Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 10:54

..የምንሰራው ገንዘብ አይተን ሳይሆን ጥበብ ተጠምተን ነው..

Written by 
Rate this item
(3 votes)

በ1973 ዓ.ም. በፈረንሳይ አካባቢ የተወለደው አርቲስቱ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በብሔራዊ ኢትዮጵያ፣ ሁለተኛ ደረጃን በተፈሪ መኰንን እንዲሁም ከእንጦጦ ቴክኒክ ኮሌጅ በቲያትር ዲፕሎማውን አግኝቷል፡፡ ..ገመና ቁ.2.. ላይ ዶ/ር ምስክርን ሆኖ የሚጫወተው አርቲስቱ፤ ከጋዜጠኛ ሰላም ገረመው ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡
እስቲ ዳንኤል ሰውየውና ዳንኤል ተዋናዩ ምን እንደሚመስሉ ግለልኝ . . .  
|ህይወት´ ፊልም ላይ በዳይ አፍቃሪ የነበረና ይቅርታን የሚጠይቅ፣ ..የአውሬው  እርግቦች.. ላይ መቶ አለቃ ሆኖ በሶማሌ ጦርነት ከቤተሰቡ የተለያየ እና እህቱን የሚያፈቅር ወታደር፣ ..እቴጌ.. ላይ ሞኝና በራሱ ያልቆመ አፍቃሪ፣ ..ትስስር.. ላይ የታሪክ መምህር፣ ..ማክቤል.. ላይ ንፁህ አፍቃሪ፣ ..የታፈነ ፍቅር.. ላይ አጭበርባሪ  ..ተስፈኞቹ.. ላይ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር ከሙስና የዳ ሠራተኛ፣ ..ሰውየው.. ላይ  ዱርዬ የሀብታም ሹፌር፣ ..ባቢሎን በሳሎን.. ቲያትር ላይ ቦዘኔ አፍቃሪ፣ ..ገመና ቁጥር 2.. ላይ ዶ/ር ምስክር ነው ዳንኤል ማለት፡፡ የሚገርመኝ ..ባቢሎንን.. ስሠራ ጥሩ ያልሆነ ገ ባህሪ ወክዬ ስለምጫወት ተመልካቹ መጣ ደሞ እንደሚለኝ አውቃለሁ፡፡

በጣም የሚያስጠላ ካራክተር ነው የምጫወተው፡፡ እኔ ግን ደስ ይለኛል፡፡ ህዝቡ ካራክተሩን ቢጠላውም እኔን ያውቀኛል፡፡ ..ገመና..ን ደግሞ ስሠራ ሁሌ የማስበው የቤተሰቤን ችግር ነው፡፡  ይሔ እንግዲህ በሥራዬ ያለኝ ማንነት ነው፡፡ በእኔነቴ ደግሞ በጣም ማግባት የሚፈልግ በፍቅር የሚያምን ሰው ነው - ዳንኤል፡፡ ክርስቶስ ፍቅርን ያሳየን እስከ ሞት ድረስ ነው፡፡ እኛ ያንን ማድረግ ባንችልም ሰውን ሁሉ በእኩል ማየት እንዳለብን አምናለሁ፡፡ ሰውን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በቀለም ሳለያይ በእኩል እመለከታለሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቤት ወጥተህ እንጦጦ እየኖርክ መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡
ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት በቤተክርስቲያን ነው፡፡ አብዛኛውን የፍልሰታና የአብይ ፆም  በሁለቱ ቤተክርስቲያናት ነው የማሳልፈው፡፡ አሁን ያለሁት በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ የሚገኝ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ፍልሰታ ፆም ሲጀምር የምቀመጥበት ቤት ነው፡፡ የቤቱ ባለቤቶች ቤቱን ቢያከራዩትም ያከራዩትን ሰዎች አስወጥተው በየዓመቱ ለእኔ ያከራዩኛል፡፡ ፆሙ እስኪያልቅ እቆይና ወደ ቤቴ እመለሳለሁ፡፡ ይሔ እኔ መንፈሴን ለማደስ የማደርገው ነው፡፡ ማናችንም ራሳችንን ለማደስ ሥራ ስንጨርስ ለእረፍት ቫኬሽን ብለን አንድ ቦታ ሔደን እራሳችንን እናዝናናለን፡፡ ከመንፈሳዊ ህይወት ደግሞ የበለጠ ብዙ ነገር ተጠቃሚ ትሆኛለሽ . . . በበረከትም በብዙ ነገርም፡፡
የፆሙ ወቅት ሥራህን አያስተጓጉልብህም . . . ከከተማ ራቅ ስላልክ ማለቴ ነው?
