Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 09:50

ሴቶችዓለምን እየመሩነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታዋቂዋየሆሊውድየኮሜዲፊልምአክትረስና ረስናበዛሬውጊዜላሉትበርካታእንስትተዋንያንሞዴልበመሆንየምትታወቀውማርሊንሞንሮ፣ከዛሬ40ዓመት    በፊት እንዲህ ብላ ነበር፣ ..ዓለም የወንዶች ናት፤ ሆሊውድ ደግሞ የበለጠ በወንዶች ቁጥጥር ስር ነው.. ነገር ግን ማርሊን ሞንሮ እ.ኤ.አ በ1962 ዓ.ም ከሞተች በኋላ በአሜሪካ ሴቶች መብታቸውንና እኩልነታቸውን ለማግኘት በተለያየ ጊዜያት ባካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ለውጦች ተከስተዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ1970 ወዲህ በአሜሪካ ሴቶች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ከመሳተፍ አልፈው አልፎ አልፎ በአመራር ደረጃ መቀመጥ የጀመሩ ሲሆን፣ በተለይም ከሬጋን ዘመን በኋላ በርካታ ሴቶች የምክር ቤት እና የሴኔት አባል እየሆኑ መጥተዋል፡፡ በተለያዩ ስቴቶች ውስጥም ገዢ እስከመሆን ለመድረስ የቻሉ አልጠፉም፡፡
በቢል ክሊንተን የአስተዳደር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆንም ማድሊን ኦልብራይት ተሾሙ፡፡ ኦልብራይት የፖለቲካ አመራር ብቃታቸውንና ጥሩ ዲፕሎማትነታቸውን ማስመስከራቸው ይታወሳል፡፡ በቡሽ ትንሹ (Junior Bush) ዘመንም ቢሆን፣ ሴቶች በተለያየ የፖለቲካ ኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን በወንዶች ብቻ ተይዞ የቆየውን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ ጃኔት ሬኖ የተባሉ ሴት ተክተው እንዳገለገሉ ይታወቃል፡፡
በተለይም ጆርጅ ቡሽ ስልጣን እንደያዙ በአሜሪካ ሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበሩት ፕሮፌሰር ኮንዶሊዛ ራይስን ቡሽ ለከፍተኛ አመራር እንዳጩዋቸው በመግለ፣ ከሚያስተምሩበት ዩኒቨርሲቲ ለቀው እንዲመጡ ጥሪ ሲያቀርቡላቸው ኮንዶሊዛም ጥሪውን በመቀበል በአሜሪካ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ (National Security Adviser) በመሆን ተሾሙ፡፡ በሁለተኛ የቡሽ አስተዳደር ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ከማድሊን ኦልብራይት ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት ሆነዋል - ኮንዶሊዛ ራይስ፡፡
ኮንዶሊዛ ራይስ በተሾሙ በአመታቸው አልቃይዳ በኒውዮርክ መንታ ሕንፃዎች ላይ የሽብር ድርጊት በመፈፀም ከ3000 በላይ ዜጐችን መፍጀቱ ይታወሳል፡፡
አልቃይዳንና መሪውን ቢላደንን ካሉበት ቦታ የማደን ስራ በፔንታጐን ባለስልጣናት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተመረዘ ቢሆንም ፕሮፌሰር ኮንዶሊዛ ራይስ እንደ ፀጥታ አማካሪነታቸው በአልቃይዳ ላይ ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ዙሪያ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ኑ በሆነው አቋማቸው የሚታወቁት የምክር ቤት አባላት ሳይቀሩ ያከብሯቸውም ነበር፡፡ በተለይም በጣም የሚቀርቧቸው የሪፐብሊካን አባላት ኮንዲ እያሉ ያቆላምጧቸው ነበር፡፡ ኮንዶሊዛ ራይስ እጅግ በሳል የሆነ የፖለቲካ እውቀት ብቻ ሳይሆን ወታደራዊ ክህሎትም እንዳላቸው አሜሪካ በአፍጋኒስታን  የነበረውን አልቃይዳን ለመደምሰስ በወሰደችው እርምጃ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት አሳውቀዋል፡፡ ኮንዶሊዛ በዚህና በሌሎች ብቃታቸው የተነሳ ወራሪዋ እመቤት የሚል ስያሜ አትርፈዋል፡፡ ኮንዶሊዛ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ናቸው፡፡
