Sunday, 24 July 2011 07:48

አዳም ረታ ለአድናቂዎቹ ጥያቄ ምን መለሰ?

Written by  ብርሃኑ ሰሙ
Rate this item
(4 votes)

እንደማይታተም እያወቁ መፃፍ አያስጨንቅም ወይ? ለሚለው፤ የምፈው ለማሳተም አይደለም፡፡ ለሁፍ ስነሳ መንፈሴ ብቻ ሳይሆን ገላዬ በሙሉ በሆነ ነገር የተሞላ ይመስለኛል፡፡ ያንን ለማስተንፈስ መፃፍ ስላለብኝ እፋለሁ፡፡ ይቀመጣል፡፡ አሳታሚ መኖሩን ሲወራ ነው የማውቀው፡፡ማህሌት፣ ግራጫ ቃጭሎች፣ እቴሜቴ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር፣ አለንጋና ምስር፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ የሚል ርዕስ ባላቸው መፃህፍቱ የሚታወቀው ደራሲ አዳም ረታ፤ ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም ከአድናቂዎቹ ጋር ተገናኝቷል፡፡

በማህሌት አሳታሚ አዘጋጅነት በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ በተሰናዳው መድረክ፤ በደራሲው ሥራዎች ላይ የጥናት ሁፍ ያቀረቡትን ጨምሮ የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች የነበሩ ሲሆን ከዕለቱ ታዳሚዎች ለቀረቡለት ጥያቄዎች ደራሲ አዳም ረታ በዚህ መልኩ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
እርስዎን ለማየት ከወሊሶ ከመጡት አንዱ ነኝ፡፡ ሥነ ወሲብን በተመለከተ ከስብሐትና ከበአሉ ግርማ ጋር የሚመሳሰሉ አፃፃፍ አለዎት፡፡ በሁለት ጐን ወይም እይታ በመተረክ እርስዎ በተለየ ይታወቃሉ፡፡ በአካል የማናገኛቸው ዓይነት ውበት፣ ተፈጥሮና ባህርይ ያላቸው ገፀባህሪ የሚስሉልን ደራሲያን ብዙ ናቸው፡፡ እርስዎ በተቃራኒው በቅርባችን የምናውቃቸውን የሚመስሉ ገፀባህርይ ይፈጥራሉ፡፡ ጥያቄዬ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጉድለት ያለባቸውን ገፀባህሪያት የሚስሉበት ምክንያት ምንድ ነው?
ሰው ሆነን ተፈጥረናል፡፡ ፍፁማዊ ሰው የለም፡፡ እኔ በምስላቸው ገፀ ባህሪያት ዝርዝር ነገራቸውን የመግለ ልምድ የለኝም፡፡ የአንዲት ሴት ገፀ ባህርይ ፊቷን ማሳየት የምፈልግ ከሆነ አይኗን ብቻ ነው አጉልቼ ለማሳየት የምሞክረው፡፡ የቀረውን አንባቢው ሞልቶ እንዲመለከት ነው የማደርገው፡፡ አሳሳቋን፣ አካሄዷን... ልናገር እችላለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ከአንባቢው ጋር አብረን ነው የምንሄደው፡፡
ኤድጋር አለንፖ እናቱን አይወድም ነበር ይባላል፡፡ ያንን ጥላቻውን ለመግለ ..ዘ ብላክ ካት.. የሚል መሐፍ ፃፈና ስሜቱን ገለፀ፡፡ አዳም ረታም በመፃህፍቶቹ የራሱን ድብቅ ፍላጐት፣ ፍርሐት... አቅርቦ ይሆን? የሚል ጥያቄ አለኝ፡፡
ለድርሰቶቼ መነሻ የሆነኝ ግለ ታሪክ የለኝም፡፡ በምፍበት ወቅት ያለሁበት ሙድ፣ የተነቃቃሁበት ሁኔታ፣ የቃላት አመራረጤ፣ የአንቀ አከፋፈሌ... ትንፋሼን ሁሉ ሊቆጣጠር ይችላል፡፡ የግል ታሪኬ መነሻ ሆኖኝ የፃፍኩት ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ከፃፍኩ በኋላ ሳነበው የእኔ ታሪክ የሚመስል ነገር ካለ በእርማት ወቅት ከሁፉ እንዲወጣ አደርጋለሁ፡፡
ገፀ ባህሪያቶችዎ የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ከእርስዎ ህይወት ጋር ምን ግንኙነት አላቸው? ተወልደው ያደጉት የት ነው?
