Saturday, 13 August 2011 11:18

..እናንተ የምትንቁ እዩ ተደነቁም

Written by  ጤርጢዮስ - ከቫቲካን
Rate this item
(0 votes)

በ..መጠየቅ.. ሀቁን፣ በ..እምነት.. እውነቱን እናረጋግጣለን!
የዛሬው ወጌ የሚያጠነጥነው አንድ ፍልስፍናዊ     እሳቤን መሠረት አድርጐ ነው፡፡ ሆኖም ዓላማዬ ፍልሰፍናን ማራገብ አሊያም ማጣጣል አይደለም፡፡
የማላራግበው የጥበብ ጌታ የህይወቱ ፍልስፍና ለሆነለት ሰው ከዚያ በልጦ የሚፈለግ ጥበብ የትም ባለመገኘቱ፣ ያንን ያላቀፈ የትኛውም ፍልስፍናም አድሮ እንደገለባ መቅለሉን በመገንዘቤ ሲሆን የማላጣጥለው ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠውን ..እስከ ጥግ.. የማሰብ ነፃነት ለማድነቅ አግዞኝ ስለሚያውቅ ነው፡፡

አሊያስ ..አዲስ - አድማስ.. ላይ እንኳ አላማኝነት መታወቂያቸው እንዲሆን በመሻታቸው ብቻ yእግዚአብሔርN ነገር በኢ-ፍትሃዊ ብይናቸው የሚያጣጥሉትን ፀሃፍት ሁፍ እስከመጨረሻው ለማንበብ መታገስን ከዬት አመጣዋለሁ? ይልቁንስ ከአሳቢነት ይልቅ አላማኝነት ..ስመ - ገናና.. እንደሚያደርግ አውቀው አንዱ ፍልስፍናን፣ ሌላው ሳይንስን፣ ሌላኛውም ..ዴሞክራሲያዊ መብትን.. የክህደቱ ማደቂያ ለማድረግ ስቄ እንጂ ገርሞኝ የማያውቀው ለዚያ ነው፡፡ የነዚህ ..ሚጢጢዬዎች.. ሀሳብ እኔን እንዲህ ካሳቀኝ ሰማያት በስንዝር የሚለካውና አሕዛብን ሁሉ በገንቦ ውስጥ እንዳለ ጥቂት ጠብታ የሚመለከተው ልዑል ምን ያህል ያስቀው ይሆን?
በቅርቡ በገበያ ላይ የዋለውና ብሥራት ዕውነቱ  በሚል ርዕስ y..ተጨባጫዊነት.. ፍልስፍና ጠንሳሽና አቀንቃኝ የሆነችውን የአየን ራንድን ..Philosophy who needs it.. የተሰኘ መሃፍ ..ፍልስፍናን ለሚፈልጉ.. በሚል ቀለል ባለ አማርኛ ጥሩ ሆኖ ተርጉሞታል፡፡ ለአዲስ አድማሷ አላማኝ ተሟጋቾቻችን መሀፉ እንደ ..ቅዱስ መሀፍ.. የሚቆጠር ሲሆን ከዚያ እየቆነጠሩ ይዞሩት ለነበረው አረም መለያ ይሆን ዘንድ የአማኞቹን ጎራ በአግባቡ በወከሉት ፀሀፊ ብዕር የነጠረው ምንነቱ ተገልጦ ታይቷል፡፡ ..ተጨባጫዊነት.. (Objectivism) ..የክህደት ራስ.. ተሰኝቶ ፍልስፍናው መንፈሣዊ ህላዌን በዜሮ ካባዘቱ ፍልስፍናዎች ሁሉ በአስቀሚያነቱ ወደር እንደማይገኝለት ገልል፡፡
