Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 31 July 2011 13:47

ግብር ከፋዮች ከሕገወጦች ጋር እንዲገበያዩ አይፈለግም..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አቶ ማሞ አብዲ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር የታክስና የጉምሩክ ጉዳዮች አማካሪ ናቸው፡፡በዘንድሮው ዓመት የግብር ተመን ቀደም ሲል ከነበረው በ10 እጥፍ እና ከዚያ በላይ መደረጉ ለንግዱ ማኅበረሰብ xSdNU•L”” ተመኑ ምን ያህል አግባብ nW?   
በ2003 ዓ.ም መንግሥት በሠጠው ውሳኔ መሰረት የፌደራል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከአዲስ አበባ የገቢዎች ኤጀንሲ ጋር አንድ ላይ ተዋህደዋል፡፡ ይህም የታክስ አስተዳደሩን ለማጣጣምና በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የታክስ ስርዓት አንድ ዓይነት ባህርይ እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡

በተለይም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያላቸው እንደ አዲስ አበባና መሰል ትላልቅ ከተሞች የሚደረገው የታክስ እንቅስቃሴ ወጥ እንዲሆን የፌደራል የታክስ አስተዳደር ከከተማው የታክስ አስተዳደር ጋር በጋራ መሥራት ጀምረዋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በፊት በባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት ስር ከነበሩት ጭማሪ በማሳየት 208 ሺህ ግብር ከፋዮች በባለሥልጣኑ መ/ቤት ስር ይገኛሉ፡፡  
የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮቻችንን ወደ ኋለ መለስ ብለን ስንመለከተው፣ 83 በመቶ የሚሆነው በግምት የሚከፍል ነው፡፡ ይህ ማለት ለሰባት ዓመታት ያህል ታክስ የሚከፍሉበት ሥርዓት ሳይሻሻል ቆይቷል፡፡ አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት በ1996 ዓ.ም በነበረው አተማመን ነበር፡፡ አንድ ኢኮኖሚ ባደገ ቁጥር የታክስ መሠረቱም እያደገ መምጣት አለበት፤ ለሰባት ዓመታት ያልተቀየረው የታክስ አከፋፈል በጥናት ላይ ተመስርቶ ታምኖበት ነው የተቀየረው፡፡  
ግብር ከፋያችን ጠንቅቆ እንደሚረዳው ግብር ለልማታችን፣ ለከተማችን አስተዳደርና ምቹ የሆነች የመኖሪያ ከተማ ለመፍጠር የግዴታ በራሳችን ገቢ ተማምነን ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል፡፡
በተለይ ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ጋር ተያይዞ ከኢኮኖሚ ጋር የሚጣጣም አዲስ የታክስ ሥርዓት መኖር አለበት፡፡ የመንግሥትን ዕቅድ የግድ ለማሣካት ተብሎ አለአግባብ በግብር ከፋዩ ላይ የተወሰነ ተመን ሳይሆን በጥናት ላይ በመመስረት የተካሄደ ነው፡፡  
የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋዮችን በተመለከተ፣ በአብዛኛው ለመመዝገብ ብቁ ሆነው ቢገኙም፣ በፈቃደኝነት ቀርበው አይመዘገቡም፡፡ በ2003 ባዘጋጀነው የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መሠረት ከቫት ከፋዮች፣ ትክክለኛና ፍትሀዊ የውድድር መድረክ እንዲኖር ፍጠሩልን፣ ቫት ያልተመዘገቡ ይመዝገቡ በሚል ተደጋግሞ በተነሣው ጥያቄ መሠረት እኛም ወደ ቫት መረቡ ያልገቡትን እንዲገቡ ለማድረግ በቀየስነው ስትራቴጂ መሠረት፣ የማትጊያ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን፣ በዚህም ወደ 5,052 (አምስት ሺህ ሀምሳ ሁለት) የሚሆኑት የመንግሥትን ጥሪ አክብረው በተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ ቀርበው ተመዝግበዋል፡፡ ይህ የማትጊያ ባህርይ ምህረትን ያካተተ ስለነበር ከዚህ በፊት መክፈል የሚገባቸው ተሽሮላቸው የሦስት ወር ብቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡ በዚህ የማትጊያ ሥርዓቱ የተጠቀሙ ወደ ኋላ ተሂዶ የታክስ ዕዳ ቢኖር እንደማይጠየቁ እንዲሁም ታክስ አለመክፈል ወንጀል በመሆኑ በሕግም እንደማይጠየቁ የሚገልጽ ነው፡፡
ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ የሚገባቸዉ ለ135 ቀናት በቀበሌ፣ በወረዳና ክፍለ ከተማ ባካሄድነው የተደራጀና ሰፊ የመረጃ ጥናት መሠረት ከ11ሺህ በላይ የሚሆኑት ቫት ለመመዝገብ ብቁ ሆነው ያልተመዘገቡ ናቸው፡፡ በማትጊያ ሥርዓት መሠረትም እነዚህ ግለሰቦች የመንግሥትን ጥሪ ባለማክበራቸው ወደ ኋላ ተመልሰን ግብር መክፈል ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስን እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ ይህን የመጠየቅ መብት አለን፡፡ የወንጀል ተጠያቂነት ከመጣ ደግሞ ወደ እስር ቤት መግባት ብቻ ነው፡፡
በሌላ በኩል በተካሄደ የመረጃ ጥናት ቀደም ሲል ምንም ግብር ሳይከፍሉ ወይም ሳይመዘገቡ በንግድ እንቅስቅሴ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለማወቅ ችለናል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም ዓይነት የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ ሕጋዊ ሳይሆኑ የሚሠሩ ናቸው፡፡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴÃcW ደግሞ ከማንም በላይ ነው፡፡ በቂ መደብር እና መጋዘን አላቸው፤ ነገር ግን ግብር ሳይከፍሉ ይሠሩ የነበሩ ናቸው፡፡
ነገር ግን ከዚህ በፊት በግብር ከፋይነት ተመዝግበው በዘንድሮው ዓመት ከፍተኛ ግብር መጣብን የሚሉትን በተመለከተ ደግሞ፣ እስካሁን ይከፍሉ የነበረው በ1996 ዓ.ም በነበረው ተመን ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አነስተኛ ሱቅ የነበረው ግለሰብ ምናልባት 100 ብር ይከፍል ከነበረ ከሰባት ዓመት በኋላ ግን ድርጅቱን በጣም አስፋፍቶና ፎቅ ጭምር ሰርቶ ባለበት ሁኔታ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ይከፍል በነበረው ተመን ይክፈል ማለት ፍትሐዊ አይደለም፡፡ በአብዛኛው ግብር ከፋዮቹ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከፍተኛ እድገት አሳይተዋል፡፡ ግብሩም የተተመነው ገቢያቸውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡  
እርስዎ እንዳሉት በርካታ ዕድገት ያሳዩ ግብር ከፋዮች መኖራቸው አይካድም፡፡ ነገር ግን ላለፉት ሰባት ዓመታት ብዙ ለውጥ ያላመጡትም ሁሉ ከፍተኛ ግብር ተጭኖባቸዋል፡፡
በመሠረቱ መንግሥት ግብር የሚሰበስብበት መንገድ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ የገቢውን መጠን በሂሳብ መዝገብ መረጃ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የሚያቀርብን እና ምንም የሂሳብ መዝገብ ሳይዝ በግዴታ ግምት የሚወሰን ነው፡፡ በአብዛኛው ግብር ከፋይ የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ባለመሆኑ በግምት በሚወሰን ግብር መንግሥትንም ሆነ ግብር ከፋዩን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህንን ልዩነት ለማቀራረብ በተጠና እና በተደራጀ ሁኔታ የሚተመን ነው፡፡ አንዳንዴ ግምቱ ተጋነነ ማለት የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጠ ማለት አይደለም፡፡ የታክስ ሥርዓታችን ባስቀመጠው መሠረት ቅሬታ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቅሬታ ሲቀርብም የቅሬታ አቀራረብ እርከኖች አሉ፡፡ በመጀመሪያ ለአስተዳደሩ ያቀርባል፣ ቀጥሎ ለይግባኝ ሰሚ ያቀርባል፤ በእነዚህ ተሰሚነት ካጣ ደግሞ እስከ ፍርድ ቤት መሄድ ይቻላል፡፡ ስለዚህ የተተመነው አግባብ አይደለም ካለ፣ ቅሬታውን ማቅረብና የመደመጥ መብቱ በሕጉ ላይ ስላለ ያንን ማቅረብ ይችላል፡፡
በደረጃ ¼ ውስጥ የነበሩ ግብር ከፋዮችን የግድ ወደ l ደረጃ እንዲገቡ ማድረግ፤ ሁሉንም በአንድ ላይ መጨፍለቅ አይሆንም?  
