Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 09:55

የስዩም አሻራ በየመን እግር ኳስ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በየዓመቱ በሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በህጋዊ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ የመን ይሰደዳሉ፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳውዲ አረቢያ የገልፍ አገራት የሚሻገሩ ወይም  በስንዓ፣ በኤደንና እና በሌሎች የየመን ከተሞች የሚኖሩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያውያኑ ኑሮ በየመን የተደላደለ ነው ለማለት ያዳግታል፡፡ ሴቶቹ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሠሩ ናቸው፡፡ በወር ከ150 እስከ 300 ዶላር ያገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ወንዶች ግን ስራ የላቸውም፡፡ በሴቶቹ ገቢ ጥገኛ የሆኑ ወንዶች ቢበዙም አንዳንዶቹ ሙዚቃ ቤት፣ ኤሌክትሮኒክስ መደብር ፣ የገፀበረከት ሱቆች በመክፈት ይነግዳሉ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ሴቶች ከቤት ሰራተኝነት ሌላ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፉርኖ ዱቄት አይን ያለው ነጭ እንጀራ ጋግረው በመሸጥ አትራፊ ንግድ ይዘዋል፡፡ የመናውያን በስንዴ ፉርኖ ዱቄት የሚጋገረው ይህን የኢትዮጵያ ሴቶች እንጀራ ወደውታል፡፡ በፆም ወቅቶች ይህን እንጀራ የሚሸጡ ሴቶች በወር ከወጭ ቀሪ ከ2500 እስከ 3ሺ ዶላር ያገኙበታል፡፡

በየመን ከተሞች የየትኛውም አገር ዜጋ ያለመታወቂያ ሠርቶም ሆነ ቦዘኔ ሆኖ መኖር ይችላል፡፡  ባለፉት 6 ዓመታት ደግሞ ለኢትዮጵያውያኑ ወደ የመን መፍለስ ምክንያት የሆነው እግር ኳስ ነው፡፡ በጣት የሚቆጠሩ አሰልጣኞችና ከ12 በላይ ተጨዋቾች ወደ የመን ሄደው በዋናው ሊግና በሁለተኛ ዲቪዚዮን በሚወዳደሩ ክለቦች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የነበረውና በጊዮርጊስና አዳማ ክለቦች አሰልጣኝ ሆኖ የሠራው ስዩም ከበደ ይገኝበታል፡፡ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በቅ/ጊዮርጊስ በወጣትና ዋና ቡድኖች ለ13 ዓመታት ሠርቷል፡፡ ወጣት ቡድኑን በማሰልጠን 10 ዓመት የሠራ ሲሆን ዋናውን የቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ለ3 ዓመት አሰልጥኖ በ2ቱ የሊጉ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ ስፖርት አድማስ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ bኢትዮጵያውያን የየመን እግር ኳስ ገድልና ተያያዥ ጉዳዮች ተጨዋውቷል፡፡  በየመን እግር ኳስ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ክረምቱን ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡ lMN?
ወደ አገር ቤት የተመለስነው የየመን ሊግ ውድድር bmÌrºå ነው፡፡ በአሰልጣኝነት የምመራው አልቲላል ሊጉ ሊገባደድ 4 ጨዋታ እየቀረው ከመሪዎቹ ተርታ ነበር፡፡ በየመን ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በውድድሮች ሳቢያ በተፈጠሩ የተለያዩ ችግሮች ፌደሬሽኑ  ሊጉን ለማቋረጥ ተገድዷል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሁላችን ወደ አገር ተመልሰናል፡፡ ፌደሬሽኑ የተቋረጠውን ውድድር ካልተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡ በደቡብ የመን ሁለት ወይም ሶስት  ክለቦች የመንግስት ተቃዋሚዎችን በመደገፍ ከውድድሩ ራሳቸውን በማግለላቸው ሊጉን ማካሄድ አልተቻለም፡፡ በተቋረጠው ሊግ እኔ የማሰለጥነው ክለብ የውድድር ዘመኑን በ2ኛ ደረጃ ጨርሷል ማለት ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች በአልቲላል፤ በአልሳከር በአልዋዳድ በዋናው ሊግ እንዲሁም በሁለተኛው ዲቪዚዮን በሚወዳደሩ ክለቦች ይገኛሉ፡፡ ዘንድሮ ከ10  በላይ ተጨዋቾች በየክለቡ ነበሩ ብዬ እገምታለሁ፡፡ 3 ያህል አሰልጣኞችም በስራ ላይ ነበርን፡፡
ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞችና ተጨዋቾች በየመን እንዲሰሩ ማን ፈር qdd? የመፈለጋቸው MKNÃTS?
