Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Monday, 08 August 2011 09:42

.6ኛው ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. በናይጀሪያዊና ዚምባብዌያዊ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለ6ኛ ጊዜ የተካሄደው የ..ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. አብሮ የመኖር ውድድር ባለፈው ሳምንት ሲጠናቀቅ የናይጀሪያዋ ኬረንና የዚምባቡዌዋ ዌንደል አሸናፊ ሆነው እያንዳንዳቸው 200ሺ ዶላር ተሸለሙ፡፡ ለ91 ቀናት በዘለቀው አብሮ የመኖር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሃና መኩሪያ እስከ መጨረሻው ሳምንት በመዝለቅ ከሰባቱ ዕጩዎች ተርታ ከመግባቷም በላይ በ90 ቀን ቆይታ ለኢትዮጵያ ተሳታፊዎች አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች፡፡

ሃና መኩሪያ እስከ 90ኛው ቀን ከቀሩት ሰባት ነዋሪዎች አንዷ ልትሆን ብትችልም  በመጨረሻው ሳምንት ውድድር ከኢትዮጵያ ብቻ አንድ ድምጽ አስመዝግባ በመጀመሪያ ዙር በመባረር 7ኛ ደረጃ ይዛ ጨርሳለች፡፡ አንዳንድ ዘገባዎች ሃኒ ከቁንጅና በቀር በውድድሩ ለአሸናፊነት የሚያደርስ ብቃት እንዳላሳየች የጠቆሙ ሲሆን በሶሻል ሚዲያ በቂ ቅስቀሳ አለመደረጉ ውጤቱ ላይ ተዕኖ እንደፈጠረባት ተገልጿል፡፡ 6ኛው የ..ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. ውድድር በነበረው ፉክክርና የተመልካች ብዛት ከዚህ ቀደሙ የላቀ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

Read 4026 times

Latest from