መድኃኒዓለም ለኔ ያለውን አላጣም፡፡ በእርግጥ ከበድ ያሉ ሥራዎች ሲኖሩ ከደብረ ሊባኖስም የምወጣበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ ..ባቢሎን በሳሎን.. አርብ ይታያል፡፡ ስለዚህ ቅዳሴ ስጨርስ እወጣና ሰርቼ ወደ እንጦጦ እመለሳለሁ፡፡ ሌላም የማይቀር ሥራ ሲገጥመኝ እንዲሁ አደርጋለሁ፡፡
በቤተክርስትያን ማደግህ ለሙያህ ያበረከተው አስተዋኦ ይኖር YçN?         
እኔ በመዘምራንም በድራማም አልተሳተፍኩም፡፡ ግን ተምሮ ማስተማር ተምሬያለሁ፡፡  ሌላ እኔ መግለጽ ከምችለው በላይ አምላኬ ፈጣሪ በጣም ይወደኛል፡፡ እናቱ ቅድስት ኪዳነ ምህረትም እንደ ልጇ በጣም ትወደኛለች፡፡ እነሱ አሳደጉኝ፤ በጣም አብልጠው ስለሚወዱኝም ወደ ራሳቸው ሳቡኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሌ ወደ ቤተክርስቲያን ስሔድ ደስታ ይሰማኛል፤ ይህንን የፈቀደው ደግሞ እግዚአብሔር ነው፡፡ በዛ መልኩ ነው እውቀት ያገኘሁት፡፡  
ወደ ፊልም ሙያ የገባኸው መቼ ነው?  
ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ነው መሥራት የጀመርኩት፡፡ እስካሁን ህዝብ የወደዳቸው ዘጠኝ ፊልሞች ሠርቻለሁ፡፡
በጣም የረካህበት ሥራ የትኛው ነው? ከፍተኛ ክፍያ ያገኘህበትስ?
ሁሉም ለእኔ ትላልቅ ሥራዎች ናቸው፤ ይሄ ይሻለኛል ብዬ መርጬ የሠራሁዋቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ ማበላለጥ አልችልም፡፡ በክፍያ ደረጀ ..የታፈነ ፍቅር..፣ በ..ማክቤል..፣ በ..ሰውየው.. ፊልሞች ከፍተኛ ክፍያ ተከፍሎኛል፡፡ መጠኑን ባልናገርም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥርን የሚያክል ትልቅ ክፍያ ተከፍሎኛል፡፡ ለእኔ ትርፌ የህዝብ ፍቅር፤ የህዝብ አስተያየት ነው፤ ክፍያን አስቤ አልሠራም፡፡ እኔ የህዝብ አገልጋይ ነኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን የፊልም ባለሙያዎች ከበፊቱ ጀምሮ ገንዘብን ተሞርኩዘን የተነሳን ቢሆን ኖሮ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ፊልምና ቲያትር አይኖርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ባለሙያው ሌላ ገንዘብ የሚያገኝበት ስራ ላይ መሠማራት ይችላል፡፡ እኛ የኢትዮጵያ አክተሮች ቦሊውድ ወይም ሆሊዉድ ካሉ የፊልም ባለሙያዎች ጋር ስንነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ተከፋዮች ነን፡፡ ሆኖም ገንዘብን አይተን አይደለም የምንሰራው ጥበብን ተጠምተን ነው፡፡ በአርቱ ፍቅር የሚኖር እንጂ ገንዘብን አስቦ የሚኖር ማንም የለም፡፡  
. . . ግን የአገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ እያደገ ነውና የእናንተንም ክፍያ (ገቢ) መጨመሩ አይቀርም . . .?  
