Saturday, 13 August 2011 09:26

ብጥብጥ - ከመኢአድ እስከ እንግሊዝ

Written by  ኤልያስ
Rate this item
(2 votes)
  • የንግሥት ኤልሳቤጥ አገር በጐዳና ላይ ነውጥ ታመሰች

በጦቢያችን ምድር የፖለቲካ ብጥብጥ ያን ያህል የሚያርበደብደን ጉዳይ ሆኖ አይደለም፡፡ ሆኖም የኢንጂነሩ ፓርቲ መኢአድ ብጥብጥ ገደብ አልፎ መሄዱ
ሰሞኑን ክፉኛ ሲያሳስበኝ ነበርና ወጌን በቀጥታ በፓርቲው ላይ አተኩሬ እንድጀምር ሰበብ ሆነኝ፡፡ ለነገሩ ጉዳዩ እናንተንም ሳያሳስባችሁ እንደማይቀር እገምታለሁ - ምናልባት ታክቷችሁ ካልተዋችሁት በቀር፡፡ ዘንግቼው እንጂ ጉዳዩ ኢህአዴግንም ማሳሰቡ አይቀርም - የፖለቲካውን ገ ግንባታ ያበላሽበታልና እኔ የምለው ግን መኢአድ ውስጥ ምን ተዓምር ቢኖር ነው ይሄ ሁሉ ቀውጢ በአመራሮች መካከል የተፈጠረው? ሥልጣን - የለም! (የምሩን ሥልጣን ማለቴ ነው) ገንዘብ - ከየት የመጣ! ዝናና ክብር - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይሄን አያውቅም! ታዲያ የብጥብጡ መንስኤ ምን ይሆን? ነገርዬው እኮ እዚህ ወረቀት ላይ እንደተጻፈው ቀላል እንዳይመስላችሁ. . . ወይስ በጦቢያ ምድር የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፍስ እንዳይዘሩ (በሁለት እግራቸው እንዳይቆሙ) የረገማቸው አለ? ይሄን ሁሉ የምዘባርቀው ወድጄ እንዳይመስላችሁ፡፡