ወደየመን እግር ኳስ የመጀመሪያ ፈር ቀዳጅ ሆኖ የሄደው የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ተጨዋች የነበረው አንዋር ያሲን ወይም አንዋር (ትልቁ) ነው፡፡ ከ6 ዓመታት በፊት አንዋር የገባበት ክለብ አልሳከር የተባለው ነው፡፡ በዚያ ክለብ መጫወት ሲጀምር በነበረው ጥበብ የሞላበት የኳስ ክህሎት አድናቆት አግኝቶ አሳልፏል፡፡ ይህ የአንዋር ስኬት የመናዊያን የክለብ አመራሮችን ፍላጐት ያነሳሳ  ነበር፡፡ አንዋር (ትልቁ) በአልሳከር ክለብ መጫወት ሲጀመር ግብፃዊያን፣ ናይጀሪያውያን፣ ኢራቃውያን ተጨዋቾች በየክለቡ ነበሩ፡፡ ከእነሱ የቴክኒክ ችሎታ የአንዋር የላቀ ብልጫ ነበረው፡፡
አንዋር በከፈተው መንገድ ዮርዳኖስ አባይ፣ አንዋር ሲራጅ  ..ትንሹ.. እና ባዩ ሙሉ ብርሃኑ ቃሲምና ታፈሰ ተስፋዬ ወደ የመን ሊግ ከተቀላቀሉ ኢትዮጵያውያን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች አስተዋጽኦ ለየክለቡ አስተዳደሮች በሚያቀርቡት ሃሳብ የየመን ክለቦች ወደ ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ፊታቸውን ማዞር ጀመሩ፡፡ እኔም አንዋር ትልቁና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች በሰጡት ምክር የአልሳከር ክለብን እንዳሰለጥን ተጠይቄ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ በየመን ሊግ የሚሰራበት ዕድሉ ተፈጠረ፡፡ በወቅቱ አሰለጥን ከነበረው አዳማ ክለብ ለቅቄ በአዲስ የውድድር ዘመን መድንን ለመያዝ ከጫፍ ደርሼ ነበረ፡፡ የየመኑ ዕድል ሲመጣ ያለማመንታት  አልሳከር ክለብን ለማሰልጠን ወሰንኩ፡፡ የ37 ዓመታት ታሪክ የነበረው አልሳከር በርካታ አሰልጣኞችን ከተለያዩ አገራት በማስመጣት ቢሠራም እንደነበረው የሀብት አቅም በዋንጫ ድል ውጤታማ ሊሆን ያልቻለበት ጊዜ ነበር፡፡
ወደ ክለቡ በገባሁበት የመጀመሪያ ዓመት አልሳከር ከምስረታው 37 ዓመታት በኋላ የየመን ሊግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮናነነት አጠናቀቀ፡፡ እኔ በአሰልጣኝነት፣ በተጨዋችነት ደግሞ አንዋር ሲራጅ ፣ ባዩ ሙሉና፣ ዮርዳኖስ አባይ ነበሩ፡፡ አልሳከር ክለብ እጅግ ሃብታም በሆኑ ባለቤትነትና የበላይ ጠባቂነት የሚተዳደር ነው፡፡ እኝህ የክለቡ ባለቤት አልታሂድ የተባለ ኩባንያ ባለቤት ናቸው፡፡ ይህ ኩባንያ በአሜሪካ፣ በኤስያና በአረቡ ዓለም  የተስፋፋ ኢንቨስትመንት ያለው ነው፡፡ የሰውየው አባት ደግሞ የአቡ ወለድ ብስኩትን የሚያመርት ፋብሪካ በመመስረት ለኩባንያው መሰረቱን የጣሉ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ አልኢትሃድ ለብዙ የመናዊያን የስራ እድል የሰጠ  ኩባንያ ነው፡፡ የአልሳከር ክለብ በእዚህ ዓለም አቀፍ ኩባንያ የሚተዳደር በመሆኑ በተሟላ የፋይናንስ አቅም የተደገፈ አደረጃጀት አለው፡፡ ክለቡ ስታድዬም፣ ካምፕ፣ ጂምናዚየምና የተሟላ መሠረት ልማት ይዟል፡፡ የእግር ኳስ ክለቡ በሊጉ ውድድር ሻምፒዮናነቱ ምንም የሚያገኘው ጥቅም የለም፡፡ ስታድዬም እንኳን የሚገባው በነፃ ነው፡፡ የክለቡ ባለቤቶች ስፖርቱን መደገፍ እንደ ዝንባሌ የያዙት እንጂ ከክለቡ የሚያገኙት ሆነ የሚፈልጉት ጥቅም ኖሮ አይደለም፡፡
በየመን ሊግ ከኢትዮጰያውያን አሰልጣኞች የመጀመርያው አንተ ነህ፡፡ ሌሎቹ አሰልጣኞች እነማን ናቸው?