የቀደሙ ባለሙያዎችን በዚህ ጉዳይ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ የኢትዮጵያን ፊልምና ቲያትር አሳድገው ለእኛ አስረክበውናል፡፡ እነሱ ግን በምን አይነት ሁኔታ፣ ምን እየተከፈላቸው፣ ምን እየበሉ ሠሩ የሚለውን ታሪካዊ ነገር ስንፈትሽ ብዙ መስዋዕትነትን እንደከፈሉ እንረዳለን፡፡ እነሱ ሳይበሉ ቲያትር ቤት ገብተው ቲያትርን ምግባቸው አድርገው፣ እስክሪፕትን እየበሉ ሳይከፈላቸው ሜዳ ላይ አጥንተው ነው ሙያውን ያሳደጉት፡፡ በርግጥ ያንን ታሪክ እየደገምን አይደለንም፡፡ የዚህ ዘመን ባለሙያ እድለኛ ነው፡፡ እኔ የመጀመሪያ ስራዬን ስሰራ የፊልም ምንነቱን በማላውቅበት ጊዜ እንኳን ክፍያ ተከራክሬ ነበር የሰራሁት፡፡ አሁን አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ክፍያ ባያገኙ እንኳን ተመጣጣኝ ገንዘብ እያገኙ ነው የሚሰሩት፡፡ አንዳንድ የምነቅፋቸው ፕሮዲዩሰሮች አሉ፡፡ አክተር የፊልሙ የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚረሱ፣ ግባቸው ገንዘብን ማግኘት ብቻ እንጂ ለሙያው ግድ የሌላቸው አሉ፡፡ ሙያውን የሚጠብቅ ባለሙያ አክተሩን ይጠብቃል፣ አክተሩ ዛሬ መኖር ሲችል ነው አስር ፊልም እናምርት ቢሉ አስሩም ፊልም ላይ ሊሠራለት የሚችለው፡፡ ከነዚህ ውጪ ግን ለሙያው ክብር ያላቸው አሁን እየመጡ ያለ ጥሩ ፕሮዲዩሰሮች አሉ፡፡ ይሄ ክፍያ አይመጥነውም ብለው የሚሟገቱ፡፡ ለምሳሌ እኔ በዚህ አጋጣሚ ጋሽ ውብሸትን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ለማስታወቂያ ቢሮአቸው ጠርተውኝ ከሠራተኛቸው ጋር ሲማከሩ ..እኛ ለማስታወቂያ የምንከፍለው ይሄን ያህል ነው፤ ነገር ግን ይሄ ልጅ የምናከብረው ባለሙያ ነው፤ ይሄ ገንዘብ ስለማይመጥነው ይሄንን እንክፈለው.. ሲሉ ደስ ብሎኛል፡፡ ባለሙያውን የሚያከብሩ ሰዎች እየመጡ ነው፡፡ መልካም የሆኑ ፕሮዲዩሰሮችን እግዚአብሔር እንዲያመጣ መፀለይ ነው፡፡ አንዳንዱ ፖስተሩ፣ ስልክ እንጨት ላይ ተለጥፎ፣ እሱ ዝናብ እየደበደበው የሚቆምና ታክሲ የሚጠብቅ አርቲስት አለ፡፡ ነገር ግን ብልጥ ልጅ የያዘውን ይዞ ነው የሚያለቅሰው፡፡ ለዛ ነው የተሠጠንን ክፍያ ይዘን አይበቃንም የምንለው፡፡ ነገ በጐ ነገር ተሻሽሎ ይመጣል ብለን ነው ህዝቡን በታማኝነት kእግዚአብሔር በተሰጠን ሙያ እያገለገልን ያለነው እንጂ አንዳንድ ፕሮዲዩሰሮች ለባለሙያው አያስቡም፡፡
አብዛኞቹ የአማርኛ ፊልሞች ላይ አንድ ሰው በፀሃፊነት፣ በተዋናይነትና በዳይሬክተርነት ስለሚሳተፍበት ደረጃው እንደሚወርድ ይነገራል፡፡ እዚህ ላይ ያንተ አስተያየት . . .?
