Saturday, 06 August 2011 14:53

ሃኒ በ..ቢግ ቢራዘርስ.. አልተሸነፈችም!

Written by  ፊያሜታ
Rate this item
(0 votes)

ላኪ - ወዳጄ
ተቀባይ - እኔ
SMS - ‘vote-hanny at 835’
***
ወዳጄ ሆይ መቼም እንትን ያሉሽን እንትን ትይ... ነገር ትቀባጥሪ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ቴክስት ሜሴጅህ ደርሶኝ እንዳነበብኩት ምን እንደተሰማኝ ታውቃለህ?... አገርህ አሸናፊ እንድትሆን የተቻለህን ሁሉ የማድረግ ቁርጠኝነት እንዳለህ... በሃኒ የተወከለች አገርህ ተሸላሚ እንድትሆን ድምህን ከመስጠት ባለፈ፣ ሌሎችም ድም እንዲሰጡ የህዝብ ንቅናቄ የመፍጠር ተነሳሽነትህ ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝቤÃlhù፡፡ ይሄን ሁሉ ተገንዝቤ ግን... እንደጠየቅኸኝ ድምፄን ሳይሆን ሀሳቤን ለመስጠት ፈቀድኩ፡፡

ምን መሰላችሁ? (አንባቢያን) ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጥሪው ደርሷት ልትታደመው ያልቻለችው የአለም የእግር ኳስ ዋ ለ19ኛ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ሲጠጣ፣ በሩቅ እያየች አንጀቷ ባረረ ልክ በአመቱ በለስ ቀናትና ሌላ ዋ ልትታደም ሁለት ልጆቿን ወደ ደቡብ አፍሪካ ላከች፡፡
6ኛው ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ-አብሮ የመኖር ውድድር በደቡብ አፍሪካ ተካሂዷል፡፡ ከተለያዩ 14 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 26 ያህል ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ይህ ውድድር፣ ግለሰቦች በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ብቃታቸውን የሚያስመሰክሩበት መሆኑን ሰምተናል፡፡ የሚገጥሟቸውን የተለያዩ ፈተናዎች በትእግስትና በጥበብ ማለፍ፣ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መዝለቅ፣ ችግሮችን በብልጠት መፍታት ወዘተ...  በየጊዜው ከሚደረገው ቅነሳ ተርፈው ለ91 ቀናት ያህል በውድድሩ መቆየት የቻሉ ሁለት ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው 200 ሺህ ዶላር እንደሚሸለሙም ሲናገር ነበር፡፡ በዘንድሮው ውድድር አገራችን ዳኒ እና ሃኒ የተባሉ ሁለት ወጣቶችን ብታሰልፍም ዳኒ ቀደም ብሎ የቅነሳው ሰለባ ሲሆን ሃኒም በቅርቡ ከውድድር ውጭ ሆናለች፡፡
ይህቺን የአገሪቱ ብቸኛ ተስፋ ወደ አሸናፊነት ለማሸጋገር የህዝብ የድጋፍ ድም ወሳኝ መሆኑን የተገነዘበው ወዳጄ ነው እንግዲህ ‘vote-hanny at 835’ የሚል አገራዊ ጥሪ ያስተላለፈልኝ - ያኔ ሃኒ ከውድድሩ ከመሰናበቷ በፊት፡፡
ወዳጄ የአገሩን ስም በአሸናፊነት የማስጠራት ከፍተኛ ጉጉት፣ አገሬ እንዳትሸነፍ የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳደረበት ይሰማኛል፡፡ ጉጉቱ ሳይሆን ስጋቱ የወዳጄን የዋህነት xrUGõL¾L፡፡
ሃኒም ኢትዮጵያም ይሸነፉ ይሆን? በሚል እንዲህ ከንቱ ስጋት የሚያንገበግባቸውን አገር ወዳድ ዜጐች እኔ የዋሆች እላቸዋለሁ፡፡
የዋሆች ሆይ!