አስቀድሜ እንደገለጽኩት ግብር የተተመነው ከሰባት ዓመት በፊት በነበረው ሁኔታ ሳይሆን በ2003 ዓ.ም በተካሄደ ጥናት ነው፡፡ በዚህ መሠረት፣ ከደረጃ l ወደ h ያደጉ አሉ፡፡ ከደረጃ ¼ ደግሞ ወደ l ያደጉ አሉ፡፡ ደረጃ ¼ ሆነው ባሉበት ያሉም አሉ፡፡ ይህም የሆነው በቀን ከሚያገኘው ግምት በመነሣት ነው፡፡ ለምሣሌ የቀን ገቢው ግምት 300 ብር ሆኖ ወደ l አላስገባነውም፡፡ ከደረጃ l ወደ ደረጃ ¼ የሚወርድም አለ፡፡
የቤት ለቤት የመረጃ ስብስብ ላይ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሳተፉ መደረጉን በተመለከተ በመረጃው ታማኝነት ላይ ቅሬታ የሚያሰሙ አለ? የተማሪዎቹ ግምት ምን ያህል ትክክል ነው?  
የተማረ ሰው የተሰጠውን ሥራ መሥራት ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህንን ሥራ በውጤት ሊያሳካ የሚችለው ስልጠና ሲሰጠው ነው፡፡ ስለዚህ ከተማ ውስጥ እንደሚባለው እነዚህ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንደመጡ የከተማውን ገቢ ሊገምቱ ወደ ከተማ አልተሰማሩም፡፡ እነዚህ ልጆች ሥነ ምግባርን ጨምሮ መሠረታዊ የሆነውን የተቋሙን የቢዝነስ ሂደቶች እንዲያውቁ ከመደረጉም በላይ እንዴት አድርገው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የቀን ገቢን መገመት እንደሚችሉ ሙሉ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የተለያዩ ነገሮች በትምህርት ቤት እያሉ የተማሩ ቢሆንም የበለጠ ብቁ የሚሆኑበትን ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተማሪዎቹ ብቻቸውን አይደለም የሚሠሩት፤ የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎችም የቡድን መሪ ሆነው በማስተባበር ነው የመረጃ ማሰባሰቡ ሥራ የተካሄደው፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ95ሺህ በላይ የንግድ ቤቶችን መረጃ ለማሰባሰብ ችለዋል፡፡  ግብር ከፋዩ አለአግባብ ተተምኖብኛል ካለ መቃወም ይችላል፡፡
አንዳንዶች ፈቃዳቸውን ለመመለ የሚመርጡ xlù?
በአሁኑ የመረጃ ሥርዓታችንን እያጠናከርን መጥተናል፡፡ ይኸውም በጣት አሻራ ላይ የተደገፈ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር መስጠት ነው፡፡ በዚህ መሠረት በርካታ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ጉር ቤት፣ ኬክ ቤት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ ቤት... የመሳሰሉት ሁሉም በአንድ መረጃ ሥርዓት ውስጥ እንዲገቡ ይሆናል፡፡ ሌላው የካሽ ሬጂስተር ማሽን እንዲያስገቡ የምንጠይቀው የሚፈጠረውን አተካራ ለማስቀረት ነው፡፡ ሁሉም ሰው በካሽ ሬጂስተር የሚጠቀም ከሆነ መረጃው እኛ ጋር ስለሚመዘገብ ተገቢ ያልሆነ ግብር ተጫነብኝ ወይም በዛብኝ የሚለውን ጭቅጭቅ ያስቀራል፡፡ ነገር ግን ፈቃዱን ለመመለስ የሚመጣ ሰው መብቱ ነው፡፡
የካሽ ሬጅስተር ማሽን እንዲያስገቡ የሚገደዱት እነማን ÂcW?
