Sunday, 31 July 2011 13:40

የመኪና ውስጥ ሲዲ ማጫወቻዎችን የሚያስንቅ ቴክኖሎጂ መጣ

Written by  ዮናስ ብርሐኔ
Rate this item
(0 votes)

አዲስ እንደተፈጠረው ቴክኖሎጂ ከሆነ በመኪና ውስጥ የምንፈልገውን /ሙዚቃ/ ለማዳመጥ አጐንብሶ /ሲዲ/ መፈለግ ወይም መመራረጥ ጊዜው ያለፈበት ነገር ሊሆን የተቃረበ ይመስላል፡፡ የአሜሪካው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ፎርድ ያመጣው አዲስ ቴክኖሎጂ፤ አሽከርካሪዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ከተለያዩ ዲጂታል ሚዲያዎች ጋር መገናኘት እና እንደ ..አይፖድ.. ያሉ ዲጂታል የሙዚቃ ማጫወቻዎችን ሰክተው መጠቀም የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡

ኩባንያው እንደገለው፤ አሽከርካሪዎች ..ዶንግል.. የተባለ አነስተኛ መሳሪያ በመሰካት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈልጓቸው ሙዚቃዎች ከሚገኙበት ..ሚዩዚክ ላይብረሪ.. ጋር ግንኙነት በመፍጠር ያሻቸውን ዘፈኖች በቀላሉ ለማግኘት እና ለማዳመጥ የሚችሉበት ..ኢንፎቴይንመንት ኸብ.. ነው ለመኪኖቹ የሚገጠምላቸው፡፡
የሞባይል ስልኮቻችንን ጨምሮ እንደ/ ያሉ ሌሎች ዲጂታል የሙዚቃ መጫወቻዎችን ከዚሁ ኮምፒውተራይዝድ የመኪና ውስጥ ሙዚቃ ማጫወቻ ..ኸብ.. ጋር አገናኝተን መጠቀም የምንችል ሲሆን እንደ አፕሉ ..አይክላውድ.. (icloud) ከመሳሰሉት በኢንተርኔት ውስጥ የሚገኙ ዲጂታል የሙዚቃ ማጠራቀሚያዎች ተጠቃሚ መሆን እንችላለን””የመኪና ውስጥ ሲዲ ማጫወቻዎችም ሆኑ የዲስኮች ሽያጭ መጠን እየቀነሰ እንደመጣ የጠቀሰው ዴሊ ሜል፤ በዲጅታል መልክ የሚቀርቡ ዘፈኖች (አልበሞች) ሽያጭ ግን እየጨመረ እንደመጣ አመልክቷል፡፡ አዲሱ ዲጂታል የሙዚቃ ማጫወቻ ከዘመኑ ጋር አብሮ ለመራመድ እና የተጠቃሚውን ፍላጐት ለማርካት ወሳኝ እንደሆነ የተናገሩት የፎርድ “Global Trends and Futuring” ክፍል ኃላፊ፤ አዲሱ ዲጂታል የሙዚቃ መጫወቻ የተገጠመላቸው የፎርድ መኪኖች ከ2015 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ ገበያ ላይ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡

Read 2877 times