Print this page
Sunday, 24 July 2011 08:08

አዲስ አድማስ ከሪፖርተር ዛሬ በድጋሚ ይገናኛሉ

Written by  ግሩም
Rate this item
(0 votes)

ኢሬቴድና የአርቲስቶች ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሰፊ ዕድል ይዘዋል
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ..ስፖርት
ለአገርልማት..በሚልመርህባዘጋጀውየሚዲያናየኪነጥበብባለሙያዎችየእግርኳስ ውድድር ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉ
ቡድኖችእየታወቁናቸው፡፡የአዲስአበባስፖርትኮሚሽንከዜድኬፕሮሞሽንጋርበመተባበር ያዘጋጀውን ይህን ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታድዬም በርካታ ተመልካቾች እየታደሙት ነው፡፡

8 ቡድኖች በተሳተፉበት ውድድሩ በምድብ 1 አዲስ አድማስ ከሪፖርተር ዛሬ 7 ሰዓት ላይ በድጋሚ ጨዋታ ይገናኛሉ፡፡ ከዚያ በፊት 5 ሰዓት ላይ የሚጫወቱት የ2003 ጋዜጠኞች ቡድን ከዛሚ ጋር ነው፡፡ አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር በውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ ተገናኝተው አዲስ አድማስ 11 ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ቢያሸንፍም በተጨዋች ተገቢነት በሪፖርተር በቀረበ ክስ ጨዋታው እንዲደገም በአዘጋጆቹ ተወስኗል፡፡  የአዲስ አድማስ ቡድን በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታውን ረቡዕ ዕለት ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሐን ጋር አድርጐ 2ለ0 አሸንፏል፡፡ በሌሎች የምድብ 1 ጨዋታዎች ኢሬቴድ የመጀመሪያ ግጥሚያውን ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሐን ጋር በማድረግ 3ለ0 ሲያሸንፍ ከትናንት በስቲያ ደግሞ ሪፖርተርን 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ ዕድሉን አመቻችቷል፡፡ በምድብ 2 የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ የ2003 ጋዜጠኞች ስብስብ ኤፍ ኤም 97.1ን 3ለ0 ቢያሸንፍም ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች በማሳለፉ ውጤቱ ተገልብጦ በፎርፌ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸናፊነቱ ለኤፍ ኤም 97.1 ተሰጥቷል፡፡ በምድብ 2 ያለው የአርቲስቶች ቡድን ተጋጣሚዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አልተቻለም፡፡ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዛሚ ኤፍ ኤም ጋር ያደረገው ቡድኑ 11 ለ1 ያሸነፈ ሲሆን ትናንት ደግሞ ኤፍ ኤም 97.1ን 8ለ1 ማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
በምድቡ ቀሪ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሪፖርተር ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሐን ኤፍ ኤም 97.1 ከዛሚ እና የአርቲስቶች ቡድን ከ2003 ጋዜጠኞች ቡድን ሰኞ ሲገናኙ እንዲሁም አዲስ አድማስ ከኢሬቴድ በመጪው ማክሰኞ ይገናኛሉ፡፡
የውድድሩ የምድብ ጨዋታዎች የፊታችን ማክሰኞ ይጠናቀቃሉ፡፡ የግማሽ ፍጻሜው ሐሙስ ዕለት ሲቀጥል የምድብ 1 አንደኛ ከምድብ 2 ሁለተኛ እንዲሁም የምድብ 2 አንደኛ ከምድብ 1 ሁለተኛ ጋር የሚገናኙ ይሆናል፡፡ በሁለቱ ጨዋታዎች አሸናፊ የሚሆኑት ቡድኖች የዛሬ ሳምንት ለሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የሚደርሱ ሲሆን ተሸናፊዎቹ ለደረጃ ይጋጠማሉ፡፡ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አንድ ኃላፊ ለስፖርት አድማስ እንደገለፁት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ውድድሩ ከሞላ ጐደል ስኬታማ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በውድድሩ የተፈጠረው የተሳትፎ ፍላጐትና መነሳሳት አበረታች መሆኑን ያደነቁት ኃላፊው አንዳንድ ቡድኖች በበቂ ሁኔታ የተደራጀ ቡድን ይዘው አለመቅረባቸው፣ በተጨዋች ተገቢነት እና btÃÃ? ጉዳዮች ውዝግቦችና ቅሬታዎች መብዛታቸው በጅምሩ ያገኘነው ተሞክሮ ነው ካሉ በኋላ በተቻለን መጠን ፍትሐዊ ዳኝነት በመስጠት ውድድሮቹን ለማካሄድ ሞክረናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡  በእግር ኳስ ውድድሩ ከ1-3 ለሚወጡ ቡድኖች የገንዘብ ሽለማት የተዘጋጀ ሲሆን ለ1ኛ 5ሺ ብር፣ ለ2ኛ 3ሺ ብር እንዲሁም ለ3ኛ ደረጃ 2ሺ ብር እንደሚበረከት ተገልል፡፡

Read 4861 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 08:19