የተወለድኩት በአዲስ አበባ ነው፡፡ ገፀ ባህሪው የሚንቀሳቀስበትን ቦታ ባላውቀውም የምፍበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ ንፋስ መውጫን አላውቀውም፡፡ የቦታውን ሥም ስሰማ ደስ አለኝ፡፡ ንፋስ መውጫን ከሚያውቁ ሰዎች መሰረታዊ ናቸው ያልኳቸውን መረጃዎች ሰበሰብኩ፡፡ ሁሉም ቦታ የሚገኙ ነገሮችን እየገለኩ ታሪኩን ፃፍኩት፡፡
ከማህሌት ጀምሮ ስራዎችህን በሙሉ አንብቤያለሁ፡፡ አፃፃፍህ እያደገ ሲመጣ የመጀመሪያ ስራዎችህን እያየህ በዚህ መልኩ ብፈው ብለህ ታውቃለህ?
እንዲህ በፃፍኩት ኖሮ እያልኩ የምቆጭበት ሥራ የለኝም፡፡
ብዙዎቹ ሥራዎች ውስጥ የእለት የሚመስሉ ገጠመኞች አሉ፡፡ ለመፃፍ የምትጠቀምበትን ዘዴ የየእለት ገጠመኝህን እየፃፍክ ታሳድገዋለህ ወይስ አመ ታሪኩን አዘጋጅተህ የየእለት ገጠመኞችህን በታሪኩ ውስጥ ታስገባለህ?
ይህ ጥያቄ ለሁፍ የሚያሳሳህ ነገር ምንድን ነው? የሚል ነገርም አለበት፡፡ ለሁፍ የሚቀሰቅሰኝ ነገር ይህ ነው ብዬ መግለ የምችል አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ በደረቅ መሬት ላይ የረጠበ ትንሽ ቦታ ባይ ገጠመኙ ድርሰት ሊሆን ይችላል፡፡ የራሴን ሥራዎች ሳነብ ጉድለት የመሰለኝ ነገር ሙሉ የድርሰት ሥራ ሊያሰራኝ ይችላል፡፡ አሁን በዚህ አዳራሽ ፊት ለፊታችሁ ተቀምጫለሁ፡፡ ቀይ ጨርቅ የለበሰ ጠረጴዛ ተደግፌያለሁ፡፡ ማይኮችንና ገመዶቻቸውን እያየሁ ነው፡፡ ዛሬ ያየሁት ነገር ቆይቶ ለድርሰት የሚያሳሳ ነገር ሊያመጣልኝ ይችላል፡፡ የማየው ዕቃ፣ ሰው ቦታ... ለሁፍ ያሳሳኛል፡፡
እኔ ሦስት ጥያቄዎች አሉኝ፡፡ ደራሲ ከአገሩ ከወጣ ከባህር የወጣ ዓሣ ይሆናል ይባላል፡፡ እርስዎ በውጭ እየኖሩ መቼቱን ኢትዮጵያ ያደረገ መፃህፍት ፈዋል፡፡ እንዴት ነው? በመፃህፍቶችዎ የልጅነት ትዝታዎችን አቅርበዋል፡፡ ስለዚህስ ምን ይላሉ? እንደሚታተምልዎ እርግጠኛ ሳይሆኑ ዝም ብለው በተከታታይ የመፃፍ ልምድ ያለዎት ይመስላሉ፡፡ አስቸጋሪ ነገር ይመስለኛል - ጉልበት የሚሰጥዎ ምንድነው?