አርቱን ከሚጥለው ዋናው ነገር ይሄ ነው፡፡ እኔ ፊልም ስሰራ እንደ ባለሙያ የማስበው ይሄን ነው፡፡ ሙያው የሚፈቅደውን ነገር ነው ይዤ መጓዝ ያለብኝ፡፡ ባለሙያ ይዤ መሄድ አለብኝ እንጂ ወጪ ለመቀነስ ብዬ የአክስቴን ልጅ (ቆንጆ ስለሆነች) እና ዘመዶቼን አሳትፌ አንድ ፊልም ማውጣት የለብኝም፡፡ ያ ፊልም ሲወጣ በህዝብ ዘንድ የዛን ፊልም ፕሮዲዩሰር ወይም አክተር ብቻ አይደለም የሚያስወቅሰው፤ የኢትዮጵያ ፊልም ተብሎ ነው የሚወቀሰው፡፡ ይህንን ስል ግን ጀማሪ ባለሙያዎች አይስሩ እያልኩኝ አይደለም፤ ተተኪ ባለሙያ ያስፈልጋል፤ ነገር ግን ለዛ ስራ ይመጥናሉ ወይ ተብሎ ችሎታቸውን መመዘን ያስፈልጋል፤ እንደዚያ ከተደረገ ሥራው ተወዳጅ ይሆናል፡፡ የሠራው ሰውም ሆነ ፊልሙ አድናቆት ያገኛል፡፡ ለአንድ ፊልም ሥራ አዳዲስ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ባለሙያውም መገምገም አለበት፤ የተለያየ ካራክተር ስለሚጫወት፡፡   
በፊልም ላይ የፍቅር ነገሮች ለምሳሌ በግል መሳሳም ለምን ታየ የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ኧረ ምንም አይደለም የሚሉም አሉ፡፡ አንተ ምን T§lH?
ፊልም የገሀዱ ዓለም ነብራቅ ነው ካልን ያንን ማሳየት አለብን፤ ህዝብን ለማስተማር፡፡ ስለዚህ አንድ ባለሙያ (ደራሲ) አንድን ነገር የሚያነሳው ከሚያውቀው ነገር ነው፡፡ የአሜሪካኖች ፊልም ላይ የማናውቀውን ነገር ሲያሳዩን በፀጋ እንቀበላለን፤ በሀገራችን ያለውን እውነታ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ግን ህይወታችን ውስጥ እንዴት ነው የምናሳልፈው የሚለውን እንጠይቃለን፡፡ ያንን በጣም መግለጽ አለብን ዳይሬክተሩ ሲገልጽ በካሜራ ሸፍኖት እንደውም በስሱ ነው የሚታየው ብዙም የለም፡፡ ለምሳሌ መሳሳምን በተመለከተ የሆሊውድ ፊልሞችን የሚመስል የአገር ውስጥ ፊልም አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ነገር ግን ትናንሽ የፍቅር ነገሮች ይኖራሉ፤ ይሄ ደግሞ ውበት አለው፡፡
አንተ እንዲህ ያለው ሚና ቢሰጥህ ትቀበላለህ . . .?
ጥሩ ገታ የሌለውና ባህላችንን የሚያሳንስብኝ እንዲሁም የህዝብን ጥያቄ የሚያስነሳብኝ ከሆነ አልሠራውም፡፡ ግን በትንሹ ማንባረቅ የሚቻልበት ከሆነና ተመልካቹን ለማሳመን ከሆነ ሥራዬ ስለሆነ እንደ ሁኔታው እሠራዋለሁ፡፡
..ባቢሎን በሳሎን.. ቲያትር ላይ የደሳለኝን ገፀባህርይ አንተን ጨምሮ አራት ያህል ተዋናዮች ተጫውተውታል፡፡ ማን ተዋጥቶለታል T§lH?