በወንዶች ብቻ ተይዞ የቆየው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤም ቢሆን በሴቶች ከመደፈር አልዳነም፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ናንሲ ፒሎሲ የተባሉት ሴት ወ/ሮ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ተሹመዋል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ለሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካንን በመወከል ኦባማን ሊገዳደሩ ይችላሉ ከተባሉት ውስጥ ሳራ ፓሊን አንዷ ናቸው፡፡ ሳራ ፓሊን ምንም እንኳን ባለፈው ምርጫ የጆን ማኬይን ምክትል በመሆን ባይሳካላቸውም በአሁኑ ምርጫ ግን ብዙ ለውጥ ማድረጋቸውን ይገልፃሉ፡፡
ከአሜሪካ ውጪም ቢሆን ሴቶች በከፍተኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መስኮች ውስጥ የመሪነት ሚና በመጫወት ስማቸው ይጠቀሳል፡፡ ለምሳሌ በፓኪስታን እ.ኤ.አ ከ1988 እስከ 1996 በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ወ/ሮ ቤናዚር ቡቶ ናቸው፡፡ ቤናዚር ቡቶ በስልጣን ዘመናቸው፣ ያሳዩት የፖለቲካ አመራር ስኬታማ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም በእስላማዊ ንፈኝነት ከምዕራቡ ዓለም ጋር ሆድና ጀርባ የነበረችውን አገራቸውን ከምዕራባዊያን ጋር በማቀራረብ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ቤናዚር ቡቶ በዓለም የሚገኙ ሴቶች ከወንዶች እኩል መብት ሊኖራቸው እንደሚገባ አጥብቀው ይገልፁ ነበር፡፡ ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ አክራሪ እስልምና ተከታይ የሆኑት ናዋዝ ሸሪፊ ስልጣን ሲይዙ፣ ቡቶ በናዋዝ ሸሪፊ አስተዳደር የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያ በመፍራት ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ የናዋዝ ሸሪፍ አስተዳደር ከተወገደ በኋላ በወቅቱ አገራቸው በምታካሂደው ምርጫ ለመሳተፍ ከ8 ዓመት በኋላ ወደ ፓኪስታን ተመለሱ፡፡ ሚስስ ቡቶ በፓኪስታን የተንሰራፋውን የፖለቲካ አለመረጋጋትና አክራሪነት በማስወገድ ነፃ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚጥሩ በመግለ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ሳለ በአንድ አጥፍቶ ጠፊ ህይወታቸው በአሳዛኝ ሁኔታ ማለፉ ይታወሳል፡፡
እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ 11 ሴቶች በተለያዩ የእስያ አገራት በጠቅላይ ሚኒስትርነትና በፕሬዝዳንትነት አገራቸውን መርተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በጣም ከፍተኛ የእስልምና ተከታይ ያለባት ኢንዶኔዥያን ከ2001 እስከ 2004 ድረስ የመሩት ሜጋ ዋቲ ይጠቀሳሉ፡፡ በባንግላዲሽ ደግሞ ካሊዳዚየ በአገሪቱ ታዋቂ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የነበሩ ሲሆን፣ ኋላ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተሹመዋል፡፡ ቻንዲሪካ ኩማራቱንጋ በሲሪላንካ፣ ግሎሪያ በፊሊፒንስ፣ አንግሳን ሱኪ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የበርማ የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እና ሌሎችም በርካታ ሴቶች በተለያየ ጊዜያት በእስያ መርተዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የዓለም የሴቶች ኮንፍረንስ ላይ ፓትሪሺያ ሲሲያኖ የተባሉ የፊሊፒንስ ሴት ምሁር ሲናገሩ፣ ..ሴቶች፣ በፖለቲካ ውስጥ እንዲሳተፉ ስንፈልግ በወንዶች የሚመራውን የፖለቲካ አካሄድ ይዘው እንዲዘልቁ ሳይሆን አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና አመራርን እንዲያመጡ ነው.. በማለት ገልፀው ነበር፡፡
