Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 13 August 2011 11:13

..ቡሄ.. በቶቶት ይከበራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ የቡሄ በአልን ባህልን በጠበቀ መልኩ እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡ በዓሉ ወግና ልማድ ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላችንን እናደርጋለን ያለው ቶቶት፤ የቡሄ አጨፋፈር ትርዒት የሚያቀርብ ሲሆን የሙልሙል ገፀ በረከትም ነሐሴ 13 ቀን 2003 ዓ.ም. እንዳዘጋጀ ገልጿል፡፡ በዝግጅቱ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ደራስያን፣ አትሌቶችና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ኢስላማዊ ኤግዚብሽኑን ከ25 ሺህ ሰው በላይ ጐበኘው
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ተባባሪዎቹ ያዘጋጁትን ኢስላማዊ አውደርእይ መክፈቻውን እና ያለ ትኬት የገቡትን ሳይጨምር ከ25 ሺህ ሰው በላይ እንደጐበኘው አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 1 ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ለቆየው አውደርእይ ከስድስት ክልሎች በተለይ ከአርጐባ፣ ከሚሌ፣ ጅማ፣ ሐረር እና ቀጥበሬ የመጡ ቅርሶች ቀርበውበታል፡፡ የአውደርእይ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፈይዘል ከማል ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረውን ቁርአን ጨምሮ ከሐይማኖት፣ ከሥነ ሕንፃ፣ ከታሪክ፣ ከባህልና ሌሎች ዘውጐች አንፃር የቀረቡትን ቅርሶች በቋሚነት ለማሳየት ታስቧል፡፡ አውደርእዩ የተዘጋጀበትን ዓላማ ጠይቀናቸውም ..የሙስሊሙ እምነት፣ ባህልና ታሪክ እንዲታወቅ ማድረግ.. መሆኑን ገልው የቅርስ ጥበቃው የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድርሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በእስልምና ቅርሶች ላይ ያተኮረ አውደርእይ ሲዘጋጅ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡

 

Read 4934 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 11:19

Latest from