የፍልስፍናውን መሠረታዊ ዕሳቤ ለማስታወስ ያህልም ለፈላስፋይቱ አየን ራንድ መኖር (Existence) ከዚህ ከሚታየውና ከሚጨበጠው ዓለም ሁኔታ የላቀ ትርጉም የሚሰጠው እንዳልሆነ፣ ሰው በጥረቱ የሚገነዘበው የህላዌ ፍቺም ከዚህ ሌላ ባለመሆኑ ይህንኑ እውነት ብሎ መቀበልና ህግ አድርጐ መገዛት ግድ ስለማለቱ ተወስቷል፡፡ የአየን ራንድ ነገረ-ቀኖና ..Existence exists.. ወይም ..ኗሪው ይኖራል.. ብሎ መጀመርያ እንጂ ..ኗሪው እንዴት ኖረ?.. ብሎ መጠየቅ ከንቱ ጥያቄ ተደርጐ ስለመቆጠሩ ብቻ ሣይሆን ለ ..ኗሪው መኖር ተጠያቂው ማነው?.. ተብሎ ቢጠየቅም ምላሹ ..ኗሪው ራሱ.. ከማለት የሚዘል መልስ እንደሌለው ተብራርቷል፡፡ በተጨባጫውያኑ ዕይታ ..ህገ-መንስኤ..   (Law of causality) እያንዳንዱ t=Æ ነገር (entity) ለመኖሩ ሰበብ እንዳለው ከመገንዘብ ለማፈንገጥ ሲሹም የሚከተለውን ስለማለታቸው ተጠቁሟል፡፡ ..እውነታ ፍጥጥ ብሎ ተገንዘበኝ እያለህ እውነትነቱንና t=ÆntÜN ወደማይጨበጥ አስተሳሰብና ድምዳሜ ሊወስድብህ የሚችል ጥያቄ አትጠይቅ፣ እንዴት ተፈጠረም አትበል፣ የተጀመረ ወይም የተጨረሰ ነገር የሌለ እውነታ (Reality) መኖሩን ትገነዘባለህ እንጂ እንዴት እንደኖረ ለማወቅ መቋመጥ ..ሃሳባዊ.. አሊያም ..qÜS-አካላዊ.. ያደርግሃል በማለት ፍልስፍናው ራሱን ከሌሎቹ የ..እውነት መቅመሻ.. ዘዴዎች የለየበትን ብጥ አስረድቷል፡፡
ግና ከተጨባጫውያኑ የነገር አገላለ አንዳች ሀቅ ብንመዝ ..ኗሪው እንዴት ኖረ?.. ተብሎ ሳይጠየቅ መኖሩን ብቻ አምነን ልንቀበል የሚገባን ፈጣሪ እንጂ ፍጥረቱ አልነበረም፡፡ ..የተጀመረም.. ሆነ ..የተጨረሰ.. ምንነት የሌለው ጅማሬውም ሆነ ፍፃሜው የሚታወቀው ..እኔ.. ማለት ..እኔ ነኝ.. ያለው እግዚአብሄር እንጂ በእርሱ ይሁንታ ወደ መኖር የመጣው ዓለም አይደለም፡፡ ስለ ..እውነትነት.. እና ..ተጨባጫዊነት.. ከተነሣም ከዚህ ..ከሚታየው.. ይልቅ ..የማይታየው.. ለሰው መንፈስ t=Æ መሆኑን በእምነት ብናውቅም ይህንን ግን ለፍጥረታዊ ሰው ማስረዳት እንዴት ንቅ ነው፡፡
ለማንኛውም ..ፍልስፍናን ለሚፈልጉ.. የተሰኘው መሀፍ የፀሀፊዋን የክህደት ሰበቦች ቢዘረዝርም ነገር ግን ሰው ራሱንና አካባቢውን ለመረዳትና በጊዜና በቦታ የታጠረውን አካላዊ ግዛቱን ለመፈተሽ የሚያግዙትን የፍልስፍና መሠረታውያን አቅፎ ይዟል፡፡ ..ከዬት መጣሁ?.. ከማለት ይልቅ ..የት ነው ያለሁት?.. የሚልን ..ቀላል.. ጥያቄ መነሻው ያደርጋል፡፡ ከፍልስፍና የእውነታ ማፈላለጊያዎችም ሜታፊዚክስን፣ ኢፒስቲሞሎጂን፣ ኤቲክስን፣ ኢስቴቲክስንና ፖለቲክስን ማጠንጠኛው ያደርጋል፡፡ የሰው ልጅ ሦስቱ መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚከተሉት እንደሆኑ YgLÉL:-
1. የት ነው ያለሁት?
