Sunday, 24 July 2011 07:21

..ያረፈዱ ለቀስተኞች..

Written by  ዶ/ር ፍቃዱ አየለ feke40ayema@gmail.com
Rate this item
(0 votes)

በሐምሌ9 ቀን 2003 ዓ.ም በወጣውአዲስአድማስጋዜጣላይ..ሳይንሳዊማስረጃወይስማወናበጃ..የሚል    ጽሁፍአነበብኩኝ፡፡ሐፊው ጻፋቸውቃናአክራሪ..እምነተቢስ..መሆናቸውግልጽነው፡፡እኝህ ሰው ..በሃሳብ ሾተላቸው.. ልክ ሊያስገቡኝ በ..ምንም የለማውያን.. መንፈስ ብቅ ማለታቸው ገረመኝና ይህችን ያህል ነገር እጽፍ ዘንድ እንደገና በአዲስ አድማስ በኩል የብዕር ኩርኩሜን ብቅ አደረኳት፡፡ መቼም ማሰብ ካለማሰብ እጅጉን የሚልቅ ለመሆኑ ብዙ ማጣቀሻ አያሻውም፡፡

ሆኖም ማሰብና ማውጠንጠን የ..እኛ.. ብቻ ነው ተብሎ አሳቢነትን በጅምላ እንደተቆጣጠሩ አድርጎ ራስን በመሰላሉ ጫፍ ላይ ከኮፈሱ በኋላ ..አያስቡም.. ለተባልነው ለእኛ (ለምናምን) የለቅሶ G_ም ደርድሮ፣ ሙሾ ማቅለጥ የተጭበረበረ ለቅሶ ነው ባይ ነኝ፡፡ ባለፈው ሳምንት የተጭበረበረ ለቅሶን ለማዳመቅ የሚመስሉ ጽሁፎች በዚህች ጋዜጣ ላይ ተሰድረው አንብቤአለሁኝ፡፡ ሁሉንም ለመዳሰስ ጊዜ ስላጠረኝ ከነዛ መጣጥፎች መካከል በቀጥታ በሚመለከተኝ እና ያረፈዱ ለቀስተኞች ዘይቤ ባለው መጣጥፍ ላይ ነው ያተኮርኩት፡፡
እኝህ ያተኮርኩባቸው ሃፊ ታዲያ ስለምናምን ሰዎች ሲያብራሩ ..ሳይንሳዊ ቅጥያ መጠቀማቸው ሰዎች ለሳይንሳዊ አስተሳሰብ ያላቸውን ክብር ተገን በማድረግ ማደናገርና... እምነታቸው ባዶ ተስፋ ሳይሆን ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ለማስመሰል ነው.. ብለዋል፡፡ ይህንን ሲሉ ታዲያ ተአማኒነትን ለማጠናከር የአንዳንድ ፈረንጆችንም ስም በዋቢነት ጠቃቅሰዋል፡፡ ዳሩ ግን እኛን ከከሰሱበት ክስ አንጻር እስከ ዛሬ ስንጽፋቸው ከነበሩት ብዙ መጣጥፎች የተወሰኑትን ብቻ ያነበቡ መሆናቸውን አሳይቶኛል፡፡ ሆኖም አንድ በደንብ ያልተገነዘቡት የ..እኔ ነገር.. አሉ እሱም፣ መከበርና መሞገስን በተመለከተ ያለኝ አቋም ሳይንስን አለማሽሞንሞን መሆኑን ነው፡፡ ሳይንሳዊ ነገሮችን መጥቀሴ በሳይንስ እያባበልኩኝ ሳይንስ ተኮር የሆናችሁትን እናንተን በ..ያለ አቻ ጋብቻ.. ለማጥመድ ፈጽሞ አይደለም፡፡ መቼም ቢሆን እኔ ..እምነቴ ሳይንስ ነው.. አላልኩም ወይም እምነቴ ሳይንሳዊ ነው ብዬ አልተሟገትኩም፡፡ ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ..ሳይንስ.. ተብሎ ሰው የሚያሸበሽብለትም ..ግኝትና ግምት.. በቃሉ ተመዝኖ ይደቆሳል ወይም ይገነባል ብዬ አውጄአለሁ፡፡ ለእኔ ሳይንስ የሚከበር፣ የሚቆላመጥ ወይም የሚሰገድለት ሳይሆን መገልገያዬ ነው፡፡ አለቀ፣ ከዛ በላይ ትርጉም የለውም፡፡ እገለገልበታለሁ ብዬ የያዝኩትን ተደምሳሽና ጠፊ ከንቱ ነገር፣ ገና ለገና እምነታቸው ያደረጉት ያከበሩትና በላያቸው ላይ ያነገሱት እልፍ አእላፋት እምነተ ቢሶች አሉና እነሱ ቅር እንዳይሰኙ፣ እምነቴንም እንዳያጥላሉት በእምነቴ ላይ ..ሳይንስ.. የሚል ቅጥያ አልቀጥልለትም፡፡
