላሉ፡፡ የጋዳፊ መንግስትና ታጣቂዎች፤ በሊቢያዊያን ላይ ጅምላ ግድያ ሲፈፅሙ እንደነበር የሚያረጋግጡ መረጃዎች መገኘታቸውን የዘገበው ዴይሊቴሌግራፍ፤ ከጋዳፊ ግፍ ጋር የሚመጣጠን ባይሆንም አማፂዎችም ምርኮኞችን የመግደል ወይም የማሰቃየት ጥፋት እንደሚፈፅሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብሏል፡፡ እጃቸው እንደታሰረ በጥይት የተገደሉ ሁለት የጋዳፊ ታጣቂዎች በቤተመንግስት አቅራቢያ መገኘታቸውም፤ ይህን መረጃ ያጠናክራል፡፡
የጋዳፊ መንግስት በሊቢያውያን ላይ የሚፈፅመውን ግድያና ግፍ ሲቃወሙ የነበሩት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የአማፂዎቹ ቡድንም ህገወጥ ግድያና ግፍ ከመፈፀም እንዲታቀብ አሳስበዋል፡፡ በምርኮ የተያዙ የጋዳፊ ታጣቂዎችና የጋዳፊ ቤተሰቦች ወደ ህጋዊ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚገባ ገልፀው፤ ከህግ ውጭ ግድያም ሆነ የስቃይ ድርጊት ሊፈፀምባቸው አይገባም ብለዋል - ሁለቱ የሰብአዊ መብት ተቋማት፡፡ ምርኮኞችን የሚያሰቃዩና የሚገድሉ ከሆነ፤ እስከ መጨረሻው መዋጋት ይሻለኛል ብለው የሚያስቡ የጋዳፊ ታጣቂዎች ቢያጋጥሙ አይገርምም፡፡ አማፂዎቹ አገሪቱን ለመቆጣጠርና ለማረጋጋት፤ ጋዳፊንም በፍጥነት ለመያዝ፣ በአጠቃላይ አላማቸውን ለማሳካት ይበልጥ የሚያግዛቸው ስልጡን የሆነ መንገድ ቢከተሉ ነው - የሰብአዊ መብት ተቋማት እንደሚሉት፡፡        
ሚሳየልን በሚሳየል
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ጭንቀት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ የጋዳፊ መንግስት በምድር ስር አሽጎ ያስቀመጣቸው መርዛማ ኬሚካሎች በአንዳች መንገድ አሸባሪዎች እጅ ውስጥ እንዳይገባ እርምጃ ወስደዋል የተባሉት የሲአይኤ ኤጀንቶች፤ ሌላ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ገጥሟቸዋል - የተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ጉዳይ፡፡
የጋዳፊ ታጣቂዎች አራት የስከድ ሚሳየሎች መተኮሳቸው፤ ለጊዜው የትሪፖሊና የሚዝራታ ነዋሪዎችን ቢያስበረግግም ያን ያህል አሳሳቢ አልሆነም፡፡ የተተኮሱት ሚሳይሎች ጉዳት አላደረሱም፡፡ አቅመቢስ ስለሆኑ አይደለም፡፡ በራሺያ የተሰሩት ሚሳየሎች ኢላማቸውን በትክክል የመምታት አቅም ባይኖራቸውም፤ ትሪፖሊና ሚዝራታ ወደመሳሰሉ ከተሞች ከተተኮሱ ከፍተኛ ጥፋት ማድረስ ይችላሉ፡፡ አራቱ ሚሳይሎች የተተኮሱትም ከተማ ላይ እንዲያርፉ ነበር፡፡ ደግነቱ አላረፉም፡፡ አየር ላይ እንዲከሽፉ ተደርገዋል - በአሜሪካ ክሩዝ ሚሳየል እየተመቱ፡፡
በእርግጥ የስከድ ሚሳየሎቹ የከሸፉት ምድር ለመድረስ ትንሽ ሲቀራቸው ነው፡፡ የፍንዳታው ሃይልም ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ ቢሆንም፤ አራት ስከድ ሚሳየሎች ተተኩሰው አራቱንም ማክሸፍ ስለተቻለ፤ የስከድ ሚሳኤል ጉዳይ ብዙም አያሳስብም ብሏል ዘ ጋርዲያን፡፡ በጣም አሳሳቢው ነገር... ከትከሻ ላይ የሚተኮሱና አውሮፕላኖችን ለመምታት የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ የጋዳፊ ሚሳየሎች አሸባሪዎች እጅ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ የሚለው ስጋት እንደሆነ አንድ የሲአይኤ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡ በጥቁር ገበያ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ዋጋ ዝቅ እያለ መምጣቱ የተዘገበ ሲሆን፤ ምናልባት የጋዳፊ ተንቀሳቃሽ ሚሳየሎች ለሽያጭ በመቅረባቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡
አገራዊ የሽግግር ምክርቤት በሚል ስያሜ ተሰባስበው ጊዜያዊ መንግስት ያቋቋሙት የሊቢያ አማፂ ቡድኖች፤ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ከቤንጋዚ ወደ ትሪፖሊ አዛውረናል ብለዋል፡፡ ትሪፖሊን ጨምሮ በርካታ የሊቢያ ከተሞች በጦርነት ቀውጢ ባይወጡም፤ የጊዜያዊው መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ግን፤ በጦርነት ማሸነፍ ብቻ በቂ እንዳልሆነ የሚያስቡ ይመስላሉ፡፡ ገንዘብ ፍለጋ ወደ ጣሊያን ያመሩት ጠ/ሚ፤ የተመድ፣ የአሜሪካ፣ የአውሮፓና አንዳንድ የአረብ መንግስታትን ሲያነጋግሩና ሲማፀኑ ሰንብተዋል፡፡ እርዳታው ቢቀር እንኳ፤ ሊቢያ የገንዘብ እጥረት የለባትም - በበርካታ አገራት ውስጥ የተቀመጠ 150 ቢ. ዶላር የሚገመት ሃብት እንዳላት ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን፤ ጋዳፊ በዚህ ሃብት እንዳይጠቀሙ ለመከልከል ሲባል፤ ያ ሁሉ ሃብት በአውሮፓና በአሜሪካ መንግስታት እንዲሁም በተመድ ውሳኔ ታግዶ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ሃብት ውስጥ ነው፤ ለጊዜው 1.5 ቢ. ዶላር ለጊዜያዊው መንግስት እንዲተላለፍ ትናንት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተወሰነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች ለወራት ደሞዝ አልተከፈላቸውም፡፡ የውሃና የኤሌክትሪክ፣ የመንገድና የስልክ አገልግሎቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆኑት የነዳጅ ተቋማትም እንዲሁ፤ ተዳክመዋል፡፡ በርካታ የአገሪቱን ችግሮች ለማቃለልና የተረጋጋ የዲሞክራሲ ሽግግር ለማስጀመር፤ አሁን 5 ቢ. ዶላር ያስፈልገናል ብለዋል - ጊዜያዊው የፋይናንስ ሚኒስትር አሊ ታርሁኒ፡፡ ተመሳሳይ የህዝብ አመ ያስተናገዱት የግብፁ ሁስኒ ሙባረክ የፍርድ ውሳኔያቸውን ለመስማት ፍ/ቤት እየተመላለሱ ነው የቱኒዝያው መሪ ደግሞ አገር ጥለው በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡የሊቢያው ጋዳፊ እጣ ፋንታ ባይታወቅም መጨረሻቸው እንዳላማረ ግን ከወዲሁ ግል ሆኗል- እንደአብዛኞቹ አምባገነን መሪዎች፡፡

Read 5387 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 14:47