2. ያለሁበትን ቦታ እንዴት ላውቅ እችላለሁ?
3. ምን ማድረግ አለብኝ?
ሆኖም ..ፍልስፍና ለእነዚህ ዋና ጥያቄዎች ቀጥተኛ መልስ አይሰጥም፡፡ ለምሣሌም የት ነው ያለሁት? ለሚለው ጥያቄ ..አዲስ አበባ.. ወይም ..ዛንዚባር.. እንደሆንክ ከመንገር ይልቅ አንተው ራስህ መልሱን ፈልገህ እንድታገኘው ዘዴውን ይነግርሃል፡፡..፣ ..የት ነው ያለሁት?.. የሚለው ጥያቄ የሚመለከተው ደግሞ ..ሜታፊዚክስ.. በመሆኑ በዚህ የማፈላለጊያ ዘዴ የማንነት ህግ (The law of Identity) ትልቅ ሥፍራ ይሠጠዋል፡፡ ሀቁን ፍንትው አድርጐ ለማሣየትም ቀጣዮቹን ጥያቄ መጠየቅ እንደሚያሻ ይጠቁማል፡፡ (የእኔ ዓላማ ደግሞ አማኞች ለፍልስፍና መሠረታዊ ጥያቄዎች ያሏቸውን ምላሽ ማስገንዘብ በመሆኑ ምላሼ ሁሉንም የእምነት ክፍሎች ባይወክልም ለጥያቄዎቹ የራሴን ምላሽ እየሰጠሁ መዝለቄ ግድ ይሆናል፡፡) እነሆም ጥያቄና መልሱ በዚህ መልኩ ተደርድሯል፡፡
- የምትኖረው በተፈጥሮ ህግ በሚመራው፣ የተረጋጋና ጥብቅ የሆነ ሥርዓት ባለው ህዋ ውስጥ ነው? ወይስ በምንም መንገድ ሊገለ በማይቻለው የተዘበራረቀ ዓለም? (መጀመሪያ ላይ በተገለፀው፡፡)
- በዙሪያህ የምታያቸው ነገሮች እውነተኛ ናቸው ምትሃት? (እውነተኛ)  
- ራሣቸውን ችለው ይኖራሉ ወይስ በዓዕምሮህ ውስጥ? (ራሣቸውን ችለው፡፡)
- ነገሮቹ አሁን እንዳሉት ናቸው ወይስ አንተ እንደ ዕውቀትህ የተገነዘብካቸው ድርጊቶች? (ግንዛቤዬ ከነገሮቹ ምንነት የተለየ ሊሆን አይገባውም፡፡)
- ምንነታቸው በሰው ምኞት ሊለወጥ ይችላል? ወይስ አይችልም? (xYCLM)
በዚህ ረገድ የተፈለገውን ያህል ድምዳሜ ላይ ቢደረስም ሌላም መልስ የሚያሻው ጥያቄ ይመጣል፡፡ ይኸውም ..እንዴት ነው ያወቅሁት?.. ወይም እንዴ ነው የማውቀው? የሚለው ሌላው መሠረታዊ ጥያቄ ማለት ነው፡፡ እናም ..ዕውቀቱ እንከን የማያጣው የሰው ልጅ ለራሱ የደረሰበት ድምዳሜ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ማረጋገጫው ምንድነው?.. ቢባል ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ዕውቀትን እንዴት እንደሚያገኝ በሚያጠናው ኤፒስቲሞሎጂ (Epistemology) በኩል ይተነተናል፡፡ በዚያ ውስጥ የሚገኙት የዕውቀት ማረጋገጫዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡ (እኔም ጎን ለጎን ለጥያቄዎቹ የራሴን ምላሽ በቅንፉ ውስጥ ማስቀመጤን እቀጥላለሁ፡፡)
- የሰው ልጅ ዕውቀትን በምክንያት በተደገፈ ሂደታዊ ትንተና ያገኛል? ወይስ ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ኃይል በድንገታዊ መገለጥ? (በሁለቱም)