አትስጉ... ስለ ሃኒም... ስለ ኢትዮጵያም አትስጉ፡፡ ውድድሩ ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ በአርቴፊሻል ፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለሦስት ወራት የመቆየት ውድድር ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለስድስተኛ ጊዜ ካዘጋጀችው ቢግ ብራዘርስ የመረረ ውድድር ለሺህ አመታት በተከታታይ ስታዘጋጅ የኖረች፣ መላ ህዝቧን አሳትፋ መላ ህዝቧን ስትሸልም የኖረች አገር ናት - ኢትዮጵያ!
የደቡብ አፍሪካው እንጂ የኢትዮጵያው ቢግ ብራዘርስ ሶስት ወር ተብሎ ቀን የሚቆረጥለት ውስን የፈተና ጊዜ የለውም፡፡ አንዲት ኢትዮጵያ በአንዲት ሃኒ ሳይሆን በመላው ህዝቧ ነው የምትወከለው... ለምን ቢባል ሶስት ወር ሳይሆን ሶስት ሺህ ዘመን በራሷ ቢግ ብራዘርስ ተካፍላ የምንጊዜም አሸናፊ ሆና ዘልቃለችና፡፡
ኢትዮጵያ ለዘመናት ባስተናገደችው የራሷ ቢግ ብራዘርስ አቻ የለሽ ፈተና ውስጥ መላው ህዝቧን እያሳተፈች ድሉን ከህዝቧ እጅ ባለማስነጠቅ ሃትሪክ የሰራች (በሺህ አመታት ስሌት) የምንጊዜም ድል ባለቤት እኮ ናት!
የዋሆች... ስለ ደቡብ አፍሪካው ቢግ ብራዘር ስለምን ትጨነቃላችሁ?... ሃኒ እኮ ለእግር ኳስ አይደለም የሄደችው፡፡ እሱንማ ብለነው ብለነው አልሆን ብሎ ቸግሮናል፡፡ ደረጃችን ከሌሎች በታች ሆኖ ቀርቶብን በሩቅ እያየነው ተብሰልስለናል፡፡ አሁን ሃኒን ወደ ደቡብ አፍሪካ የላክናት ከአቅሟ በላይ ሳይሆን በታች ወርዳ ወደምትጫወትበት  አብሮ የመኖር ቀላል ፉክክር ነው፡፡ ሰቆቃንና ፈተናን ተጋፍጦ በመኖር የአለም ሻምፒዮናነቱን አለም በአንድ ድም ያፀደቀለት አሸናፊ ህዝብ ወኪል የሆነችው ሃኒ፣ ያለ ዲቪዚዮኗ ስንትና ስንት ቁልቁል ወርዳ እኮ ነው የተወዳደረችው፡፡
ሃኒ ከቢግ ብራዘር ውድድር ውጭ መሆኗን ሰሞኑን ሰማሁ፡፡ ሰማሁና ሳቅኩ፡፡ ለምን ሳቅኩ? የአገሬ መሸነፍ የማያንገበግበኝ ሰው ሆኜ ነውን?... አይመስለኝም!
ሃኒ ከውድድሩ ውጭ የሆነችው የቢግ ብራዘርስ አብሮ የመኖር ውድድር አሸንፏት ወይም አቅቷት አይመስለኝም! እሷ ከመስፈርቱ በላይ ሆና እንጂ!... (over qualified እንደ¥ለት)   ኢትዮጵያ ከ6ኛው የቢግ ብራዘርስ አፍሪካ ውድድር የተሰናበተችው በቀላል ሚዛን ውድድር የከባድ ሚዛን ተወዳዳሪ በማሰለፏ ነው ባይ ነኝ፡፡
ልክ በእግር ኳስ ውድድር ላይ እንደሚከሰተው... ለምሳሌ ከ16 አመት በታች የሆኑ ተጫዋቾች በሚሳተፉበት የታዳጊ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ የ25 አመት እድሜ ያለው ተጫዋች በማሰለፉ ከውድድር ውጭ እንደሚሆን ክለብ፡፡
ይመስለኛል... ሃኒ ከውድድሩ የተባረረችው የቢግ ብራዘርስ ፈተና ስላቃታት አይደለም፡፡ ምናልባትም እሷ ለፈተናው ከብዳው ቢሆን እንጂ፡፡ ሃኒ ከቢግ ብራዘር ግቢ ተባረረች የሚሉ፣ እነሱ አንዷን ሃኒ ብቻ የሚያዩ የዋሆች ናቸው፡፡ ሃኒ እዚያው ደቡብ አፍሪካ ናት... ደቡብ አፍሪካ... ኡጋንዳ... ኬኒያ... ሊቢያ... ሻሸመኔ... ቤሩት... አሜሪካ... እዚህም እዚያም ተበትና ከቢግ ብራዘር የመረረ ሰቆቃ ውስጥ እየተንገላታች ችግር ቻይነቷን እያስመሰከረች ያለች ብዙ ኢትዮጵያዊ ሴት ናት ሃኒ፡፡
ቢግ ብራዘር በሚሉት የፌክ ፈተና እና ፎርጅድ ውጣ ውረድ ተሸነፋችሁ ሲሉን ሰማሁና ሳቅኩ!
ዳኒ እና ሃኒ አይችሉም ተብለው መባረራቸው በሳቅ አፈረሰኝ፡፡
