Saturday, 06 August 2011 15:26

ኢህአዴግ በቀኝ ነው በግራ?

Written by  ኤልያስ
Rate this item
(0 votes)

እንዴትይዟችኋልክረምቱ?ብርዱመቼምእንደኑሮውድነቱበየዕለቱእያመረረነው አይደል...አንዳንድ     የሸገርሴትእህቶቻችንንአለባበስየተመለከተግንጊዜውየብርድሳይሆንእልምያለየሙቀትወቅት ሊመስለው ይችላል፡፡ ወዳጅ አገር ቻይናስ ምን ብንበድላት ነው በክረምት ስስ ታይቶችን አምጥታ የዘረገፈችልን? ወይስ ታይቶቹ ..ብርድ ፕሩፍ.. (ብርድ ተከላካይ) ናቸው? እኔማ ምን አሰብኩ መሰላችሁ... አሰብኩ ሳይሆን አሳሰበኝ ኢህአዴግ ወጪ ወራጁ ሁሉ ግብርና ቫት ካልከፈለ በሚል ..ሰፍ.. ባለበት በዚህ ሰዓት የሴቶቹን አለባበስ አይቶ ..የቅንጦት ግብር.. ጥያለሁ ቢል የማን አለህ ይባላል፡፡

ሴቶች ተሰብስበው የተቃውሞ ሰልፍ እንኳ ቢወጡ (ከተፈቀደላቸው) ምን እንደሚባሉ ታውቃላችሁ? መጀመሪያ 20 በመቶ ክፈሉና ተከራከሩ ነው የሚባሉት፡፡ መቼም ሴቶቻችን ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ነው የሚወድቁት፡፡ ለ100 ብር ታይት 200 ብር ግብር ሊጣል እንደሚችል አትጠራጠሩ፡፡ አንዳንዶች ቅዠታም ሊሉኝ ቢችሉም ፈጽሞ አልፈርድባቸውም - ኢህአዴግን ስለማያውቁት ነው፡፡
ደቡብ አፍሪካ ወስጄ የዓለም ዋንጫን አሳያችኋለሁ በሚል ከ40 ሚ. ብር በላይ ሰብስቦ ጀርመን ገባ የተባለው ሰውዬ በፖሊስ ተይዞ አገሩ ሲመለስ ጋዜጠኛ ገንዘባቸውን የተበሉ ሰዎችን አስመልክቶ ..እነዚህ ሰዎች ገንዘባቸውን ማግኘት የለባቸውም?.. ብሎ ሲጠይቀው ..አለባቸው ግን ገንዘባቸውን ለመመለስ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል.. ሲል መመለሱን ሰምቼ ተገርሜ ነበር፡፡ አንድ ጓደኛዬ ምናለ መሰላችሁ? ..ከሌሎች ሰዎች ላይ እንዲሁ ገንዘብ ሰብስቦ ሊመልስ ይሆናላ!.. ብሎ የበለጠ አስገርሞኛል፡፡ ሰውየው ልቀቁኝና ተንቀሳቅሼ አለብህ የተባልኩትን እዳ ልክፈል ማለቱ በመርህ ደረጃ እኮ ችግር የለውም፡፡ ለመንግሥትም ሆነ ለተበዳዮች ግን ..ሰዶ ማሳደድ.. ስለሚሆንባቸው ተጠርጣሪው ሌላ አማራጭ ቢያቀርብ ሳይሻለው አይቀርም፡፡
የማጭበርበር ነገር ሲነሳ ወደ አእምሮዬ ከመቅጽበት ከች ያለው ምን መሰላችሁ? ..የወራሹ ፓርቲ.. የቅንጅት ሊ/መንበር የነበሩት ሰውዬ ናቸው፡፡ ከግለሰቦች 100ሺ ነው 150ሺ ብር ተቀብለው የቅንጅት አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን አባል ናቸው በማለት ቪዛ እንዲሰጣቸው ለጀርመን አምባሲ ደብዳቤ ጻፉ የተባሉትን ግለሰብ ማለቴ ነው፡፡ አሁን ጀርመን ይሁን አሜሪካ ገብተዋል አሉ፡፡ ስለ እኚህ ሰው ሳስብ አንድ የቆየች ተረት ትዝ አለችኝ ..