ሳይንስን የሁሉም ነገር ቁልፍ አድርጎ በሳይንስ ላይ ተስፋ ጥሎ ..ሳይንስ.. ሃይማኖቴ  ማለት ለእምነተ ቢስ የመጀመሪያም የመጨረሻም ተስፋው ነው፡፡ በእኔ ዘንድ ግን ሳይንስ እዚያ ደረጃ የሚያደርስ ግርማ የለውም፡፡ ሳይንስ ብቻውን ገለባ ነው፡፡ ደጋግሜ እንደፃፍኩት ምናልባትም መልሼ ለማሳየት እንደምሞክረው በ..ሳይንስ.. መገልገል የሰው ሁሉ መብት ነው፡፡ ሳይንስ እና እምነት ለየቅል ናቸው፡፡ ሳይንስ ለሚያምኑም ለማያምኑም የጋራ መገልገያ ነው፣ ችግሩ እምነተ ቢስ የሆኑ ሰዎች ሳይንስ የኛ ስለሆነ ..ሳይንሳችንን.. አትንኩ አይነት አሸሼ ገዳሜ መያዛቸው ነው፡፡
በሳይንስ ለመገልገል ከሰው የሚጠበቀው ..ጥረትና ትጋት.. ብቻ ነው፡፡ ማመን ወይም አለማመን ግን አለምን የመመልከቻ እይታ ነው፡፡ አንዱ ያለመነር እውነታውን ካላየሁ ብሎ ከእምነት ተነጥሎ ይባዝንና እምነተ ቢስ ተብሎ ተቅበዝባዥነትን ይጎናፀፋል፡፡ ሌላው የእምነትን መነር አድርጎ ..ያለመነር.. ሊታይ የማይቻለውን በእምነት በኩል ያያል፡፡ አንዱ ..እግዚአብሔር አለ.. ይላል፤ ሌላው ..የለም.. ይላል፡፡ ልዩነቱ እሱ ነው፡፡
ሳይንስን የሙጥኝ ካሉ አማኞች ወይም እምነተ ቢሶች ጎራ አለመሆኔን ደጋግሜ አብስሬ እያለ ሳይንሳዊ መሆኔን ለማስረዳት የምፍጨረጨር ተደርጌ መከሰሴ ያልሆንኩትን ..ነህ.. ብሎ አቅልሞ ለኢላማ ለማመቻቸት ነው፡፡ ሳይንስ ስለፍጥረት አመጣጥ የተመቱ መላምቶች እንጂ ግኝቶች የሏትም፡፡ እናም ስለ ፍጥረት መጀመሪያና መጨረሻ በኩራት የመናገር ብቃት ሊኖራት አይችልም፡፡ የተናገረችም ጊዜ ሳይንስነቷን አቁማ ሃይማኖት ትሆንና ከሌሎች ሀይማኖቶችና አመለካከቶች ጋር ግጭት ውስጥ ትገባለች፡፡ ሁሉም ሳይንሳዊ መላምቶች የሰው ድካም ውጤቶች ናቸው፣ ስለሆነም ..የማይሻር ቃል.. የመሆን አቅም የላቸውም፡፡ ሲገለበጡና እርግፍ ተደርገው ሲጣሉ እያየን ነው፡፡ ታዲያ የሃምሌ ዘጠኙ ..ለቀስተኛ.. ፀሐፊ፤ የተሻሩትን የ20ኛው ክፍለ ዘመን የእነ ጆን ኤዲ   (John Eddy) እና Aram Boornozian (አራም ቡርናዚያን) መላምቶች ዛሬም ድረስ ሳይንሳዊ ናቸው ብዬ እንደተቀበልኩ አይነት ለማድረግ በሁፎቼ ያልጠቀስኳቸውን እነዚህን ሰዎች የሁፎቼ መሰረት አድርገው ሊያሳጡኝ ከጅለዋል፡፡