ተስፋዬ ገ/ሃና፣ ሱራፌል ወንድሙ፣ ሰለሞን ቦጋለና ሳሞሶን ታደሰ (ቤቢ) ተውነውታል፡፡ በሰሌና በቤቢ ጊዜ አይቼዋለሁ፡፡ ሰሌ ሲሠራው ፊልሙን ለማየት ነው የገባሁት፡፡ በቤቢ ጊዜ ግን ብሎኪንጉን ለማየት ነው፡፡ ሰሌ በሚሠራ ወቅት ደሳለኝ ቲያትሩ ላይ መምጣቱ የሚታወቀው በማስቲካው ድም ነው፡፡ እኔም እንደ ተመልካች አንድ ጥያቄ ነበረኝ፡፡ በትክክል ማስቲካ ነው ወይስ ባክግራውንድ ድም ነው ጧጧ የሚለው፡፡ ሰዎች ባክግራውንድ ድም ሆኖ እሱ አፉን የሚያንቀሳቀስ ነው የሚመስላቸው፡፡ ነገር ግን ማስቲካ መሆኑን ሳውቅ በጣም ነው የገረመኝ፡፡ ለሌላ ሥራ ይጠቅማል ሰሌን አለማምደኝ እለዋለሁ ብዬ ሳስብ ነበር፤ ግን ሳልጠይቀው ነው ሥራውን የጀመርኩት፡፡
እንዴት ነው ወደ ቲያትሩ የገባኸው?
ቤቢ ..ባቢሎን..ን ሳይሠራው በፊት አርብ ሀገር ፍቅር የሚያጠናው ሌላ ቲያትር ነበረው፡፡ በወቅቱ ሰሌ ወደ ውጪ ሔደ፡፡ በሰሌ ፋንታ ቤቢ ይተካዋል፣ ቤቢ ..ባቢሎን..ን እየሠራ ለረጅም ጊዜ የተለማመደው ቲያትር በሀገር ፍቅር አርብ መታየት ሲጀምር ሰው ያስፈልግ ነበር፡፡ ጌታቸው ስለሺ (ፕሮዳክሽን ማናጀሩ) ደግሞ ከእኔ ጋር አንድ ላይ ነው የምንማረው፡፡ ባክስቴጅ ሆነው ማን ይምጣ እየተባባሉ ሲያወሩ ጌች እኔን ይመርጠኛል፡፡ አለማየሁ ይቀበልና በዚህ ድቆ ነው ካስት የተደረኩት፡፡ ጽሑፉ እሁድ ተሰጥቶኝ አርብ ነው ያቀረብኩት፡፡ በጣም አስቸኳይ ነበር፡፡ ስለዚህ በሦስት ወር የሚያልቅ ነገር ነው በአንድ ሳምንት ተለማምጄ የጀመርኩት፡፡ አሁን አመት ከዘጠኝ ወር ሆኖኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ ያበቃኝ ቡድኑ ነው፡፡ ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡ ይሔ የመጀመሪያ ቲያትሬ ነው በማበረታታት የሚሰጡኝ ሞራል የበለጠ እንድሠራ አድርጐኛል፡፡
..ህንደኬ.. ቲያትር ላይ የመቅዶናዊው ንጉሥ እስክንድርን ካራክተር ለረጅም ጊዜ ተለማምደህ በመጨረሻ ለህዝብ ሲቀርብ አንተ አልተሳተፍክም . . .     