የመኢአድ አመራርና አባላትን ስለትና ዱላ የሚያማዝዝ በቂ ምድራዊ ምክንያት አስሼ አስሼ ማግኘት ስላቃተኝ ብቻ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንቱ የዚህ ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ ስለ ፓርቲው ብጥብጥ የወጣው ዜና ውስጥ ክስተቱን ደህንነቶች በቪዲዮ ካሜራ ሲቀርት እንደነበር የአንደኛው ወገን ኃላፊ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ ይህቺ ነገር አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን የተማሪ ቤት ገጠመኙን አስታወሰችኝ፡፡ እንግዲህ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳሉ ከቤተሰብና ከጓደኞች ገንዘብና ደብዳቤ ይላክላቸዋል - ተማሪዎች፡፡ አንዱ ተማሪ ግን እምብዛም ገንዘብና ደብዳቤ የሚልክለት ወዳጅ ወይም ዘመድ አልነበረውም፡፡ ይሄን ምስጢር የሚያውቅ ጓደኛው ክፍላቸው ሰሌዳ ላይ ..እገሌ ድሃ ስለሆነ ደብዳቤ የሚልክለት የለም.. ብሎ ይጽፋል፡፡ ተማሪው አበደ - ለምን ተጻፈብኝ በሚል፡፡ ወዳጄ ምን ቢለው ጥሩ ነው? ..ድህነትህ ሳያስጨንቅህ ደሃ መባልህ እንዴት እንዲህ ያንጨረጭርሃል.. አለው፡፡ እኔም ለመኢአድ ኃላፊው ይሄንኑ ነው የምላቸው፡፡ የአገርንና የህዝብን አንገት የሚያስደፋ የብጥብጥ ተግባር ሳያስጨንቃችሁ የኢህአዴግ ደህንነት የተከሰተውን ብጥብጥ በቪዲዮ መቅረ እንዴት ያን=ru‰CºL? (የሚሰማኝ ካለ ነው እንግዲህ. . .)
ለመኢአድ አመራሮች አንድ መልዕክት ወይም ምክር አለኝ፡፡ እስካሁን ብጥብጡ የኢንጂነሩን መኪና ከመስበር ውጭ ያስከተለው አደጋ ስለመኖሩ ባንሰማም ድብድቡ ሲያይል ግን አካልና ህይወት ላይ የከፋ አደጋ ያስከትላልና ብጥብጥ በሚኖር ቀን ከፓርቲው ቢሮ አካባቢ ብትርቁ ይመረጣል፡፡ እድሜ lt½KñlÖ©þ ድብድቡን በሪሞት ኮንትሮል፣ በቴክስት ማሴጅና በፌስ ቡክ መምራት ይቻላል እኮ፡፡ ቢያንስ ከፍተኛ አመራሮች በድብድቡ ውስጥ በአካል ተሳትፈው ትዝብት እንዳያተርፉ ብዬ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ (አትደባደቡ ከማለት ይሄኛው ይሻላል ብዬ ነው) አመራሩ ምክሬን በጥሞና ሰምቶ ከተገበረው ብጥብጡ የአገር ገ ግንባታ ላይ የሚያሳርፈውን አሉታዊ ተጽዕኖ መከላከል ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡
በመጨረሻ እኔ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ብሆን ምን እንደማደርግ ብነግራችሁ ደስ ይለኛል. . . ሥልጣኔን በፈቃዴ እለቅ ነበር!! የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን እንዲህ ያለውን ነገር ፈጽሞ አያውቁትም፡፡ ለነገሩ ከመንግሥት ባለሥልጣናትም ቢሆን የፈለገ ቀውስ ቢደርስ ኃላፊነት ተሰምቶት ሥልጣን በፈቃዱ የሚለቅ እስከዛሬዋ ቀን አላየንም፡፡ (ባህላችን xYdl¥) እናም የተቃዋሚ መሪዎችን ከሥልጣን ለማውረድና ዲሞክራት መሪዎችን ለመተካትም የመካከለኛው ምስራቅ ዓይነት የህዝብ አመጽ ሳያስፈልግ አይቀርም ማለት ነው (ወይ ጣጣ!)
እስቲ ከመኢአድ ብጥብጥ ደግሞ ወደ እንግሊዙ ብጥብጥ እንለፍ፡፡ የእንግሊዙ ግን ከብጥብጥም አለፍ ይላል - ነውጥ ነው!   
ሰሞኑን መቼም ከዓለም ዙሪያ የሚሰሙት ወሬዎች ሁሉ ምናቸውም ደስ አይልም፡፡ የእንግሊዙ የወጣቶች ..ረብሻ.. ወይም የመንገድ ላይ ነውጥ ዘመናዊቷንና ዲሞክራቷን አገር እየቀወጣት አይደለም እንዴ? መቼም ለምን ተቃውሞ ተነሳ አይባልም፡፡ የእንግሊዝ ወጣቶች የጐዳና ላይ ነውጥ እንዴት ያደርጋሉ ማለትም አግባብ አይመስለኝም፡፡ ምናልባት ግን የ8ኛው ሺ መቅረብን አመላካች ሊሆንእንደሚችል ልቤ ጠርጥሯል፡፡
እኔ የምለው ግን ረብሻ ሲባል በሰለጠነም ባልሰለጠነም ህዝብ ባህርይው ተመሳሳይ ነው እንዴ? ፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወር፣ መኪና ማቃጠል፣ መስተዋት መሰባበር፣ ሱቆች መዝረፍ ወዘተ. . . ከኋላ ቀር አገራት እንዳለ ኮፒ የተደረገ እኮ ነው፡፡ በዚህ ላይ የረብሻው ወይም የነውጡ መንስኤ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ከነበረው ጋር አንድ ነው - ያው የኑሮን ጉዳይ ይመለከታል፤ በሃብታምና በድሃ የህብረተሰብ ክፍል መካከል የተፈጠረው ሰፊ ክፍተት (gap) የነውጡ ዋና ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እኔን ግርም ያለኝ ታዲያ የነውጡ ሰበብ አንድ ቢሆንም የሰለጠነው የእንግሊዝ ህዝብ ተቃውሞውን የገለበት መንገድ ከእኛ ጋር መመሳሰሉ ነው፡፡ የሰለጠነ የጐዳና ላይ ነውጥ እስከዛሬ አለመዘጋጀቱም በጣም አስገርሞኛል፡፡ የዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴት የሰለጠነ የነውጥ ሥርዓት የለውም? ከሁከት የተሻለ ማለቴ ነው፡፡ የሰለጠነ አገር፣ የሰለጠነ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የሰለጠነ ፓርላማና የሰለጠነ ሁሉ ነገር ያለው መንግሥት የሰለጠነ ረብሻ ወይም የሰለጠነ የጐዳና ላይ ነውጥ ሊኖረው ይገባ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ሰሞኑን እንደታዘብነው ግን በነውጥ ጉዳይ እንግሊዞች ከኛ ብዙም የተሻሉ አልሆኑም - ቢብሱ እንጂ፡፡ በእርግጥ የማንክደው አንድ ሀቅ አለ - መንግሥታቸው የሰለጠነ ነው፡፡ ረብሻውን እንኳን በጥይት ውሃ በመርጨትና በአስለቃሽ ጭስ እንኳን ለመከላከል ፍላጐትና ፍቃድ አላሳየም፡፡ ጭራሽ እንዲህ ያለው ነገር የእንግሊዝ ፖሊስ ባህል አይደለም አሉና አረፉት፡፡ እና ነውጠኞቹ የተከበረችውን የንግሥት ኤልሳቤጥ አገር ሲቀውጧት ይሰንብቱ? ሲባሉ . . . ኦክስፎርድ ሳይማሩ አይቀሩም ተብለው የሚጠረጠሩት የእንግሊዝ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የአፍሪካ ..ቆራጥ መሪዎችን.. የሚያሸማቅቅ መልስ ሰጡ፡፡ ስለሚወሰደው እርምጃ ከህብረተሰቡ ጋር እንማከራለን በማለት፡፡ አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች ይሄን ሰምተው ምን እንዳሉ ሰምታችኋል. . . ..ሥልጣን ላይ ያለው ቅንጅት ነው እንዴ?.. ብለዋል (እንግሊዝ አገር ማለታቸው ነው)፡፡ በ97 ዓ.ም. ፓርላማ ስለመግባትና አለመግባት ቅንጅት ህዝቡን አማክራለሁ ማለቱን አስታወሰው መሰለኝ፡፡ የደላቸው ካድሬዎች! አልኩኝ ለራሴ፡፡
እኔ ደግሞ ጠጋ ብዬ ለምን ኢህአዴግ ነውጥ የማስቆም ወይም የመግታት ተመክሮውን ለእንግሊዝ መንግሥት አያጋራም ልላቸው ፈለኩና ፈርቼ ተወኩት - ነገር ፍለጋ እንዳይመስልብኝ፡፡ ያለዚያማ ሀሳቤ ክፉ እንዳልሆነ እኮ አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ እንዴት መሰላችሁ. . . ኢህአዴግ ..ሃቀኛ.. እንደሆነ ማንም አይክደውም አይደል. . . አካፋን አካፋ የሚል ጽኑ ፓርቲ ነው፡፡ እናም በ97 ዓ.ም. የጐዳና ላይ ነውጥ መደረጉ ሀቅ ነው፡፡ ኢህአዴግም ነውጡን ተከላክሎ ነዋሪውን ወደ ሰላማዊ ኑሮው መመለሱም ሌላ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ ከተስማማን በቃ! ይሄን ሀቅ ነው ለእንግሊዝ ያካፍላት ያልኩት፡፡ ዕውቀትን መሸሸግ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ እንዳልሆነ ኢህአዴግም ያምንበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ የሰለጠነችው አገር ብልሃት ጠፍቷት በነውጠኞች ከምትናወጥ ኢህአዴግ ቢታደጋትስ?
የግድ በሶማሊያ እንዳደረገው ጦሩን መላክ የለበትም፡፡ በኢ-ሜይል የመፍትሔ ሀሳቦችን ከላከ በቂ ነው፡፡ ወይም የእንግሊዝ ፖሊሶችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰልጠን ይቻላል - በነውጥ መግታት ላይ ያተኮረ ሥልጠና በመስጠት፡፡ አገራችን በዚህ አጋጣሚም ታዲያ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ሚናዋን ታሰፋለች ብዬ አስባለሁ፡፡ ድሃና ኋላ ቀር አገር እያሉ ለሚዘልፉን ምዕራባውያንም ማለፊያ አፍ ማዘጊያ እንደሚሆነን አልጠራጠርም፡፡ ኢህአዴግ በዚህ ከተሳካለት እኔ ደግሞ በግሌ አንድ ነገር አስቤአለሁ፡፡ የሰለጠነ የጐዳና ላይ ነውጥ በፕሮፖዛል ደረጃ አርቅቄ ለንግሥቲቷ አገር ላበረክት እፈልጋለሁ፡፡ ሰሞኑን በዘመናዊቷ አገር ዓለም በዓይኑ በብሌኑ የታዘበው የጐዳና ላይ ነውጥ የሰለጠነ አገርና ህዝብን የማይመጥን ሆኖ ስላገኘሁት ነው ይሄን የነውጥ ፕሮፖዛል ለማዘጋጀት ያሰብኩት፡፡ እግረ መንገዴንም ታዲያ አገሬ እርዳታ መቀበል ብቻ ሳይሆን መለገስም እንደምታውቅ ለማሳየት ነው፡፡ እንዴት ነው. . . ሀሳቤ ተመችቷችኋል? እንደሚመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የንግሥቲቷ አገር ፕሮፖዛሌን ተቀብላ ዘመናዊውን የጐዳና ላይ ነውጥ ከተገበረችው ደግሞ የአገሬ ስም ሰማይ ይነካል ማለት ነው፡፡ ከእኔ ፕሮፖዛል አስቀድሞ ግን ኢህአዴግ የመንገድ ላይ ነውጥ እንዴት ማስቆም እንደሚቻል ተመክሮውን ለእንግሊዝ መንግሥት በአፋጣኝ ማጋራት አለበት፡፡ ለአገር ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለፓርቲውም እኮ ጥሩ የገ ግንባታ ይመስለኛል፡፡ ዶ/ር ነጋሦ ..የነጋሦ መንገድ.. የተሰኘው መጽሐፍ ላይ ኢህአዴግ ከአፍሪካ ጠንካራና ዕውቅ ፓርቲ የመሆን ምኞት እንደነበረው ገልዋል፡፡ እናም ተመክሮውን ለእንግሊዝ በማጋራት ፓርቲው መልካም ስምና ዓለም አቀፍ ዝና ይቀዳጃል ብዬ አስባለሁ፡፡ ..መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣ.. ይባል የለ! አህጉራችንን ከእንግሊዙ ዓይነት ነውጥ  ይጠብቅልን

 

Read 2891 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:35