Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 31 July 2011 14:32

አንድ ቃል.. ትያትር በመሃፍ ታተመ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከሰባት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ለሕዝብ ቀርቦ ለረዥም ጊዜ ሲታይ የነበረው የፀሐፌ ተውኔት ተገኝ ለማ ..አንድ ቃል.. ትያትር በመሃፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ፡፡ሕትመቱን አስመልክቶ ለአዲስ አድማስ መግለጫ የሰጡት ፀሐፊ ተውኔት ተገኝ ለማ፤  ..ከነሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ሥራዎች ወዲህ በርካታ ትያትሮች ባለመታተማቸው የትያትር ኮርስ የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲ ሌሎች ተቋማት የግብአት ችግር ሲገጥማቸው በማየቴ አሳትሜአለሁ.. ብለዋል፡፡

መታሲቢያነቱን በትያትሩ ትተውን ለነበረችውና አሁን በሕይወት ለሌለችው አርቲስት ሙናዬ መንበሩ ያደረገው የተውኔት መጽሐፍ፤ 114 ገፆች ያሉት ሲሆን ለገበያ የቀረበውም በ20 ብር ነው፡፡ በተውኔት መጽሐፉ ጀርባ ከተጻፉት አስተያየቶች መካከል አዲስ አድማስ ጋዜጣ በሕዳር 19 ቀን 1996 ዓ.ም ዕትሙ ..የአንድ ጥበብ ሥራ ታላቅነት የሚመዘነው በሕብረተሰቡ ላይ በሚያመጣው ለውጥ በመሆኑ ‘አንድ ÝL’ ትያትር በዚህ ተሳክቶለታል፡፡.. በሚል የጠቀሰው ይገኝበታል፡፡

 

Read 4401 times Last modified on Sunday, 31 July 2011 14:36