የካሽ ሬጂስተር ማሽን ግብር ከፋዩ መጠቀም እንዳለበት ስንወስን፣ የመግዛት አቅም የሌላቸውን ሰዎች ግምት ውስጥ አላስገባንም ነበር፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱም አቅም የለንም ለሚሉት የዱቤ ሽያጭ አመቻችቶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የደረጃ ¼ ግብር ከፋዮች የካሽ ሬጂስተር ማሽን እንዲያስገቡ አይገደዱም፡፡ ደረጃ h እና ደረጃ l ግብር ከፋዮች ግን የካሽ ሬጂስተር ማሽን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የቫት ተመዝጋቢዎች ደረሰኝ ከሌላቸው ግለሰቦች ዕቃ በሚገዙበት ወቅት የባለሥልጣኑ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ማስረጃ እንደ¥Yqb§*cW YgLÚlù?
አንድ የመረጃ ሥርዓታችን አካል የመረጃ ልውውጥ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ደረሰኝ መስጠት እንዳለበት ሕጉ ይጠቅሳል፡፡ ይህ በባለሥልጣኑ ቁጥጥር ሥርዓት ውስጥ የተመዘገበና ፈቃድ የተሰጠው መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች ከጥቃቅኖች እንገዛለን፡፡ ይህ ማለት k¼ ግብር ከፋይ ዕቃ ሲገዙ ¼ ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ ስለማይዙ ራሳቸው የሚያዘጋጁት ቫውቸር መኖር አለበት፡፡ በዚህ መሠረት የገዛበትን ዋጋና የገዛበትን ግለሰብ አድራሻ አሟልቶ ማቅረብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጥያቄው የሚነሳው... በ100ሺ እና በ200ሺ ብር ግብይት ተካሂዶ ደረሰኝ የላቸውም ማለት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም እነዚያ ሰዎች በቀን ያንን ያህል ሽያጭ የሚያደርጉ ከሆነ የግዴታ በታክስ ስርዓት ውስጥ የገቡ መሆን አለባቸው፡፡ አለበለዚያ ግን ሕገ ወጦች ናቸው፡፡ ሕገ ወጦች ከሆኑ ደግሞ ግብር ከፋይ ከሕገ ወጦች ጋር እንዲገበያይ አይፈለግም፡፡ እንዲያውም ስለእነዚህ ሰዎች ለባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ መረጃ ሊሰጥ ይገባዋል፡፡   
ግብር ተቀባዮች ግብር ከፋዩን በአግባቡ ያለመስተናገድና አንዳንዴም የማመናጨቅ ሁኔታ እንዳለ YglÉL?  
በእርግጥ እነዚህ ስህተቶች የሉም ማለት አይቻልም፡፡ ግብር ከፋዩን በተለያዩ መድረኮች ስናወያይ እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በተለያየ ዘርፍ ላይ ከግብር ከፋዩ ጋር በግንባር ሊገናኙ ለሚችሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ሊያሻሽሉ የሚችሉበትን ሥልጠና ሰጥተናል፡፡ በቀጣይም እየሰጠን ነው፡፡ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች መሥሪያ ቤቶች የሚለየው የራሱ የሆነ የሥነ ምግባር መመሪያ አለው፡፡ ያንን የሥነ ምግባር መመሪያ መሠረት አድርጐ ለግብር ከፋዩ ተገቢውን አገልግሎት የማይሰጥ ሠራተኛ ካለ መጠቆም አለበት፡፡ የሐሳብ መስጫ ሳጥን ውስጥ አስተያየት መስጠት ይቻላል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙዎች ባለሙያዎች ከቦታቸው ተነስተዋል፡፡ ግብር ከፋዩ በምናዘጋጀው መድረክ ላይ ብቻ ይህንን ነገር ከሚገልጽ እያንዳንዱ ሠራተኛ ደረቱ ላይ ባጅ ስላለው፣ ከዚያ ላይ ሙሉ ስሙን በመጻፍ በግንባር ቀርቦ ሊናገር ይችላል፡፡

Read 6362 times