ምን ማለታቸው ነው ዳኞቹ?... እንደ ዳኒ... እንደ ሃኒ... እንደ መላው ኢትዮጵያዊ ለችግር ሳይረታ ዘመናትን ያለፈ ማን ነው?... ተቻችሎ መኖር ከሆነ ጉዳዩ... ማን እንደነሱ ተቻቻይ አለና ነው!... ስድብ ዘለፋን አይደለም፣ ግርፋትን ችሎ የኖረ ቆዳው ድርብ ህዝብ እኮ ነው ተሸንፈሃል የተባለው፡፡
ከዚህ በላይ ኮሜዲ አለ እንዴ?
ለሶስት ሺህ ዘመን ክፉ ደጉን ችሎ አብሮ የኖረ ህዝብ እንዴት ነው ለሶስት ወር አብሮ መኖር አቃተህ ተብሎ ቀይ ካርድ የሚሰጠው?
ሃኒ እና ዳኒ እኮ በቢግ ቢግ ቢግ ብራዘርስ-ኢትዮጵያ' ፈታኝ የኑሮ ውድድር ለዘመናት አሸናፊ የሆነው የመላው ኢትዮጵያዊ ወኪሎች ናቸው፡፡ ትከሻው መከራን መሸከም የማይደክመው፣ በስቃይ ውስጥም ተቻችሎ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከሴት ሃኒ፣ ከወንድ ዳኒ ብሎ የወከላቸው ናቸው፡፡
ሁለቱን ከቢግ ብራዘር-አፍሪካ ውድድር ውጭ ማድረግ የመላውን ችግር ቻይና አብሮ ኗሪ ህዝብ ክብር መንካት ነው፡፡
ቢግ ብራዘርስ-አፍሪካ እንጂ አመቱን ጠብቆ የሚካሄደው፣ ቢግ ብራዘርስ-ኢትዮጵያ' ይሄው ከዓመት አመት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በየጓዳ ጐድጓዳው የሚካሄደውን የእኛን የቀን ተቀን የመኖር ውድድር የሚቀር ካሜራ ባይጠመድም ፍልሚያው ይሄው ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡
በእነሱ እንጂ በእኛ ቢግ ብራዘር ለመወዳደር ምዝገባ አያስፈልግም፡፡ ማጣሪያውን ለማለፍ የህዝብ ድም ወሳኝ አይደለም፡፡ የ200 ሺህ ዶላር ሽልማት ባገኝ ብሎ አይደለም ኢትዮጵያዊ ወደ አገሩ ቢግ ብራዘር የሚገባው፡፡
የደቡብ አፍሪካውን እንጂ የእኛን ቢግ ብራዘር የውድድር ሂደት የሚቀርፀው ካሜራ በተወሰነ ቦታ ላይ አይተከልም፡፡ ደፋ ቀና ስንል የሚያሳየንን፣ ቻይነታችንን የሚያመለክተውን የኑሮ ፊልማችንን የአለም አይን ለዘመናት ደጋግሞ ሲያየው ኖሯል - እያየም ሲያደንቀን፣ ሲንቀን፣ ሲስቅብን፣ ሲሳለቅብን... ሙድ ሲይዝብን...፡፡
ተሸነፋችሁ የተባልንበት አርቴፊሻል ቢግ ብራዘር አፍሪካ ከመጀመሩ ከዘመናት በፊት እኮ ነው የእኛው ብሔራዊ ቢግ ብራዘር የተጀመረው፡፡
ከቢግ ብራዘር-አፍሪካ' ቀድሞ አለም የእኛን ቢግ ብራዘር ይከታተል ነበር፡፡ አርቴፊሻል ያልሆነውን ፈተናችንን፣ ተሰልቶ ያልተሰጠንን መከራችንን፣ ህግ ያልወጣለት... ገደብ ያልተቀመጠለት...ከእዚህ እስከ እዚያ ያልተባለለት አብሮ የመኖር ትራጀዲያችንን እያየ አለም ሁሉ አጃኢብ ሲል ኖሯል፡፡ ተደናቂው የእኛ ቢግ ብራዘር በተወሰነ ቻናል ለተወሰነ ተመልካች አይደለም ሲሰራጭ የኖረው፡፡
አለም ሁሉ ሲያየው ኖሯል - ዲኤስ ቲቪ ሳያስገጥም! ያየውንም ፎ አስቀምጦታል... በየታሪክ ድርሳኑ... በየ መዝገበ ቃላቱ፡፡
(በነገራችን ላይ) ...እነ ሃኒ ያሸንፉ ዘንድ የህዝብ ድም እንደ¥ÃSfLUcW ሁሉ በኦክስፎርድ ላይ ያለውን |Famine´ የሚል ቃል ፍቺ ለማሠረዝም የህዝብ ድም ዋጋ የለውም!
(በፌስ ቡክ በኦክስፎርድ መዝገበ-ቃላት ላይ ስለ ኢትዮጵያ የተፃፈውን ፀያፍ ነገር ለማሰረዝ ድም እንስጥ የሚል ዘመቻ መጀመሩን ልብ በሉ)
‘drought’ እና “Famine’ ከኦክስፎርድ ማሰረዝ ቢቻል እንኳን ከአለም ልቡና ግን መፋቅ  አይቻልም፡፡   
እና!... ሃኒ በ..ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. አልተሸነፈችም! ምናልባት ሃኒ በ..ቢግ ቢራዘርስ..
xLt¹nfCM
አልቀረም፡፡

 

Read 5005 times Last modified on Saturday, 06 August 2011 15:20