ወደ ውጭ አገር ስሄድ ትውስታዬን እዚህ አገር ትቼው አልሄድኩም፡፡ በአብዛኛው የምፈው ባለፈው መቼት ላይ ሆኜ ነው፡፡ ስፍ ድሮ ያየሁትን ለማስታወስ እሞክራለሁ፡ ያንን ማስታወስ ከቻልኩ ለመፃፍ የግድ በአገር ውስጥ መኖር የለብኝም፡፡ ለእኔ እነዚህ በቂዬ ናቸው፡፡ ያልተኖረ ስለማይፃፍ ከትውስታዬ በመነሳት የምፈው ለዚህ ነው፡፡እንደማይታተም እያወቁ መፃፍ አያስጨንቅም ወይ? ለሚለው፤ የምፈው ለማሳተም አይደለም፡፡ ለሁፍ ስነሳ መንፈሴ ብቻ ሳይሆን ገላዬ በሙሉ በሆነ ነገር የተሞላ ይመስለኛል፡፡ ያንን ለማስተንፈስ መፃፍ ስላለብኝ እፋለሁ፡፡ ይቀመጣል፡፡ አሳታሚ መኖሩን ሲወራ ነው የማውቀው፡፡
መፃህፍትህ ላይ ስዕሎችን ትጠቀማለህ፡፡ ምንድነው ምክንያትህ? ከመፃህፍቶችህ በአንዱ ላይ ደግሞ ብዙ አሞራዎች አሉ፡፡ ለምንድነው አብዝተህ የተጠቀምከው?    
ስዕል ብዙ አልጠቀምም፡፡ ከተጠቀምኩም በምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ ግራጫ ቃጭሎች ውስጥ የድንጋይ ስዕል አለ፡፡ ቴክኒካል ግዴታ እየሆነብኝ የማስገባው አለ፡፡ በቃላት መግለ የማልችላቸውን ነገሮች በስዕል አስቀምጣለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ እኔ ብቻ ሳልሆን አንባቢውም ይጠቀማል፡፡ አሞራዎቹን አንዱን ታሪክ ከሌላው ጋር አገናኝ ሆነው ነው ያስገባኋቸው፡፡ አንባቢውም አሞራዎቹን መረዳት ያለበት ከታሪኩ ጋር እያዛመደ ነው፡፡
ሥራዎችህን ሳነብ የሰዎችን አካሄድ፣ አቀማመጥ፣ አነጋገር... በየእለቱ በትኩረት እየተከታተልክ ማስታወሻ የምትይዝ ይመስለኛል፡፡ በመጀመሪያ ይህ ግምቴ እውነት ነው ወይ? ከአገር ከመውጣትህም በፊት ይህ ባህርይ ነበረህ? ሌላው ጥያቄዬ በአፃፃፍ ተእኖ ያሳደረብህ በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ ማን አለ?
በልጅነቴ ነገሮችን እንዴት እመለከት እንደነበር አላውቅም፡፡ ግን ያን ጊዜ ያየሁትን እያስታወስኩ ነው የምፈው፡፡ የማን ተእኖ አለብህ? ለሚለው እኔ ሥራዬን ዝም ብዬ መስራት እንጂ ማን ተእኖ አሳደረብኝ ብዬ አላስብም፡፡ ወይም ሌላ ደራሲ አላይም፡፡ ጥያቄው ተደጋግሞ ይቀርብልኛል፡፡ እኔ የማንም ተእኖ የለብኝም፡፡ ተእኖም አልፈራም፡፡ ተእኖ አለበት ብሎ የሚያምን ካለ ማጥናት ይችላል፡፡ ለእኔ ግን ወረቀቴ፣ ራሴና እኔ ነን ያለነው፡፡
እዚህ ላይ ለመድረስህ ሚስጢሩ ምንድነው? ከተፈጥሮ የተሰጠህ ችሎታ ወይስ በብዙ ጥረትና ድካም ነው እዚህ የደረስከው?