ከጌትነት ጋር የመሥራት አጋጣሚውን ለማግኘት ስመኝ ነበር፡፡ አጋጣሚውን ደግሞ በ..ህንደኬ.. አግኝቼው ነበር፤ ሆኖም የንጉሥ እስክንድርን ካራክተር ተለማምጄ ለህዝብ በቀረበበት ሰዓት ጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበርኩም፡፡ የፈተና ሰዓት ነበር፡፡ የራሴን ፊልምም ጀምሬ ነበር፤ ..ሊንዳ.. የሚል ሙሉአለም ታደሰ፣ ፍቃዱ ተክለማርያም፣ ሀምለሰት ሙጨ፣ ዝናህ ብዙ ወይም በ..ሰው ለሰው.. ድራማ ላይ መስፍንን ሆኖ የሚሠራውን እኔን ጨምሮ የሚተውኑበት ትልቅ ፊልም እየሠራሁ ስለነበረ ነው፡፡ የሰውን አስር ፊልም የምትሠሪበት ጉልበት የራስሽን አንድ ፊልም ለመሥራት ይፈጅብሻል፡፡ ፊልሙ አዲስ አበባ ብቻ አልነበረም፤ ጐንደር ይሠራል፣ ባህርዳር ይሠራል ሁለቱ ቦታዎች ላይ ነበር ከትምህርት ጊዜ W በማገኛት ሰዓት ሁሉ የማጠፋው፡፡ ሌላ ስክሪፕት ለማጥናት አልችልም ነበር፡፡ ምክንያቱም የራሴን ድርሰት ማረም የነበረብኝ፡፡ ስለዚህ ምን ያህል ድካም እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚያ ላይ ሁለት ፊልሞችን እየሠራሁ ነበር፡፡
..ሰውየው..ን እና ..ተስፈኞች..ን ይህን ሁሉ ይዤ ነበር ..ህንደኬ..ን ስለማመድ የነበረው፡፡ በኋላ ..ህንደኬን.. እንደማልሠራው እያወቅሁ መጣሁ፡፡ ምክንያቱም ጐንደር ላይ ለአንድ ወር እንቀመጣለን፤ በፕሌን እመጣና ከጐንደር ሀሙስ ገብቼ አርብ ..ባቢሎን በሳሎን..ን እሠራለሁ፣ ቅዳሜና እሁድ ጐንደር መመለስ አለብኝ፤ ግን ..ህንደኬ..ን ከሠራሁ ቅዳሜ  ላልመለስ ነው ማለት ነው፡፡ ለምን እሁድ ..ህንደኬ..ን ማሳየት አለብኝ፤ ስለዚህ የእኔን ፊልም ለመሥራት ጐንደር ያሉ ባለሙያዎችን እንዴት ትቼ ነው እዚህ የምቀመጠው፡፡ ..ባቢሎን..ን የገባሁበት ግዴታዬ ስለሆነ ነው፤ እናም ለጌትሽ ችግሮቼን ነገርኩት፡፡  አይተን መፍትሔ እንፈጥራለን አለኝ፡፡ ሌላ የእስክንድርን የሚሠራ ካስት ሲደረግ ከላዬ ላይ ትልቅ ሸክም የተራገፈልኝ መሰለኝ፡፡ በደስታ ነው ያንን ቀን ያሳለፍኩት፤ ምክንያቱ ደግሞ ጌትሽን ማስቀየም ስለማልፈልግ ነው፡፡
የአንድ ቀን ሥልጣን ቢሰጥህ ምን ¬dRUlH?
መሬት ለመሀንዲሶች ሰጥቼ በዓመትም ይጨርሱት ሀምሳ ሲኒማ ቤቶችና ቲያትር ቤቶች አስገነባለሁ፡፡
በ..ገመና.. ብዙ ገጠመኞች አለኝ፡፡ ቅዳሜ ቀን ነው፡፡ ቦሌ አካባቢ አንድ ወጣት ..ዶ/ር እባክህ ምሳ ግዛልኝ.. ሲለኝ ..ዝርዝር ጨርሻለሁ ነገ እንገናኛለን.. አልኩት፡፡ ልጁም ..ነገ የምንገናኘው በገመና ነው.. አለኝ፡፡ ሌላው አርቲስት ደረጄ ደመቀ ሲያገባ ሚዜ ነበርኩ፡፡ በወቅቱ ደግሞ ዶ/ር ምስክር ታስሮ በዋስትና የሚለቀቅበት ክፍል ነበር፡፡ ታዲያ የሙሽሪት ቤተሰብ አዩኝና ..ለሠርጉ ነው ዋስትና የተፈቀደልህ.. አሉኝ፡፡ ደረጄ ደመቀ ማለት ..ገመና.. ላይ የእኔ ዳኛ ሆኖ የሚሠራው ነው፡፡

 

Read 5280 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:00