ሮገር ኪንግ የተባሉ በሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ የፋሚሊ ስተዲስ ጥናት ባልደረባ ስለ እስያ ሴቶች በሰጡት አስያየት፤ ..እስያ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ውሳኔ በመስጠት ይታወቃሉ፡፡ በመሆኑም በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ ሴቶች በመሪነት ቦታ ላይ ይገኛሉ.. ብለዋል፡፡ ሮገር ኪንግ ሲቀጥሉ፣ ይህም የሆነበት ምክንያት የእስያ ሴቶች ለወላጅ አባታቸው ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያላቸው በመሆኑ፣ የአባታቸውን ስም ላለማስነቀፍ ይጠነቀቃሉ፤ ስለዚህም ውሳኔ አሰጣጣቸው ከወንዶች የተሻለ ነው፡፡
ለምሳሌ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የበርማዋ አንግሳሱ ኪ አባታቸው በፖለቲካ ምክንያት ሲገደሉ እርሳቸው ገና የ2 ዓመት ሕፃን ነበሩ፡፡ ነገር ግን አንግሳሱ ኪ ሲያድጉ የአባታቸውን ፈለግ በመከተል በበርማ የዲሞክራሲ አስተዳደር ለማምጣት ቆርጠው ተነሱ፡፡ ስለ አባታቸው አብዮተኝነትም መሐፍ ፈዋል፡፡ ቤናዚር ቡቶም ቢሆኑ ወደ ፖለቲካው በመግባት ፓኪስታንን የሚያክል በአክራሪዎችና በንፈኞች የተሞላን አገር ለመምራት ቆርጠው የተነሱት ለአባታቸው በነበራቸው ክብር ነበር፡፡ ፓኪስታንን ሲመሩ የነበሩት አባታቸው ዙሊፊቃር አሊ ቡቶ መገደላቸው ፍትሃዊ አይደለም በማለት የተቃወሙት ቡቶ፤ ኋላ ላይ በፓኪስታን ትክክለኛ ፍትህን ለማረጋገጥ በሚል ኑ ፍላጐታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር እስከመሆን ደርሰዋል፡፡
የፈረንሳይ ቢዝነስ ስኩል ፕሮፌሰር የሆኑት ክርስቲያን ኮሎንዴል በበኩላቸው፤ ..ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለነገሮች ትኩረት ስለሚሰጡ የአመራር ብቃታቸው ውጤታማ ነው.. ይላሉ፡፡
በቻይናም ቢሆን ሴቶች በከፍተኛ አመራር ላይ በስፋት ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በቻይና ፓርላማ ውስጥ የሴቶች ቁጥር 21.3 በመቶ ሲሆን ይህም በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ካሉት የሴቶች ቁጥር ይልቃል፡፡ በተጨማሪም ከ10 ታላላቅ የቻይና ኩባንያዎች ውስጥ ስምንት የሚሆኑት በሴቶች የሚመሩ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአውሮፓ ከ10 ኩባንያዎች አምስቱ በሴቶች ሲያዙ፣ በአሜሪካም መጠኑ ተመሳሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል በቻይና 31 በመቶ ያህሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ሴቶች ሲሆኑ በአሜሪካ 20 በመቶ ነው፡፡
በቻይና የሚያማምሩ መንገዶችና ሕንፃዎች የተገነቡት በወንዶች ብቻ ሳይሆን በሴቶችም ተሳትፎ ምር ሲሆን በርካታ ፎቆችም በቻይናዊያን ሴቶች ባለቤትነት የሚገኙ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
በቻይና ወደ ፊት ከኮሌጅ ሲወጡ ስራ አስኪያጅ የመሆን ፍላጐት ያላቸው ሴቶች 75 በመቶ የሚጠጉ  ሲሆኑ፣ በአሜሪካ ግን 50 በመቶ ናቸው፡፡ 77 በመቶ የሚጠጉ የቻይና ሴቶች ጉልበት በሚጠይቅ ስራ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሲሆን በአሜሪካ የሚገኙት አቻዎቻቸው ግን 69 በመቶ ናቸው፡፡በቻይና ከዩናይትድ ስቴትስና ከአውሮፓ በላቀ ደረጃ ሴቶች ብቃትን በሚጠይቅ ስራ ለመሳተፍ መፈለጋቸው ሲታይ፣ ለዚህም ምክንያቱም ቻይና የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት ከጀመረች በኋላ ለሁለቱም ፆታዎች እኩል ቦታ መስጠቷ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡“Center for work-life” የተባለ የጥናት ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሪፓ ራሾድ ስለዚሁ ሁኔታ ሲገልፁ፣ ..በቻይና የተካሄደው ፈጣን እድገት ታሪካዊና ባህላዊ አስተሳሰቦችን በማስወገድ ሴቶች ብቃታቸውን እንዲያሳዩ መልካም እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እንደሌላው ዓለም በቻይና ሴቶች እንዲበረታቱ እድል ከመስጠት አልፎ፣ ለአንድ ከፍተኛ የስራ መስክ ብቁ መሆናቸው የተረጋገጠበት ጊዜ ነው.. ብለዋል፡፡በቻይና የማኦ አብዮት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረ ቢታወቅም፣ ሴቶች በኃላፊነት እንዲሰሩ ያደርግ ነበር፡፡ በቻይና የኮሚኒዝም ስርዓት ውስጥ ሴቶች ወንዶች የሚሰሩትን መስራት እንደሚችሉ ይታመንም ነበር፡፡ ትምህርትን በተመለከተም ሴቶች ከወንዶች እኩል የትምህርት እድል ያገኛሉ፡፡
የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአሜሪካ ምንም እንኳን ከ40 አመት በፊት ካለው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር ሴቶች የተሻለ መብት እና የቁሳዊ ሃብት ስኬት ላይ የደረሱ ቢሆንም በወንዶች ከተያዙ አያሌ መስኮች ጋር ሲወዳደር ሴቶች ገና ብዙ መስራት እንዳለባቸው ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ ተቺዎች ደግሞ አሜሪካዊያን ሴቶች ማህበረሰባዊ ወይም አገራዊ ፋይዳ ላይ ከማተኮር ይልቅ የራሳቸው ግላዊ ስኬት ላይ ብቻ ያተኩራሉ በማለት ይገልጿቸዋል””የዲሞክራሲ መብትና የፆታ እኩልነት በሚሰበክባት አሜሪካ፤ በከፍተኛ የአመራር ቦታ የተቀመጡ ሴቶች ከወንዶች እኩል ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደማይችሉ በብዙ አሜሪካዊያን መታመኑ በጣም አስገራሚ እንደሆነ y”Work Life Center” ጥናት ይገልፃል፡፡ ለምሳሌ ሂላሪ ክሊንተን በ2008 የመጀመሪያዋ ሴት መሪ ለመሆን ባደረጉት ፉክክር የበርካታ አሜሪካዊያንን ሴቶች ቀልብ የሳቡ ቢሆንም ሂላሪ አሜሪካንን ሊመሩ መቻላቸው ግን በብዙ አሜሪካዊያን ሴቶች ጥርጣሬን ፈጥሮ ነበር፡፡ የቀድሞ የአየር ላንድ ፕሬዝዳንትና የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የሰብዓዊ ኮሚሽነር የነበሩት ሚስስ ሜሪ ሮቢንሰን የኔልሰን ማንዴላ አድናቂ እንደሆኑ ሲናገሩ፣ ከፕሬዝዳንት ከወረዱ በኋላ የሰብዓዊ ኮሚሽነር ሆነው ሲመረጡ፣ አምባገነንና በስልጣን የሚባልጉ መሪዎች በሕዝባቸው ላይ የሚፈጽሙትን ኢ - ሰብዓዊ ድርጊት በማጋለጥ ለአለምአቀፍ ማኅበረሰብ አሳውቀዋል፡፡ ሚስስ ሮቢንሰን ሲናገሩ፣ ላለፉት በርካታ ዘመናት ሴቶች በጦርነት ወቅት ዋነኛ ሰለባ ነበሩ፤ ነገር ግን አሁን ጊዜው የሴቶች ነው፡፡ ሴቶች በየትኛውም መንግስታዊ አስተዳደሮች እና አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በመሳተፍ የዓለምን ችግር ከወንዶች ጋር በጋራ የሚፈቱ መሆን አለባቸው በማለት ተናግረዋል፡፡ “Center f or life work” በአፍሪካና በሌሎች የሶስተኛ ዓለም አገራት የሚኖሩ ሴቶችን በተመለከተ ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት፤ በአፍሪካ በማኅበረሰብ ውስጥ ባሉ የረጅም ጊዜ ልማዶችና ባህሎች እንዲሁም ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች የተነሳ ከወንዶች በታች መሆናቸው ሰፊ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጓል ብሏል፡፡ በመሆኑም ሴቶች በቤት ውስጥ ባሉ ስራዎችና በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ብቻ እንዲያተኩሩ ተገደዋል፡፡ በተለይ የሴቶች የመስራት ችሎታና ብቃትን ከማየት ይልቅ አካላዊ ውበት ከፍተኛ ቦታ እንዲሰጠው መደረጉ ሴቶች ችሎታቸውን አውጥተው እንዳይጠቀሙ አድርጓቸዋል፡፡ የሚገርመው ግን ሴቶች ራሳቸው ከችሎታቸው በላይ ስለውበታቸው መጨነቃቸው ነው ይላል - ጥናቱ፡፡
ነገር ግን በዓለም በጣም ቆንጆ የሆኑ በርካታ ሴቶች በችሎታቸው አንቱ መባላቸውም መዘንጋት የለበትም፡፡ ለአብነት ያህል ወ/ሮ ዜናዚር ቡቶ በስልጣን ላይ እያሉ “People” የተሰኘ የአሜሪካ መጽሔት እ.ኤ.አ በ1996 የዓመቱ የዓለም ቆንጆ ሴት ብሎ መርጧቸዋል፡፡ ነገር ግን ቡቶ አለም እንዲያውቃቸው ይፈልጉ የነበሩት በቁንጅናቸው ሳይሆን በፖለቲካ አመራር ችሎታቸው ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ በታዳጊም ሆነ ባደጉት አገሮች ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ በርካታ ሴቶች ወደ አመራር መድረክ እየጐረፉ እንደሆኑ “Center for life work”  ይገልፃል፡፡

 

Read 6240 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:54