የሄድክበት ደረጃ ምን ይመስላል ለሚለው እውነቱን ለመናገር ዝም ብዬ እየፃፍኩ፣ እየፃፍኩ እዚህ ነው የመጣሁት፡፡ ሌላ ትዝ የሚለኝ ነገር የለም፡፡
ዛሬ በዚህ መድረክ በሥራዎችህ ላይ የጥናት ሁፍ ያቀረቡት ምሁራን ከሥራዎችህ ተነስተው ስለምትከተለው ፍልስፍና ትንተና አቅርበዋል፡፡ አንተ ምን ትላለህ? ተእኖ ቢያሳድሩብህም ባያሳድሩብህም በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ የምታደንቃቸው ፀሐፍት እነማን ናቸው?
ጥናት አቅራቢዎቹ ስላቀረቧቸው የፍልስፍና አይነቶች እኔም ከየመሐፉ አነባለሁ፡፡ በፍልስፍናዎቹ ውስጥ ያሉትን ቴክኒኮች እየወሰድኩ ድርሰቴን ለመፃፍ አልሞክርም፡፡ እኔ የድርሰቴን ቅር የማገኘው ከህይወት ነው፡፡ በ1960ዎቹ የማውቀውን ሰው ከ30 አመት በኋላ ሳገኘው ሽበታም፣ ራሰ በረሀ... ከሆነ ምን ሆነህ ነው ብዬ መጠየቅ አያስፈልገኝም፡፡ የዓመታት ጉዞውን መገመት በቂዬ ነው፡፡ እኔ ድርሰትን ከህይወት እንጂ ከፍልስፍና አልቀዳም፡፡ ፍልስፍናዎቹ ግን ይገቡኛል፡፡
የጥሩ ደራሲ ሥራ ሳነብ ከዚያ በኋላ እፈራለሁ፡፡ የደራሲውን ሥራ ዳግመኛ ላላነብም እችላለሁ፡፡ ቀንቼ ሊሆን ይችላል፡፡ የላቲን አሜሪካ ፀሐፊዎችን ሥራ ማንበብ ደስ ይለኛል፡፡ ግን እንደነሱ ለመፃፍ አልሞክርም፡፡ የራሴን ዘዴ ለመፍጠር እጥራለሁ - ተጨንቄ ግን አይደለም፡፡
ሥም ተግባርን ይመራል ይባላል፡፡ ለስምህ መነሻ የሆነው ..አደመ.. የሚለው ግሥ ትርጉም ያማረ ማለት ነው፡፡ ሥምህ ሰፊና ጥልቅ ነው፡፡ በሥራዎች ላይም ባህረ ሃሳብ አለ፡፡ አዳም እንዴት ተባልክ? በግዕዝ መፃህፍት ውስጥ የቅዱሳን ሥም በቀይ ይፃፋል፡፡ አንተም በግራጫ ቃጭሎች ውስጥ ቀይ ቀለም ተጠቅመሃል፡፡ እየተረሱ ስለመጡት ስለ ስምንቱ አቅጣጫዎች ፈሃል፡፡ እነዚህን ለምን አመጣህ? ለእኔ የተሰበረውን ድልድይ እየቀጠልክ ያለ መስሎኛል...
ሥሜ አዳሙ ነበር፡፡ ኃይለኛ ስለመሰለኝ አዳም አልኩት፡፡ በቀይ ቀለም ለመፃፍ የሞከርኩት በቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ እንዳለው ያንን ቅር ጠብቄ በተዋረድ ለመፃፍ ፈልጌ አይደለም፡፡ የእኔ ሥራ የሰው ለሰው ግንኙነት ነው፡፡ ድርሰት ለማህበራዊ ሃሳቦች ቦታ ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው አንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ ቢሳተፍ ሌላኛው ጫካ ውስጥ ቁጭ ብሎ የቅጠሎች እንቅስቃሴ ቢያይ ሁለቱም ላመኑበትና ለፈለጉት ጉዳይ ከእድሜያቸው ላይ ጊዜ ቀንሰው ሰጥተዋል፡፡ ሁለቱም የሚፈልጉትን አግኝተዋል፡፡ ጥቁርና ቀይ ቀለምን ስጠቀም ከዚህ በተለየ አይደለም፡፡

Read 7086 times