በሶሻል ሚዲያ በተጀመረው ዘመቻ ..አይአምጎ ነቢዩር ፍሬንድ.ኦርግ.. በሚል ድረ ገ በ1973 እ.ኤ.አ የተዘፈነው የቦብ ማርሌይና ዘ ዌለርስ ..ሃይ ታይድ ሎው ታይድ.. የተሰኘው ዜማ ከኢንተርኔት ለሚገለብጡ አድማጮች በ1.29 ዶላር የቀረበ ሲሆን በዘመቻው 1 ቢሊዮን የዓለም ህዝቦችን ለማስተባበር ታቅዷል፡፡ በዚሁ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ቢዮንሴ፣ ማዶና፣ ብሪትኒ ስፒርስ፣ ሌዲ ጋጋ፣ ፖል ማካርቲኒ፣ ጀስቲን ቢበርና ሌሎቹም የዓለማችን ምርጥ ሙዚቀኞች እየተሳተፉ ናቸው፡፡ በተያያዘ የቦብ ማርሌይ ቤተሰብ ..ዋን ላቭ.. በተባለው ፋውንዴሽን ..ሰላማዊ፣ ንፁህና የተሟላ የወደፊት ዓለማችንን እንፍጠር.. በሚል መርሁ 100ሺ ዶላር ለኢትዮጵያ እንደለገሰ ታውቋል፡፡ ፋውንዴሽኑ ሰሞኑን በለገሰው የገንዘብ እርዳታ 1300 መንደሮች፤ 12 ክሊኒኮችና 128 ትምህርት ቤቶችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዳሚያደርግ ተገልል፡፡