- ምክንያታዊnTN የሰው ልጅ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት በመተንተን የሚያገኘው ነው? ወይስ የሰው ልጅ ከመወለዱ አስቀድሞ በህሊናው ውስጥ በአንድ ጊዜ የሚቀመጥ (ሁለቱም XNdyምንነታቸው መልስ ይሆናሉ፡፡)
- ምክንያት እውነታን በብቃት ለመረዳት ይችላል? ወይስ የሰው ልጅ ከምክንያት የሚበልጥ ሌላ የሚያስብበት ሂደት አለው፡፡ (ሁለቱም መልስ ይሆናሉ፡፡)
- የሰው ልጅ ስለ ነገሮች በእርግጠኝነት መናገር የሚችልበት ደረጃ ላይ ይደርሣል? ወይስ ሁልጊዜ በማያቋርጥ ጥርጣሬ ውስጥ ሲባዝን ይኖራል? (የሰውን ልጅ ከማያቋርጥ ጥርጣሬና መባዘን አውጥቶ እርግጠኛ ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም ዳሩ ግን ፈላስፋነቱ በ..ኗሪው.. መኖር እርግጠኛ የሆነችውን ያህል እኔም እርግጠኛ ነኝ፡፡ ..ኗሪውን.. በሚያኖረው ላይ ያለን እርግጠኝነት ደግሞ ከዚያ በጣም ይልቃል፡፡)
ከአየን ራንድ የተጨባጫዊነት ፍልስፍና አንፃር ከጊዜና ቦታ (Space and Time) አጥር ውጪ ስላለው መንፈሣዊ ዓለምም ሆነ በዚያ ክልል ተንሠራፍቶ ስለሚኖረው ልዑል ማሰብ መጠየቅና እርግጠኛ መሆን ቂልነት ተደርጐ በመቆጠሩ የስሜት ህዋሣቱ ተሣትፎ የሌለበት ..ዕውቀት.. ማስረጃ ምክንያት ሁሉ ውድቅ ያደርጋል፡፡ በ..ኢፒስቲሞሎጂ.. ምክንያት ያለውን የበላይነት (The Supremacy of reason) ታሣቢ አድርጐም ..ምክንያት.. ኗሪውን በእርግጠኝነት ለመጨበጥ የሚያስችል በመሆኑ yxþ-እርግጠኝነትM ሆነ የአንፃራዊነት የጥርጣሬ ፍልስፍና በእጅጉ ይብጠለጠላል፡፡ ..ይህንን ማረጋገጥ አልችልም ነገር ግን እውነት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ (I can’t prove it but I feel that it is true) ተብሎ የሚቀርብ ምክንያት ለስሜት ተስማሚ ሆኖ የቀረበ አባባል ከመሆን ያለፈ ግምት የሚሰጠው ዓይደለም፡፡
በዘመናዊው ዓለም የሞራል ፍልስፍና ዘርፍ ስሙ ከፍ ብሎ የሚጠራው ዴቪድ ሂዩምም ስለ ጉዳዩ ሥር በሰደደው ጥናቱ ደጋግሞ የሚታነቅበት መንፈሣዊ ሀቅ እንደነበር ቢታወቅም ስለ እምነት በሰጠው አስተያየቱ ..እምነት ከግላዊ አስተያየት ጋር የተያያዘ ስሜት እንጂ ዕውቀት ሆኖ በሰው ውስጥ የሚቀመጥ t=Æ ነገር አይደለም፡፡.. በማለት ፎ ነበር፡፡ ሆኖም በግለሰቡ ውስጥ ያደረገው የእምነት ስሜት ስለሚታመነው ነገር አንዳች ተፈጥሯዊ ወይም መገለጫዊ መነሻ ሣይኖረው ከቶም እምነት ሆኖ ሊቀመጥ የሚችልበት መሠረት የለውም፡፡ ሁሉን ነገር ከሚታየውና በስሜት ህዋሳት በኩል ከሚጨበጠው ዕውቀት አንፃር ከሚመለከቱት ፈላስፎች በተቃራኒ የቆመው ፈላስፋውና የሂሳብ ሊቁ ፓስካል ግን በተለይም እግዚአብሔር ሳይታይ የሚኖር አምላክ ስለመሆኑ ለመግለ ሲፈልግ ያለው ይህንን ነው:- ..yእግዚአብሔርN አለመታየት የማያረጋግጥ ሃይማኖት ሁሉ እውነት ዓይደለም፡፡..
