Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Monday, 08 August 2011 09:49

የኢትዮጵያ ቡድን በዓለም ሻምፒዮና ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ2 ሳምንት በኋላ 13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በደቡብ ኮርያዋ ዳጉ ውስጥ ሲካሄድ ኢትዮጵያን የሚሳተፉ አትሌቶች የነበረ ታሪካቸውን ለማስጠበቅ ከኬንያውያን ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ለመረዳት ተቻለ፡፡ በሻምፒዮናው የኢትዮጵያ ቡድን 53 አባላት ያሉበትን ልዑካን በመያዝ እንደሚሳተፍ ሲታወቅ ከ400 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ይካፈላል፡፡

ታላላቆቹን አትሌቶች ቀነኒሳ፣ ጥሩነሽና ስለሺን በጉዳት ሳቢያ ለማካተት ያልቻለው ቡድኑ በአዳዲስ አትሌቶችና በውድድሮች የተሳትፎ ብዛት ቢለይም ከኬንያ ቡድን ያነሰ ልምድ መያዙም ስጋት ፈጥሯል፡፡ ለኢትዮጵያ ቡድን ውጤታማነት ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው በ5ሺ ሜትርና በ10ሺ ሜ ደርባ የምትሮጠው መሠረት ደፋርና በዳይመንድ ሊግ ባለፉት 2 ውድድር ዘመናት ውጤታማ የሆነውና በ10 ሺ.ሜ እንደሚወዳደር የሚጠበቀው ኢማና መርጋ ናቸው፡፡
13ኛው ጊዜ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ..ህልም፣ ጥልቅ ስሜትና ጥረት.. በሚል መርህ ሲከናወን ከ207 አገራት የተወከሉ 2472 አትሌቶች ይሳተፉበታል፡፡ ከማራቶን ውጭ እስከ 47 የሚደርሱ የውድድር ዓይነቶች የሚደረጉበት ሲሆን 7.33 ሚሊዮን ዶላር ለሽልማት ቀርቦበታል፡፡  200ሺ ኮርያውያን እና 300ሺ የውጭ እንግዶች በስፍራው ተገኝተው እንደሚከታተሉት sþºbQ yt½l¤V?N ተመልካቹ አጠቃላይ ድምር 6.5 ቢሊዮን እንደሚሆን ተገምቷል፡፡
ከ13ኛው በፊት በተደረጉት 12 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች የውጤት ታሪክ በሁሉም የውድድር መደቦች ከተሸለሙት 1615 ሜዳልያዎች (538 ወርቅ፤ 542 ብርና 535 ነሐስ) ከፍተኛውን የሜዳልያ ብዛት በመሰብሰብ በወጣው ደረጃ ኬንያ ከኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪኳ አሜሪካ 250 ሜዳልያዎች (120 ወርቅ፣ 66 ብርና 64 የነሐስ) በመሰብሰብ አንደኛ ደረጃ ላይ ስትሆን ራሽያ በ130 ሜዳልያዎች (37 ወርቅ 52 ብርና 43 ነሐስ) 2ኛ ደረጃ ላይ ነች፡፡
የኢትዮጵያ የቅርብ ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በሻምፒዮናው የተሳትፎ ታሪኳ 83 ሜዳሊያዎች (31 ወርቅ፣ 27ብርና 25 ነሐስ) በማስመዝገብ 3ኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡ ከኬንያ በኋላ ከ4-7 ያለውን ደረጃ የያዙት ጀርመን፣ ሶቪዬት ህብረት ኩባና ምስራቅ ጀርመን ሲሆኑ በ8ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በድምሩ 49 ሜዳልያዎች (18ወርቅ፣ 16 ብርና 15 ነሐስ) በማስመዝገቧ ነው፡፡
በዓለም ሻምፒዮናው ከምስራቅ አፍሪካዎቹ የአትሌቲክስ ውጤታማ አገሮች በወንዶች በርካታ ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ኢትዮጵያ 2 አትሌቶችን ስታስመዘግብ ኬንያ ግን የለችበትም፡፡ በሴቶች ሁለቱም አገራት ባለ ብዙ ሜዳልያ አትሌቶችን ሳያስመዘገቡ ቀርተዋል፡፡   ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ በርካታ ሜዳልያ በመሰብሰብ ከዓለም አትሌቶች 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው በ5ሺና በ10ሺ ሜትር ተሳትፎ የነበረው ኃይሌ ገ/ስላሴ 7 ሜዳልያዎች (4 ወርቅ፣ 2 ብርና 1 ነሐስ) በማስመዝገብ ሲሆን በ5ኛ ደረጃ ላይ የሰፈረው ቀነኒሳ በቀለ በ6 ሜዳልያዎች (5 ወርቅና 1 ነሐስ) አሸንፎ ነው፡፡
