Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 11:08

አዳዲስ መፃህፍት ለንባብ በቁ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በደሳለኝ ስዩም የተዘጋጀው ..የጠረፍ ህልሞች.. ልቦለድ መሐፍ ታትሞ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ 184 ገፆች ያሉት መሐፍ በ25 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በሦስት ሺህ ቅጂ የታተመው መሐፍ በረከትነቱን ለፀሐፊ ተውኔት ጌትነት እንየው አድርጓል፡፡ አዘጋጁ ካሁን ቀደም ..ደም የተፋ ብእር.. የሚል የግጥም መሐፍ ያሳተመ ሲሆን ባሁኑ ወቅት በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በአምደኝነት ይታወቃል፡፡በአካሉ ቢረዳ የተዘጋጁ ሁለት የትርጉም መፃህፍት ሰሞኑን ለንባብ በቅተዋል፡፡

..የቤንጃሚን ፍራንክሊን የህይወት ታሪክ.. የሚለው መሐፍ 218 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋውም 30 ብር ነው፡፡ በብርያን ትሬሲ የተዘጋጀው ..ያለልፋት መቋመጥ ሀብት.. የተሰኘው ሌላው የትርጉም መሐፍ 262 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋውም 34 ብር ነው፡፡መሀመድ ሰልማን “Tadyas Ethiopia” የተሰኘ የልጆች መሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ 70 ገ ያለው መሐፍ ዋጋ 20 ብር ነው፡፡
..አይፈራም ጋሜው እና ፍልስፍናዊ ወጐቹ.. የሚል ሀገርኛ የፍልስፍና መሐፍ በሲሳይ መኳንንት ተዘጋጅቶ ለገበያ ቀርቧል፡፡ በ27 ብር የሚሸው መሐፍ 188 ገፆች አሉት፡፡ቀዳማዊ ሰለሞን የደረሰው ..ቀን.. የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መጽሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ለንባብ በቅቷል፡፡ መሐፉ 345 ገፆች አሉት፡፡ ዋጋውም 50 ብር ነው፡፡

 

Read 6915 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 11:12