Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 August 2011 15:42

የሴቶች ገፅታ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አዲስ የልማት ራዕይ ከአጋሮቹ ከኢንቪዥን ቢዮንድ ቤዚክ ኒድስ አሶሲየሽን ከሴቶችና ህፃናት ልማት ድርጅት እና ከማህበረሰብና አካባቢ ልማት አገልግሎት ከሚባሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ..የሴቶች ገፅታ ክፍል 2.. በሚል ርዕስ የተሰጠው የስዕል አውደርዕይ በብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ ከነሀሴ 4 - ነሀሴ 8 2003 ለተከታታይ አምስት ቀናት ለህዝብ እይታ ክፍት ይሆናል፡፡ ይህ ክንዋኔ በአዲስ አበባ በሚገኙ አምስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራቶች አንዱ ሲሆን  አውደርዕዩ በከተማችን ውስጥ ሴቶች በልማት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያመለክት በመሆኑ ጠቃሚ መልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በተጓዳኝ በሚቀርቡለት የግጥም ምሽቶች ውይይቶች ወ.ዘ.ተ. እየተዝናና ዕውቀት የሚገበይበትም ይሆናል፡፡

በሴቶች ላይ በተለይም በትምህርት ቤት ባሉ ልጅዓገረዶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በሃገሪቱ እንዲሳኩ የታለሙ የልማት ግቦች በተለይም ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስና የሴቶችን እኩልነት መረጋገጥ የመሳካት አላማዎች እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ከሚተገበሩት ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ሥርዓተ-ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ማጥናት ነበር ፡፡ ጥናቱ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ያተኮረ ሲሆን በግንቦት ወር 2003 ዓ.ም ተጠንቶ ለተለያዩ የመንግስት አካላቶች ጥናቱ ይፋ ተደርጓል፤፤ በዚህም ጥናት መሰረት ሴትና ወንድ ተማሪዎች የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች እንደሆኑ የሚያመለክቱ ውጤቶች የተገኙ ሲሆን ለምሳሌ ከ 156 የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች 70% ያህሉ ወደ ት/ቤት በሚሄዱበትና በሚመጡበት ወቅት የድብደባ (ቀላልም ከባድም) ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከዛ ውስጥ  95% ያህሉ ሴት ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተይዞ 51% ያህሉ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች የወሲባዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ወይም የቅርብ ሰው ጉዳት ሲደርስበት የተመለከቱ ናቸው፡፡ ይህ ጥናት ባጭሩ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያሳይ ሲሆን በትምህርት ቤቶች ውስጥ  የሚፈፀሙ ጥቃቶች አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጫና በመፍጠር ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ለትምህርት ፍላጎታቸው እንዲቀንስና ዝቅተኛ ውጤት እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋፅዎ ያደርጋል፡፡  
አዲስ ዴቨሎፕመንት ቪዥን ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ባለፉት 17 ወራቶች  የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የሴቶች ገፅታ ሁለት የስእል አውደርዕይም  የዚሁ አካል ሲሆን አውደርዕዩ በአራት ዋና ዋና ሀሳቦች ማለትም  የሴቶች ጥቃት፣ ሴቶች በልጆች መነፅር፣ የውሎ አሻራ ??? ከአድማስ ባሻገር በሚል ርእስ የሚቀርቡ ስእሎችን ለእይታ ያቀርባል፡፡ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው አውደርዕይ አላማው ህብረተሰቡ እየተዝናና በስርአተ ፆታ ዙሪያ ግንዛቤውን እንዲያዳብር ማድረግ ነው፡፡
..የመሃፉ አውደ ርዕይ.. እና የስእል አውደርዕዩ የሴቶች ገፅታ 2 አንዱ አካል ሲሆን የ ሴት ደራሲያን ማህበር  በመሀበሩ አባሎች የተፃፉ መፅሀፎችን ለእይታ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሴት ደራሲያን ማህበር የግጥም ምሽቶችን አሰናድተው ለታዳሚው በማቅረብ ለፕሮግራሙ ድምቀት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ በውይይትና በግጥም ምሽቶች የታጀበውን አውደርዕይ ላይ በመታደም እየተዝናና ግንዛቤውን እንዲዳብር ሁሉም የህብረተስብ ክፍል ተጋብዘዋል፡፡

 

Read 7162 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 15:50