..(ውስጣዊ) ስሜት የማወቂያ መሣሪያ ዓይደለም፡፡.. የምትለን አየን ራንድ ..አንድ ነገር የሆነ ዓይነት ስሜት እንዲሰማህ ከማድረግ ባለፈ ስለ እውነታ የሚነግርህ ምንም ነገር የለም፡፡.. ትላለች፡፡ ፈላስፋይቱ የሰው ልጅ በሎጂክ ብቻ መኖር ያለመቻሉንና ከስሜቶቹ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ነገሮች ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚገባው የሚቀርቡ የትኞቹንም ምክንያቶች አትቀበልም፡፡ ይሁንና ስለማይታዩትና ስለማይጨበጡት የሰው ልጆች ሃሳብ አንስታ የምትለግሰውን ምክር ምንነት አንባቢው ራሱ ብይን ይሰጥበት ዘንድ እተወዋለሁ፡፡ ሴቲቱ የምትለው እንዲህ ነው:- ... . . የማይታዩ፣ የማይዳሰሱ፣ የማይጨበጡ ሃሳቦች ላይ ፍላጐት ከሌላችሁ ሀሳቦቹን ለመጠቀም ለምን ተገደዳችሁ? ... ሀቁ ግን እነዚህን የማይታዩና የማይጨበጡ ሀሳቦች፣ በስሌት ሊደረስባቸው የማይቻል  ንሰ ሀሳቦችን በውስጣቸው መያዛቸውና ካለ እነዚህ በግል የሚታዩትን እውነተኛ የህይወት ችግሮች መጋፈጥ ያለመቻላችሁ ነው፡፡ . . . ዕይታችሁን፣ ማስተዋላችሁን፣ ልምዳችሁን፣ ዕውቀታችሁን፣ ከማይታዩና ከማይጨበጡ ሀሳቦች ጋር ይኸውም ከመርህ ጋር ከማጣመር አስፈላጊነት ሌላ አማራ የላችሁም፡፡ ያላችሁ ብቸኛ አማራ እነዚህ መርሆዎች እውነት ወይም ሀሰት መሆናቸውን ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡.. ለእኔ ግን ይሄ አነጋገር የሚያስረዳኝ ..ስለ¤¬WÃnù.. ራሣቸው በስሌታቸው የማይደርሱበት ወይም በስሌት ሊገለ የማይቻል ስውር ምንነት መኖሩን ፈሞ ለመካድ ያለመቻላቸውን ነው፡፡ እኛም አማኞቹ ሳይታይ በውስጣችን ሆኖ የሚመራንን አምላክ ሃሳቦች የምንገልፀው ሊውጠን ዙሪያችንን የሚዞረውን የ..ሃሰት አባት.. wgþD የምንለው በዚሁ እውነት ውሸቱን የማጣሪያ ዘዴ በመጠቀም ነው፡፡ ..በሎጂክ ተደግፈህ ስለ እግዚአብሔር ልታስረዳኝ xTCLM.. ለሚለው  ማሣመኛ ባይሆንም ምክንያታዊ ስልትን መከተል ግን ሰዎች እውነተኛውን አምላክ ይፈልጉት ዘንድ FN ለመስጠት ጠቃሚ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ሥነ - ፍጥረቱ ማንም አጨናብሮ ሊያመልጥ የማያስችለውን እጅግ ምክንያታዊ መረጃዎችን አቅፎ ይዟል፡፡ የመነሻና የውጤት ማስረጃው (Cosmological Argument) ማንኛውም የተፈጠረ ነገር ሁሉ የታወቀ መነሻ እንዳለው ይገልፃል፡፡ የትኛውም ህንፃ የተገነባው በሰው ከሆነ ይልቁንም ዩኒቨርሱ ከዚያ የላቀ መሃንዲስ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህም ፍጥረቱ ጥበበኛ መነሻ፣ ህያው መነሻ፣ ኃይል መነሻ አለው፡፡ ተፈጥሯዊ ሀቁም ሆነ የፈጣሪው እውነትነት ግል ነው፡፡