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአትሌቲክስ ከተመዘገቡ ሪኮርዶች 3ቱ bኢትዮጵያውያን ሲያዙ በኬንያ አትሌት የተያዘው 1 ብቻ ነው፡፡ bኢትዮጵያWÃnù ከተያዙ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሪኮርዶች በ5ሺ ሜትር 14 ደቂቃ ከ38.59 ሰኮንዶች በሄልስንኪ በ2005 እ.ኤ.አ ላይ የተመዘገበው በጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያው ሲሆን በ10ሺ ሜትር ደግሞ በ2003 እ.ኤ.አ ፓሪስ ላይ አትሌት ብርሃኔ አደሬ በ30 ደቂቃ ከ04.18 ሴኮንዶች በሆነ ጊዜ 2ኛው ክብረወሰን ተመዝግቧል፡፡ በ10ሺ ሜ. ወንዶች ደግሞ ታላቁ የረዥም ርቀት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2009 እ.ኤ.አ በበርሊን ተደርጐ በነበረው 12ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ርቀቱን በ26 ደቂቃ ከ46.31 ሰኮንዶች በመሸፈን 3ኛውን ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡  በ2005 እ.ኤ.አ በ5ሺ ሜትር ወንዶች እ.ኤ.አ ፓሪስ ላይ ኤሊውድ ኪፕቾጌ ርቀቱን በ12 ደቂቃ ከ12.79 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ በመጨረስ ክብረወሰን የያዘ ብቸኛው የኬንያ አትሌት ነው፡፡
በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካቸው የኢትዮጵያና የኬንያ አትሌቶች በተለያዩ የአትሌቲክስ የውድድር መደቦች ያስመዘገቡት የሜዳልያ መጠን ሲነፃፀር ካለፉት 2 ሻምፒዮናዎች ወዲህ ኬንያውያን የኢትዮጵያ የነበረውን የበላይነት እየነጠቁ መምጣታቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች በ10ሺና በ5ሺ ሜትር ብልጫ ሲኖራት ኬንያ በወንዶች 5ሺ ሜትርና በሁለቱም ፆታዎች የማራቶን ውድድሮች የተሻለ የውጤት ታሪክ አላት፡፡
በሴቶች 5ሺ ሜትር ኢትዮጵያ 8 ሜዳልያዎች (3 ወርቅ፣ 1 ብርና 1 ነሐስ) ሲኖራት ኬንያ 5 ሜዳልያዎች (1 ወርቅ 2 ብርና 2 ነሐስ) አስመዝግባለች፡፡ በሴቶች 10ሺ ሜትር ደግሞ ኢትዮጵያ 13 ሜዳልያዎች (5 ወርቅ፣ 5 ብርና 4 ነሐስ) ስትሰበሰብ ኬንያ 4 ሜዳልያዎች (1 ወርቅና 3 ነሐስ) ብቻ አግኝታለች፡፡
በ5ሺ ሜትር ወንዶች ኬንያ ብልጫ ያላት በድምሩ 12 ሜዳልያዎች (7 ወርቅ፣ 2 ብር፣ 3 ነሐስ) በመሰብሰብ ሲሆን ኢትዮጵያ 7 ሜዳልያዎች (1 ወርቅ፣ 4 ብርና 2 ነሐስ) አግኝታለች፡፡ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን ብልጫ ያሳዩት ከ1993 እ.ኤ.አ ጀምሮ ሲሆን 15 ሜዳልያዎችን (8 ወርቅ፣ 4 ብርና 3 ነሐስ) ሲወስዱ ኬንያውያን 11 ሜዳልያዎች (3 ወርቅ፣ 4 ብርና 4 ነሐስ) አግኝተዋል፡፡  
በማራቶን በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በፊት አሰለፈች መርጊያ ባገኘችው 1 ነሐስ ብቻ ስትወከል ኬንያ 2 ጊዜ ወርቅ እና 1 የብር ሜዳልያ በማግኘት የተሻለ ታሪክ ተመዝግቦለታል፡፡ በወንዶች ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያ በተሳትፎ ታሪኳ 1 ወርቅ፣ 1 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያዎችን የወሰደች ሲሆን ኬንያ ደግሞ 3 የወርቅና 2 የብር ሜዳልያዎችን ለማግኘት በቅታለች፡፡

Read 4455 times

Latest from