በየመን እግር ኳስ የምትሸነፍ ሰው ከሆንክ ያለህ ክብርና ዝና ሰማይ ይነካል፡፡ ስትሸነፍ ግን የዚያኑ ያህል መሬት ትወርዳለህ፡፡ እኔ በየመን እግር ኳስ ስራ ስጀምር ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ ምን ይዞ? ከየት መጣ? በሚል ብዙ አፍራሽ አስተያየቶች ነበሩ፡፡ በአልሳከር ዋና አሰልጣኝነት መስራት በጀመርኩበት የመጀመርያው ዓመት ክለቡን ሻምፒዮን ሳደርገውና የውድድር ዘመኑ ኮከብ አሰልጣኝ ተብዬ ስሸለም ግን ሁሉም የየመን ክለቦች bኢትዮጵያውያን ላይ የነበራቸው ጥርጣሬ ተገፈፈ፡፡
ከእኔ በኋላ ወደ ሌላው የየመን ክለብ አልሂላል በመጓዝ ስራ የጀመረው አብርሃም መብራቱ ነበረ፡፡  አብርሃም የሚያሰለጥነው አልሂላል ክለብ ንብረትነቱ አሁን የየመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ግለሰብ ነው ፡፡ እኝህ የየመን እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት በነዳጅ ንግድና በመርከብ ትራንስፖርት በዓለም ታዋቂ ኩባንያን የሚመሩ ናቸው፡፡ አብርሃም መብራቱ በአልሂላል መስራት በጀመረበት የመጀመርያ ዓመቱ  ክለቡን በሊጉ 4ኛ ደረጃ ይዞ እንዲጨርስ አድርጐ ስኬታማ ሆነ፡፡  በዚህ ስኬቱም ከፍተኛ እውቅና አግኝቶ አሁን በየመን እግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ክፍል ውስጥ እየሰራ ከመሆኑም በላይ የየመን ኦሎምፒክ ቡድንም ዋና አሰልጣኝ ነው፡፡ ከአብርሃም በኋላ ሰውነት ቢሻው፣ ወርቁ ደርገባ፣ ገ/መድህን ኃይሌ እና ሌሎችም  የየመንን እግር ኳስ ተቀላቅለዋል፡፡ yኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ብቃትንም ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ሰውነት ቢሻው በየመን ሊግ  ደጋግሞ ሻምፒዮን የሆነው ትልቁ ክለብ አልኢሴና ዋና አሰልጣኝ ነበር፡፡ ወርቁ ደርገባም በዘንድሮው የውድድር ዘመን አልዋሃዳድ የተባለ ክለብ ይዞ ነበር፡፡
በየክለቡ ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ሲሰሩ ችግሮች ነበሩ፡፡ አብዛኛዎቹ ክለቦች በሃብታሞች ቢረዱም ይህን የፋይናንስ አቅም ለስራቸው ስኬት እንደፈለጉት ማዋል ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ባለሀብቶቹ ክለባቸውን ለማጠናከር የሚመድቡትን በጀት የአስተዳደር ሠራተኞች በአግባቡ ወደ ታች አውርደው የሚሠሩበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ክለቦች በእነዚህ ብልሹ አመራሮች ሃብታቸው ይመዘብራል፡፡ ይህም ለኢትዮጵያውያኑ አሰልጣኞች ባስፈለገ መጠን ስኬታማ ተግባር እንዳያከናውኑ እንቅፋት ሆኗል፡፡ አንዳንዴ እንደውም በየክለቡ በነበረው ብልሹ አስተዳደርም ደሞዝ ሁለትና ሦስት ወር ይዘገይባቸው ነበር፡፡ በዚህም ሁሉም አሰልጣኞች ደስተኞች አልነበሩም፡፡
ከ5 ዓመት በፊት የአልሳከር ክለብን በዋና አሰልጣኝነት ሻምፒዮን በማድረግ ስራህን ከጀመርክ በኋላ በየትኞቹ የየመን ክለቦች ሰርተሃል?