እማዬ ምነው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ.. የምትለዋ፡፡ ግለሰቡ ከ97 ምርጫ ቀውስ በኋላ የተፈጠረውን ግርግር ተጠቅመው የቅንጅት ወራሽ ነን በሚል ቅንጅት የምትለዋን ስም ከምርጫ ቦርድ ላፍ ማድረጋቸውን አታስታውሱም? ክፋቱ ግን አልጠቀማቸውም፡፡ ስሙን ቢወርሱም የኦርጅናሉን ..ቅንጅት.. ደጋፊ ህዝብ (ያ እንኳን ማዕበል የተባለውን) በጮሌነት ላፍ ማድረግ አልተቻላቸውም፡፡ በግርግርና በጮሌነት ህዝብን መሸወድ እንደማይቻል እንዲህ ያለ ታክቲክ ለመሞከር ላሰቡ ..አራዳ ነን ባይ ፖለቲከኞች.. ማለፊያ ማስተማሪያ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እኔ የምለው የፖለቲከኞችን ፊታቸውን ወደ ትምህርት ማዞር እንዴት አያችሁት? በሥልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ አባላትም እኮ ከላይ እስከ ታች bW አገር ካሉ ዩኒቨርስቲãCÂ ኮሌጆች የርቀት ትምህርታቸውን ተከታታለው አነሰ ቢባል ዲፕሎም በተረፈ ግን ድግሪና ማስተርሳቸውን እንደያዙ ሰምተናል - በወሬ ወሬ፡፡ እናም የኢህአዴግ ታጋዮች በበረሃ ትግል ያጠፉትን ወርቃማ የትምህርት ጊዜ በመንግስትነት ዘመናቸው ስላካካሱ እዳ የለብንም ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! አንዳንዶቹ እኮ የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ከሁለተኛና ሦስተኛ ዓመት አቋርጠው ነበር በረሃ የገቡት - ከትምህርት በፊት ነፃነት ይቀድማል ብለው፡፡ መቼም አበሻ ሃሜት ይወዳልና መንግስት የርቀት ትምህርትን አግጃለሁ ያለ ሰሞን ..ኢህአዴግ የራሱ ሰዎች ተምረው እስኪጨርሱ ጠብቆ የርቀት ትምህርትን አገደ.. እያሉ ሲቦጭቁት ነበር፡፡ ሃሜቱ በማስረጃ የተደገፈ ይሁን አይሁን ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም፡፡ ኢህአዴግ ለትምህርት የሚሰጠውን ትኩረት ለማጣጣል የሚሹ አንዳንድ የኒዮ ሊበራሊዝም አቀንቃኞች ደግሞ ፓርቲው አገር እየመራ ሳይሆን ..የሥራ ላይ ልምምድ.. (On Job training እንደሚሉት) እያደረገ ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡ እነሱ የሚሉት እውነት ከሆነ እኮ ኢህአዴግ መንግስትነትን እየተለማመደብን ነው ማለት ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ግን ይሄን ሀሜት እንጂ ትችት ብዬ አልቀበለውም፡፡ ሥልጣን ይዞ ልምምድ. . . ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው!