በንድፋዊ የአወቃቀር ሥርዓቱም የተፈጠረው ዓለም በሥርዓት የተቀናጀና በህግ የሚመራ ነው፡፡ ይህን ንድፍ ደግሞ አንዳች ጠቢብ የነደፈው ካልሆነ በቀር ሰዓሊ በሌለበት ሥዕል ለማየት እንደመናፈቅ ይቆጠራል፡፡ ዶ/ር ጆን ሳውንሰን ግን ይህንኑም እያወቀ ዓይኖቹን ስለሚጨፍነው አላማኝ የሚገልፁት እንዲህ በማለት ነው:- ... . . they see the cause and the effect of the Artist’s Brush Strokes But they can not see the picture Being Painted...
በፍጥረቱ ውስጥ ያለው የስምምነት ህግም ጨለማና ብርሃን፣ ክረምትና በጋ የሚፈራረቁበት ጥበብ፤ ሰውና መሬት፣ ሰውና አየር፣ ሰውና ውሃ፣ የተሳሰሩበትን ተዓምር በማሣየት ይህች ዓለም የመገኛ ምክንያት፣ ደራሲና ባለቤት እንዳላት ይገልፃል፡፡ ስለ እግዚአብሔር መኖር ከሚቀርቡት ማስረጃዎችም ሌላኛው ውስጣዊው የሰው ህሊና (intuitive) ምሥክርነት ነው፡፡ ይኸውም የማንኛውም ሰው ..ውስጥ.. ስለ እግዚአብሐር ማሰቡ ሲሆን ሰውዬው ቢያምንም ባያምንም አምላካዊ ፍለጋውና መሻቱ ሁሉን አቀፍ ነው፡፡ (አየን ራንድ ..በመርህ.. ልትተካው የፈለገችው ምናልባትም እሱን ሃይማኖት ራሱ በታሪክ ውስጥ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ የመሆኑ ምስጢርም ይኸው ነው፡፡ ከሰው ..ውስጥ.. ባንወጣም የሞራል ተጨባጫዊነት (ethical Objectivism) ሌላኛው yእግዚአብሔር ህላዌ አስረጂ ሲሆን ይህም ደግሞ ተፈጥሯዊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው የሞራል ግዴታና ኃላፊነት እንዳለበት ያውቃል፡፡ የሃሳቡን ቀናነትና ጥመት የሚነግረው ሊክደው ወይም ከውስጡ አውጥቶ ሊጥለው የማይቻለው ቋሚ ህግና ዳኛ ሞቶ አፈር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ሲሞግተው ይኖራል፡፡
እንግዲህስ እናንተ የምትንቁ ሆይ ልትቀበሉን ባትፈቅዱም በመጠየቅ የደረስንበት ሀቅ፣ በእምነትም ያረጋገጥነው እውነት ይሄ ነው፡፡ በቀረው ማንም ቢተርክላችሁ በማንነታችሁ ልታምኑት የማይቻላችሁን ልዑል ..ዓይኖቻችሁ.. ተከፍተው አይተውት ትደነቁ ዘንድ፣ የአሳዳጁን ሰው እልከኝነት አስክኖ የራሱ ምሥክር ያደረገው አልፋና ኦሜጋ ይገለጥላችሁ ዘንድ፣ ..ጥበበኛ የታለ? ፀሀፊስ የታለ? የዚህች ዓለም መርማሪስ የታለ? እግዚአብሔር የዚህችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?.. ያለበቱም ምስጢር ይፈታላችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡

 

Read 3194 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 11:54