በአልሳከር ክለብ የመን ከገባሁ በመጀመርያ ዓመቴ ሻምፒዮን ሆንኩ፡፡ ከዚያ በኋላ በ2ኛው ዓመቴ በሊጉ በ3ኛ ደረጃ አጠናቀቅኩ፡፡ በየመን ሊግ በ3ኛ ደረጃ ባጣናቀቅን ማግስት የክለቡ አመራሮች የውሌን ኮንትራት ማደስ ቢኖርባቸውም ፍላጐት ሳያሳዩ ቀሩ፡፡ ይባስ ብለው ለእኔ ሳይገልፁ ሌላ ግብጻዊ አሰልጣኝ ወደ ክለቡ አመጡ፡፡ ይህም አበሳጨኝ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በአልሳከር ክለብ እየሠራሁ በነበረ ግዜና ክለቡን መልቀቄ ከተሰማ በኋላ በዚያ ከተማ የነበረው የአልኢትሂድ ክለብ በእኔ ላይ ፍላጐት ስለነበረው የዝውውር ሃሳብ አቀረበልኝ፡፡ አልኢትሃድ በሰንዓ ከተማ አንጋፋ የሆነ በርካታ ደጋፊ  ያለው ክለብ ሲሆን በወቅቱ  በ2ኛ ዲቪዚዮን ሲጫወት  ነበር፡፡ የእኔ ቅጥር ይህን ክለብ ወደ ዋናው የሊግ ውድድር ለማሳደግ ታስቦ ነበር፡፡ አልኢትሃድን ለማሰልጠን የወሰንኩት በአልሳከር ክለብ የሁለት ዓመት ቆይታዬ መጨረሻ በክለቡ አመራሮች ተገፍቼ የነበረበትን ሁኔታ ለመበቀል በተነሳሳሁበት ሞራል እንጅ የተሻለ ክፍያ በማግኘቴ አልነበረም፡፡ ስራዬን ስጀምር በ2ሺ ዶላር ወርሃዊ ደሞዝ ነበር፡፡ በመጀመሪያው ዓመቴ የአልኢትሂድን ክለብ ከ2ኛ ዲቪዚዮን ወደ ዋናው የሊግ ውድድር እንዲያድግ አስቻልኩ፡፡ ወደ አንደኛ ዲቨዚዮን ከገባን በኋላ በሁለተኛው ዓመት የአልኢትሃድ ክለብ አሰልጣኝነቴ ስቀጥል ሊጉን በ4ኛ ደረጃ ጨርሰን ቡድኑ የዓመቱ ምርጥ ተብሎ ነበር፡፡ በአልሳከር የነበረውን የምርጥ ቡድን ስራና አጨዋወት ነው አልኢትሃድ የወረሰው፡፡ በዚሁ የአልኢትሃድ ክለብ እየሰራሁ  በሁለተኛው ዓመቴ ላይ አልቲላል በተባለ ክለብ ያሉ የበላይ ሃላፊዎች የዝውውር ፍላጎታቸውን በመግለ በይፋ ጥያቄ ያቀርቡልኝ ጀመር፡፡ የአልቲላል ክለብ አመራሮች ለዝውውሬ ጥሪ ሲያቀርቡ ወርሃዊ ደሞዝ እስከ 4ሺ ዶላር በፊርማ ክፍያ ደግሞ 13ሺ ዶላር እንደሚከፍሉኝ በይፋ ተናግረው ነው፡፡ በዚሁ ክለብ የኢትዮጵያ ቡናና የመብራት ሃይል ክለቦች ተጨዋች የነበረው ለሚ ኢታና ሲጫወት ሁለተኛ ዓመቱን ይዞ ነበር፡፡ እኔ ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት መመራት ከጀመርኩ በኋላ ደግሞ ሌላውን የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ታፈሰ ተስፋዬን xSfrMkùT፡፡ የአልቲላል ክለብ የበላይ ሃላፊዎች የየመን ፕሬዝዳንት ቀኝ እጆች የነበሩና ወንድማቸውም ክለቡን በፕሬዝዳንትነት ይመራ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ከአገሪቱ አጠቃላይ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ  በክለቡ የመጀመርያ ዓመት ቆይታዬን ምቹ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡ የየመን ፕሬዝዳንትና ደጋፊዎቻቸው በክለቡ የነበራቸውን ትኩረት በመቀነሱ በአልቲላል ለነበርን ኢትዮጵያውያኖች የተሳካ ዓመት እንዳናሳልፍ ምክንያትም ነበር፡፡ በአገሪቱ ያለው የፖለቲካ ችግር አመራሮችን ከስፖርቱ እያራቃቸው በመምጣቱ በፋይናንስ ድጋፍ የተፈጠሩ ችግሮች ነበሩ፡፡ በተለይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን የደሞዝና ሌሎች የማበረታቻ ክፍያዎችን በወቅቱና በሚገባን መጠን ሳናገኝ tgù§LtÂL፡፡ ደሞዝ እንኳን ሁለት ወር እያለፈ ነበር ሲከፈለን የነበረው፡፡ ሆኖም ግን ያሉ ችግሮች በአልቲላል ክለብ ለየመን እግር ኳስ አዲስ ታሪክ ያስመዘገብኩበትን አጋጣሚ x§sÂklWM፡፡ ክለቡ ከዓመት በፊት በፕሬዝዳንቱ የተሰየመ የጥሎ ማለፍ ውድድር አሸንፎ  በኤስያ በሚከናወን የኮንፌደሬሽን ውድድር ተሳትፎ ነበረው፡፡ በዚህ በአህጉራዊ ውድድር በዋና አሰልጣኝነት ቡድኑን እየመራሁ ሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ አልናስር የተባለውን የዚያን አገር ክለብ 2ለ0 በማሸነፍ አስደናቂ ስኬት ተመዘገበ፡፡ በኢንተርናሽናል ውድድር አንድ የየመን ክለብ ከአገር ውጪ አሸንፎ ስለማያውቅ በእኔ ዋና አሰልጣኝነት አልቲላል በሊባኖስ ክለብ ላይ ከሜዳው ውጪ  ባስመዘገበው ድል በየመን እግር ኳስ አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል፡፡
በየመን ሊግ የደሞዝና የፊርማ ክፍያ ሌሎችም ጥቅማጥቅሞች እንዴት ነው
ተጨዋቾችም ሆነ አሰልጣኞች ከገንዘብ ጥቅም አኳያ ብዙ አግኝተናል፡፡ ክለቦቹን ስንቀላቀል ደሞዛችንና የፊርማ ክፍያው በኢትዮጵያ ከምናገኘው ገቢ በብዙ ዕጥፍ የላቀ ነበር፡፡ የዛሬ 5 ዓመት እኔ አልሳከርን በአሰልጣኝነት ስቀላቀል ወርሃዊ ደሞዜ 1500 ዶላር ሲሆን ለፊርማ የተከፈለኝ ደግሞ 7ሺ ዶላር ነበር፡፡ የተጨዋቾች ደሞዝ ደግሞ ከ1200 ዶላር ጀምሮ ነው፡፡ ክለቦች ለተጨዋቾችና ለአሰልጣኞች የተሟላ የቤት እቃ ያለው አፓርታማ የምግብና ሌሎች የአበል ክፍያዎችን ይፈማሉ፡፡ የሚታሰብልን የጉርሻ ክፍያም የሚያነቃቃ ነበር፡፡ የጉርሻ ክፍያው በአሰራሩ ተጨዋቾች ባንድ ጨዋታ ሲያሸንፉ 100 ዶላር ሲያገኙ እኔ አሰልጣኝ በመሆኔ ሁለት መቶ ዶላር ቦነስ እየተከፈለ የተጀመረ ነበር፡፡ ይህ ጉርሻ በሁለተኛው ተከታይ ጨዋታ ስናሸንፍ የተጨዋቾች 150 ዶላር የአሰልጣኝ 300 ደረሰ፡፡ በዚህ አሰራር ብዙ ጨዋታዎችን ማሸነፍ እንደሚቻል የክለቡ አስተዳደር  ስላመነበት አጣናክሮ ሠርቶበታል፡፡ ይሄው የጉርሻ ቀመር አንድ ወቅት በአንድ ጨዋታ ድል ለተጨዋቾች 900 ዶላር ለእኔ 1800 ዶላር ሊደርስ ችሏል፡፡ የጉርሻ አሰጣጡ የክለቡን ሰርዓትና ደንብ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ከዲሲፒሊን፣ ከአለባበስ ከስልጠና ጥንካሬ ጋር ተያይዞ የወጣ ነበር፡፡
