Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 20 August 2011 11:16

የሸራተን የስዕል አውደ ርእይ አርብ ይከፈታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የሸራተን የስዕል አውደ ርእይ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በመቀጠል ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የተሰበሰቡ የአርባ ሦስት ኢትዮጵያውያን ሥራዎች እንደሚቀርቡበት ተገለፀ፡፡ በመጪው አርብ ጧት በሆቴሉ በሚከፈተው የአራት ቀናት አውደ ርእይ ዋጋቸው ከአንድ ሺህ እስከ 100 ብር እና ከዚያም በላይ የሆኑ 400 ሥዕሎች ለሕዝብ ይቀርባሉ፡፡ የዛሬ አራት አመት በስምንት አርቲስቶች የስዕል ሥራዎች የተጀመረው አውደ ርእይ አምና የ40 ሰዓሊዎች፣ አቻምና የ30 ሰዓሊዎች ሥራዎች ቀርበውበታል፡፡

ሰሞኑን አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ላይ ከተገኙ አንጋፋ ሰዓሊያን መካከል ደስታ ሀጐስ እና ታደሰ መስፍን ሸራተን በአርቲስቶች ላይ ኢንቨስት አድርጓል በማለት ያመሰገኑ ሲሆን ሰዓሊ ወንድወሰን በየነ በበኩሉ ..ኢትዮጵያ ውስጥ በሰዓሊነት መኖር ከባድ ነው፤ ሸራተን የማንቂያ ደወል በመደወል አነቃቅቶናል.. ብሏል፡፡ ከሸራተን አዲስ አርት ኢንዶውመንት ፈንድ፣ ከስዕሎቹ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ እና ከካታሎግ ሽያጭ ለሥነጥበባት ት/ቤት ሊቶግራፊክ ፕሪንቲንግ ፕሬስ የተገዛ ሲሆን በዚሁ ፈንድ ቀጣይ የሥነ ጥበባት ሥራዎች ለመስራት እንደታቀደ የሸራተን አዲስ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ሴልስ እና ማርኬቲንግ ኤርያ ዳይሬክተር ኦማር ከሬራ ገልፀዋል፡፡በአውደ ርእዩ ከሚሳተፉት አርቲስቶች መካከል ዘሪሁን የትምጌታ፣ ወርቁ ጐሹ፣ ሶፊ ክፍሌ፣ ልዑልሰገድ ረታ፣ ተፈሪ መኮንን ይገኙበታል፡፡ በአውደርእዩ የሚታዩ ሥዕሎች www.artofethiopia.com በተሰኘ ድረገ ላይ የሚገኙ ሲሆን ሸራተን አዲስ የ80 ኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎችን ሥራዎች በቋሚነት እያሳየ ነው፡፡

 

Read 4591 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:17

Latest from