እንዴት መሰላችሁ. . . ኢህአዴግ እኮ የ20 ዓመት የመንግስትነት ልምድ ያለው ፓርቲ ነው፡፡ እርግጥ ነው ትላንትና ሥልጣን ላይ እንደወጣ ፓርቲ አዳዲስ ህጐችና ደንቦች በየጊዜው ሲያወጣ ታዝበነዋል፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ የሸቀጦችን ዋጋ በመተመን የዋጋ ንረቱን ለማርገብ ሙከራ አድርጐ ከሽፎበታል፡፡ አንዴ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነኝ ሌላ ጊዜ bn ካፒታሊዝም ነው የምመራው እያለ ሲወላውልም አስተውለናል፡፡ እኛ ብቻ ሳንሆን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ የህይወት ታሪካቸውን በሚተርከው ..የነጋሦ መንገድ.. መጽሐፍ ላይ አፍረጥርጠውታል፡፡
ነጋሦ ከኢህአዴግ የተፋቱትም በዚሁ ወላዋይነቱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖች ኢህአዴግ ወደ ግራ እያዘነበለ እንደሆነ ቢናገሩም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ይሄንን አይቀበሉም፡፡ እውነት ግን አሁን ኢህአዴን የቱ ጋ ነው? በቀኝ ነው በግራ? ይሄ ጥያቄ የ1 ሚ. ብር ሽልማት የሚያሸልም ጥያቄ የመሆን አቅም እንዳለው በእርግጠኝነት XnግራCºlhù”” እንኳን እኛ ተራ ተርታ ዜጐች ራሳቸው የፓርቲው አመራሮች ድንገት ቢጠየቁ የሚደነጋገሩ ይመስለኛል፡፡ ኢህአዴግ ካፒታሊስት ይሁን ኮሙኒስት፤ ልማታዊ መንግስት ይሁን ኒዮሊበራሊስት በትክክል አውቃለሁ የሚል ከተገኘ ይንገረን - ወሮታውን ስፖንሰር አፈላልገንም ቢሆን እንከፍላለን፡፡ ዶ/ር ነጋሶ በመጽሐፋቸው እንደጠቀሱት ኢህአዴግ 10 ዓመት ሙሉ ጭጭ ብሎ ከርሞ አንድ ቀን ተነስቶ ሶሻሊዝምን መሳቢያ ውስጥ ደብቀነዋል ቢለን ኖሮ በጣም እንቀየመው ነበር፡፡ ወዳጆቼ. . . ሌላ ሌላውን ስቀድ ኢህአዴግ ..የሥራ ላይ ልምምድ.. (On the Job training) እያደረገ ነው ወይስ አገሪቱን እየመራ? የሚለውን አወዛጋቢ ጥያቄ ዘነጋሁት አይደል!
አሁን ስጠረጥር አንዳንድ የኒዮሊበራሊዝም አቀንቃኞች ኢህአዴግ on job training ላይ የመሰላቸው አዳዲስ ህግና ደንብ እያወጣ መልሶ ስለሚሽር ከሆነ ይሄ የሥራ ላይ ልምምድ ሳይሆን ሙከራ (Experiment) ተብሎ እንደሚጠራ ልጠቁማቸው እፈልጋለሁ፡፡ አንዳንድ ሆቴሎች ወይም ባሮች (bars) ምሽት ላይ የቢራ ዋጋ የሚቀንሱበት |Happy hours´ እንዳላቸው ሳታውቁ አትቀሩም፡፡ (የቢራ ኮታችሁን የኑሮ ውድነቱ ቢቀንሰውም) ኢህአዴግ ደግሞ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመኑን |Experimenting Year´ ብሎ እንደሰየመው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል፡፡
መሃል ላይ ሌላ አጀንዳ ጥልቅ አለና የወጌን አቅጣጫ አሳተኝ እንጂ አጀማመሬስ በትምህርት ዙሪያ ነበር፡፡ እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምን ያህል የማስተርስ ምሩቅ አባላት አሉት? የዲግሪና የዲፕሎማስ? በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው የተማረ የሰው ሃይል ምን ያህል እንደሆነ የሚያጠና ተቋም ቢኖር አይከፋም፡፡ በተለይ በምርጫ ወቅት ይሄ ዓይነቱ መረጃ በጣም ያስፈልገናል፡፡ መቼም ከ97 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ኢህአዴግ የተማሩ እጩዎችን ለምርጫ ማቅረብ ያለውን ፋይዳ የተረዳ ይመስለኛል፡፡ ከዛ በፊትስ? ከዛ በፊትማ ዋናው መስፈርት ትምህርትና ችሎታ ሳይሆን ታማኝነት ነው እያለ ሲያደርቀን እንደነበር እማኞቹ እኛው ራሳችን ነን፡፡ (ታማኝነት ግን ለካድሬነት ካልሆነ በቀር...) ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ህዝብ የተማረ ..አድናቂ.. መሆኑ የገባው መቼ መሰላችሁ? ወደ ቅንጅት ያዘነበለ ጊዜ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ዘግይቶም ቢሆን እንኳን ህዝቡ የሚፈልገው ገባው እላለሁ፡፡
