ሰሞኑን አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ላይ ከተገኙ አንጋፋ ሰዓሊያን መካከል ደስታ ሀጐስ እና ታደሰ መስፍን ሸራተን በአርቲስቶች ላይ ኢንቨስት አድርጓል በማለት ያመሰገኑ ሲሆን ሰዓሊ ወንድወሰን በየነ በበኩሉ ..ኢትዮጵያ ውስጥ በሰዓሊነት መኖር ከባድ ነው፤ ሸራተን የማንቂያ ደወል በመደወል አነቃቅቶናል.. ብሏል፡፡ ከሸራተን አዲስ አርት ኢንዶውመንት ፈንድ፣ ከስዕሎቹ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ እና ከካታሎግ ሽያጭ ለሥነጥበባት ት/ቤት ሊቶግራፊክ ፕሪንቲንግ ፕሬስ የተገዛ ሲሆን በዚሁ ፈንድ ቀጣይ የሥነ ጥበባት ሥራዎች ለመስራት እንደታቀደ የሸራተን አዲስ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ሴልስ እና ማርኬቲንግ ኤርያ ዳይሬክተር ኦማር ከሬራ ገልፀዋል፡፡በአውደ ርእዩ ከሚሳተፉት አርቲስቶች መካከል ዘሪሁን የትምጌታ፣ ወርቁ ጐሹ፣ ሶፊ ክፍሌ፣ ልዑልሰገድ ረታ፣ ተፈሪ መኮንን ይገኙበታል፡፡ በአውደርእዩ የሚታዩ ሥዕሎች www.artofethiopia.com በተሰኘ ድረገ ላይ የሚገኙ ሲሆን ሸራተን አዲስ የ80 ኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎችን ሥራዎች በቋሚነት እያሳየ ነው፡፡