በየመን ያለው የእግር ኳስ እንቅስቃሴና አጠቃላይ የሊግ ውድድሩ ምን አይነት ገታ አለው?
ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ያለን ሰዎች ወደ የመን ሄደን በአሰልጣኝነትና በተጨዋችነት ተሳትፎ አድርገን ቆይተናል፡፡ ከመካከላችን በዚህ ልምድ የተሳካለት አለ ያልተሳካለትም አለ፡፡ በአገሪቱ እግር ኳስ በተለይ የሊጉ ውድድር ጠንካራ ነው፡፡ ሁሉም የየመን ክለቦች በሜዳቸው በሚያደርጉት ግጥሚያ በቀላሉ የሚሸነፉና ውጤት የሚያጡ አይደሉም፡፡ ክለቦች የራሳቸው ስታድዬም ያላቸው በባለቤትነት የሚያስተዳድሯቸው ባለሀብቶች የተደገፉ ናቸው፡፡ ሊጉ በመጠናከሩ ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን እያሳደገ ነው፡፡ የየመን ሊግ እያደገ የሚሄድ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ያለበት ነው፡፡ በሊጉ ካሉ  ክለቦች 7 እና 8 የሚሆኑት የራሳቸው አርቲፊሻል ሜዳ አላቸው፡፡ የተሟላ ካምፕ፣ ጅምናዚዬም እና የፋይናንስ አቅም በመያዝም ተደራጅተዋል፡፡ በየክለቦቹ ከናይጀሬያ፣ ከግብጽ፣ ከካሜሮን፣ ከኮንጎ፣ ከኢራቅ በአ-ቃላይ ከ8 በላይ አገራት ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ተሰባስበዋል፡፡ ክለቦቹ ስታድዬም  እንዲኖራቸውና ያስቻለውና በከፍተኛ ድጋፍ እንዲገነቡ ያደረገው የአገሪቱ መንግስት ነው፡፡ መንግስት ስፖርቱን ለመደገፍና ለማሳደግ ብሎ ስታድዬሞቹን ገንብቷል፡፡ የሊጉ ጥንካሬ የአገሪቱን ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተፎካካሪ እያደረገው ይገኛል፡፡ የታዳጊና የወጣት ብሔራዊ ቡድኖች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ጠንክረዋል፡፡ መንግስት በሰጠው ትኩረት እነዚህ የወጣትና ታዳጊ ቡድኖች በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ይሳተፋሉ፡፡ ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች ከየትኛው ጨዋታ በፊት ቢያንስ የ3 ወር ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ወደ ግብጽ፣ ሆላንድና ሌሎች አገራት በመጓዝ ካምፕ መስርተው ረዘም ያለ ዝግጅትንም ያከናውናሉ፡፡ ሌላው ልዩ የዝግጅታቸው ባህርይ በርካታ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ማድረጋቸው ነው፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንድ ዓለም አቀፍ ጨዋታ በፊት እስከ 8 የወዳጅነት ጨዋታዎች ሊያደርግ ይችላል፡፡
በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከሌሎች አገራት ጋር ፌደሬሽኖች ጋር በተለያዩ ዘርፎች ተቀራርበው መስራታቸው ነው፡፡ ለአሰልጣኞች በየጊዜው የሙያና የብቃት ማሻሻያ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት የተለመደ ሥራ ነው፡፡
በአጣቃላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስን በተመለከተ የምትሰጠው አስተያየት ምንድነው
የኢትዮጵያ እግር ኳስን በቴሌቭዠን ስርጭት በሚተላለፉ ፕሮግራሞችና ዜናዎች እንከታተላለን፡፡ ክለቦች በተለይ ዘንድሮ በሊጉ ያሳዩት ጠንካራ ፉክክር ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ክለቦች እግር ኳሱን ለማሳደግ ከፈለጉ ታዳጊና ወጣት ቡድኖችን ይዘው መስራት ÃSfLUcêL፡፡ ይህ  በግዴታ ሁሉም እንዲተገብረው ካልሆነ በየክለቡም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ተተኪ ሆነው በብቃት የሚጫወቱ ልጆችን ላናገኝ እንችላለን፡፡ ሞያተኞች መቀራረባቸው ለአንድ ዓላማ መስራታቸውና በየሙያቸው ለውጥ ለማስመዝገብ መትጋታቸውም አስፈላጊ ነው፡፡ ደደቢት፤ ሲዳማ እና አሁን ወደ ነበረበት የተመለሰው አርባምንጭ ሊጉን እያሳመሩ ያሉ አዳዲስ ጠንካራ ክለቦች ናቸው፡፡ ክለቦች ምርጥ ስፖርተኞችን ለማግኘት በእኩል ደረጃና አቅም የላቸውም፡፡ ለዚህም መፍትሔ ያስፈልጋል፡፡ ሃብታሞች ወደ ስፖርቱ መጥተው ሙሉ ለሙሉ ኢንቨስት ያደርጋሉ ብሎ ለማሰብም ይከብዳል፡፡ ስለዚህ የከተማ መስተዳድሮችና ከነማዎች የሚወክሏቸውን ክለቦች በስፋት መደገፍ አለባቸው፡፡ ክለቦች ስታድዬም ÃSfLUcêL፡፡ ይህን ተግባራዊ ማድረግ ከባድ እየመሰለን የስፖርት ማዘውተርያም መጥፋቱ ደግሞ ያሳስበኛል፡፡ ክለቦች ወደ ህዝባዊነት ይለወጡ በሚል የሚሰማው ነገርም ጨልሞ ነው የሚታየኝ አሁን ክለቦችን የሚያስተዳድሩ የመንግስት ተቋማትና ድርጅቶች ህዝባዊነት በሚል መርህ እንዲርቁ ማድረግ አደጋ ነው፡፡ እነ አየር መንገድ፤ እነ ጉምሩክ፤ እነ ጭማድ የሚያስተዳድሯቸው አካላት ሲርቋቸው ነው ከስመው የቀሩት፡፡ የክለቦች ህዝባዊነት አሁን ካለው የመንግሥት ድጋፍ ጋር በተጓዳኝ ይሂድ ብዬ ነው የምመክረው፡፡
?መጨረሻM አሁን ያተኮርኩበት ትልቁ ዓላማዬን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ በስልጠና የምከተለውን የራሴን ተግባራዊ ፍልስፍናና ፈጠራ ለሌሎች እንዴት ላካፍል እችላለሁ ብዬ የሰራሁት ነው፡፡ ይህን የሙያዬን ተሞክሮና የስልጠና ፍልስፍናዬን ካለኝ የስራ ልምድ ጋር በማዋሃድ በሲዲ xzUJc½êlhù፡፡ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች ለማዳረስም ጥረት እያደረግኩ ነው፡፡

 

Read 4991 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:59