ይሄ የትምህርት ነገር ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ላይ ተጋብቶባቸው የአንጋፋ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለትምህርት ባህር ማዶ እየተሻገሩ መሆናቸውን እያየንና እየሰማን ነው፡፡ ከመድረክ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ከአንድነት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌው ለትምህርት ወደ W አገር ሄደዋል፡፡ በእርግጥ የትምህርቱን ዓይነት አላወቅነውም፡፡ ከፖለቲካው ጋር የተያያዘ ትምህርት ቢማሩልን ግን ለእኛም ለራሳቸውም ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፡፡ በርግጥ የመቻቻል፣ የመግባባት፣ የመደማመጥ ኮርስም እግረ መንገዳቸውን ቢወስዱ የበለጠ ይጠቀማሉ፡፡ ለዛ ያለው ንግግር የማድረግ ሥልጠናም ቢያገኙ አይከፋም፡፡ እንጨት እንጨት የሚል ንግግር ከመስማት እንድናለን፡፡ እርስ በርስ ሲዘላለፉም እንኳ በለዛ ይሆናላ! ቅድም የኢህአዴግ አባላትን የርቀት ትምህርት ስናወጋ የተከታተሉትን የትምህርት ዘርፍ ሳልጠቅስ ነበር ያለፍኩት፡፡ ለምን መሰላችሁ? አላውቀውማ! ግን የኢህአዴግ ባለስልጣናት እንዲህ እየመሩን ያሉት ምን ተምረው ቢሆን ነው የሚለውን ማወቅ በጣም የሚያጓጓ ነገር ይመስለኛል፡፡ መረጃው አለን የምትሉ እባካችሁ ተባበሩን፡፡ የባለሥልጣናት ሃብት እየተመዘገበ ነው በሚባልበት ዘመን የተማሩትን ትምህርት የተመለከተ መረጃ ማግኘት ያን ያህል አስቸጋሪ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በተለያዩ አገራት የተመደቡ 46 ገደማ አምባሳደሮቻችን የንግድና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሆነ ሰማሁና በደስታ ፈነደቅሁኝ፡፡ አንድ ..መርዶ ነጋሪ.. የምለው ወዳጄ የሰጠው አስተያየት ግን ደስታዬ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሰበት፡፡ ..ባይማሩ ይሻላል . . . የተማሩት ፖለቲከኞች ምን ሰሩልን?.. አለኝ - በጨለምተኝነት በታጀበ ቅላፄ፡፡
ሁሌም የፖለቲከኞቻችንን የትምህርት ነገር ሳስብ አንድ ወዳጄ የነገረኝ እውነተኛ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡ የዛሬ ፖለቲካዊ ጨዋታችንን በዚሁ ታሪክ ብንቋጨውስ፡፡ ሰውየው በደርግ ዘመን ለብዙ ዓመት በወህኒ ቤት የታሰረ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ የወህኒ ቤቱ ገራፊ ነበር፡፡ ሰውየው የእስር ጊዜውን አጠናቆ ከወህኒ ይወጣል፡፡ ብዙ ዓመት ካለፈ በኋላ ይሄ እስረኛ የነበረ ሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲከታተል ያንን የወህኒ ቤት ገራፊውን ካምፓስ ያገኘዋል፡፡ ..እዚህ ምን ትሠራለህ?.. ይለዋል - ተገርሞ (ዩኒቨርስቲ ገራፊ አያስፈልግማ!) ..ህግ እየተማርኩ ነው.. ሲል መለሰ - ገራፊው፡፡ ሰውየውም ..ፈርደህ ጨርሰህ!.. አለው፡፡ የፖለቲከኞቻችንም ነገር እንዲህ እንዳይሆን እንጂ መማራቸውስ አይከፋም ነበር፡፡ ኧረ ይማሩልን!!

Read 2915 times