Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 August 2011 14:15

የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት በዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላይ የተላለፈውን እግድ ተቃወሙ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ዲያቆን ዳንኤል የአሜሪካ ቆይታውን አቋርጦ ተመልሷል
የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያስተላለፈውን ከማኅበሩ አባልነት እና አገልግሎት የማገድ ውሳኔ ተቃወሙ፡፡ ከማኅበሩ የሀገር ውስጥ 47 ማእከላት መካከል ከዐሥር ያላነሱት እግዱን በማእከላቸው ተፈፃሚ ለማድረግ እንደሚቸገሩ ለዋናው ማእከል ጽ/ቤት በስልክ እና በደብዳቤ መግለፃቸውን የማኅበሩ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ዲያቆን ዳንኤል በማኅበሩ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመደበኛ አገልጋይነት በሚሠራበት ወቅት የተፈጠሩ፣ በማኅበሩ የአገልግሎት ስትራቴጂ እና አካሄድ ላይ የተመሠረቱ ልዩነቶች የዲያቆን ዳንኤልንና በማኅበሩ የወቅቱ አመራር አባላት መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት እንዳሻከረው ምንጮቹ አብራርተዋል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ሥራ አመራሩ ኮሚቴ አቋቁሞ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች በመጓተቱ የችግሩ አያያዝ በዲያቆን ዳንኤል ላይ ቅሬታ አሳድሯል ተብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የማኅበሩ ዋና ሐፊ ዲያቆን ሙሉጌታ ኃይለማርያም በቅርቡ ለ..ዕንቁ.. መጽሔት የሰጠውን ቃለ ምልልስ አስመልክቶ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጽሑፍ ያዘጋጀውን ትችት ከቆየው መሠረታዊ ልዩነቱ ጋራ አካትቶ በ..ደጀ ሰላም.. ብሎግ እና በማኅበራዊ ድረ ገፆች ይፋ በማድረጉ ከአመራሩ ጋራ የነበረው ቅሬታ ተባብሶ ለመታገድ እንዳበቃው ተመልክቷል፡”የማኅበሩ ማእከላት በተቃውሟቸው፣ በሥራ አመራሩ የተላለፈው እግድ በዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍ አሉታዊነትና በማኅበሩ አገልግሎት ላይ የሚጋርጠውን አደጋ ለመከላከል በሚል የታሰበ ቢሆንም በአባላት የሥነ ምግባር መከታተያና መቆጣጠሪያ ደንብ መሠረት ደረጃውን ጠብቆ ያልተፈፀመ እና አድሏዊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዚህም ሳቢያ የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ የማኅበሩ ማእከላት የሥራ አስፈፃሚ ተወካዮች የሚገኙበት የሥራ አመራር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራቱ ታውቋል፡፡ የማኅበሩን የእግድ ውሳኔ አግባብነት እና ዲያቆን ዳንኤል በ15 ገጽ ያቀረባቸውን የልዩነት ሐሳቦች መርምሮ መሠረታዊ መፍትሔ እንደሚሰጥ የሚጠበቀው አስቸኳይ ጉባኤው፤ ዛሬና ነገ እንደሚካሄድ ተገልጿ፡፡ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ለአንድ ወር አገልግሎት ተጉዞ የነበረው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ በጉባኤው ላይ በአስረጅነት ለመሳተፍ አገልግሎቱን አቋርጦ መመለሱ ታውቋል፡፡

 

Read 8549 times Last modified on Thursday, 15 September 2011 07:35