ሃንስ ቤዝ (Hans Bethe) የተባለ የፊዚክስ ሊቅ በ1939 ዓ.ም የሃይን የሙቀትና የሃይል ምንጭ በተመለከተ አንድ መላምት መታ፡፡ ይህ በ1967 ዓ.ም የኖቤል ሽልማትን ያቀዳጀው መላ ምት |Nuclear fusion´ የ..ኒውክለር ውህደት.. የሚባል ሲሆን የሃይድሮጅን እምብርት የሆነው ..ፕሮቶን.. ቅጣ ያጣ ፍጥነት የሚፈጥረው የጥቃቅን መዋቅሮች መቀያየጥ ውጤት ነው፡፡ ይህ ሂደት ከፍተኛ ሙቀትን የሚጠይቅ እጅግ ግለታም ውህደት ነው፡፡ ክብደት ወደ ኃይልነት የሚቀየርበት የጥቃቅን መዋቅሮች ስነ እንቅስቃሴአዊ ቀመር ነው፡፡ ያም ቀመር በ E=mc2  መብራራቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ መላምት ድምዳሜ ሃይ ይህን ትርምስ መሰረት አድርጋ ከጨረር በተጨማሪ ..neutrino´ ..ኒውትሪኖችንም.. ትረጫለች፡፡ እነዚህ ኒውትሪኖች በጠጣር ነገሮችም ውስጥ ጭምር በቀላሉ ማለፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ እነሱን ነጥሎ መያዝ ቀላል አልነበረም፣ ..ምትሃተኛ.. ባህሪያቸው ለጥናት አስቸጋሪ እንዲሆኑ አድርጓቸውም ቆይቷል፡፡ ሆኖም ይህ ..ምህታታዊ.. ባህሪያቸው የፀሃይን ውስጠ ምስጢር ለመረዳት ጠቃሚ መሆኑም መካድ የለበትም፡፡
ፀሐይ ለብዙ ቢሊዮን አመታት የሚያበራ አብረቅራቂ ፍንጣቂና ከፍተኛ ሙቀት የማመንጨቷ ምክንያት ..Nuclear fusion´ መሆኑን የሃምሌ ዘጠኙ ሃፊ በፀሃይ ሆድ ውስጥ ከርመው ያረጋገጡት ያህል በመተማመን ሊያስረዱን ይሞክራሉ፡፡ ሳይንሳዊ ሃቅ የተባለውን ..Nuclear fusion´ በእሳቸው ግምገማ ሳይንስ ..የማናውቅ.. አማኞች እንደካድነው አድርገው ..ጉድ ያፈሉ አዋቂ.. መሆናቸውን ለማሳየት ተንጠራርተዋል፡፡ ኒውኩለራዊ የንጥረ ነገሮች መንተክተክ ፀሃይ ሙቀትና ብርሃኗን ከየት እንዳመጣች ለማብራራት ሲባል የተመታ ..መላምት.. ነው እንጂ ግኝት አይደለም፡፡ የምናምን ሰዎች ሁሉ ..የተሰወሩት ኒውትሪኖች ችግር (Missing problems)´ ተብሎ የተሰየመን መከራከሪያ፣ ይህን መላምት ላለመቀበል እንደምንጠቀም አድርጎ ያላልነውን ማለት ..እምነት አልባዊ ፈጣጣነት.. ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ እንግዲህ እስከ ዛሬ ድረስ ካልሰሙ ላሰማዎ ..Missing neutrino´ የሚባል መላምታዊ ክፍተት ሁሉም .. neutrinos´ ከተገኙ በኋላ አክትሟል፡፡ ስለዚህ ..ያልተገኙ ኒውትሪኖች.. የሚባል ነገር የለም፡፡ ግን ጠፉ ተብለው የነበሩትም፣ የተገኙትም ኒውትሪኖች የፀሃይን እድሜ በሰማይ ላይ የሚጽፉ ..እምነት አልባ መናፍስት.. አይደሉም፡፡ ከፀሐይ እድሜ ጋርም የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡
በነገራችን ላይ ከፀሃይ ልብ ውስጥ ይፈልቃሉ ተብለው የሚገመቱት የኒውትሪኖች መጠንና የሰው ልጅ እስከዚህ ክፍለ ዘመን በትክክል ለክቶ ..አሉ.. ያላቸው ኒውትሪኖች መጠን የተለያየ ነበር፡፡ ያ መለያየት ነበር ..ያልተገኙ ኒውትሪኖች ችግር.. ተብሎ ይነገር የነበረው፡፡ የዚህ ችግር መከሰት ምክንያት ግን ኒውትሪኖችን በጨረራዊ ስነ-እንቅስቃሴ ዘዴ ለማጥናት የመሞከር ሳይንሳዊ ሸፋፋነት ውጤት ነበር፡፡
ሆኖም  በኒውትሪኖ ስነ-እንቅስቃሴ ምርምር በ Sudbury neutrino obserbatory (SNO) የመረጃ ጥርቅም (data) ይህ ጥያቄ ተፈቷል፡፡ በሳይንሳዊ ዘዴ እነዚህን ኒውትሪኖች በመጠቀም ፀሃይ ያን ሁሉ ሙቀትና ጨረር ከየት እንደምታመጣው ለመገመት ጥረት ሲደረግ መክረሙ ግን የሚረሳ አይደለም፡፡ ሆኖም ..የኒክውለር ውህደት.. መላምት ፀሃይ 1/3ኛ የሚሆን ሃይሏን ከየት እንደምታመጣው ለመመለስ አልቻለም ነበር፤ ምክንያቱም 1/3ኛ የሚሆነው የኒውትሪኖች መጠን የት እንደገባ ማወቅ የዛ ዘመን ችግር ነበርና ነው፡፡ ስለዚህ የቀረውን ሃይል bKelvin Helmholtz Collapse መላምት መሙላት ግድ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ግን ጠፉ የተባሉት ኒውትሪኖች ስለተገኙ የ..Kelvin Helmholtz´ መላምት እንደሌሎች መላምቶች ሁሉ መሻሩ ግድ ሆኗል፡፡
ይህ ዘመን ሙለ በሙሉ የ ..Nuclear fussion´ መላምት ዘመን ነው፡፡ ከዚህ ውህደት ውስጥ የሚመነጩ ሶስት አይነት ኒውትሪኖች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን አሁን ሁሉንም በሶስት አይነት ሳይንሳዊ ዘዴዎች መለየት ተችሏል፡፡ ጉዱ ግን በእንቅስቃሴ አልባነት ጊዜ ምንም ክብደት የላቸውም ተብለው ይታሰቡ የነበሩ ኒውትሪኖች እንደዚያ አለመሆናቸው አብሮ መታወቁ ነው፡፡
እንግዲህ የሃምሌ ዘጠኙ ሐፊ የደስታ መነሻ ሃይ የሙቀትና የሃይል ምንጭዋ ..Nuclear fussion´ ከሆነ በመጽሃፈ ዝግመተ ለውጥ በኩል በታላቁ ፍንዳታ ስር የተነገረላትን እድሜ ስለምታሟላ ..አለማመናችን.. ከአደጋ ተረፈ ብሎ ለቅሶን በዘፈን ለመቀየር ነው፡፡
ሆኖም የ ..Nuclear fussion´ መላምት መቶ እጅ እውነት እንኳ ቢሆን ..አንድ በዚህ መልኩ ሙቀትና ብርሃን የሚሰጥ ኮከብ ለብዙ ሚሊዮን አመታት ያለችግር ሊቀጥል ይችል ይሆናል.. ለሚለው ክርክር መልስ ይሰጥ እንደሆነ እንጂ ..ሃይ የማያበራ የንዳድ ምንጭ አላትና እድሜዋም በቢሊዮን የሚቆጠር ነው.. የሚል ድምዳሜ ላይ አያደርስም፡፡ እሱም ብቻ ሳይሆን የሃይን ..ውስጣ ውስጥ.. ለማጥናት ዋንኛ የሚባሉት ኒውትሪኖዎች እያሳዩ ያሉት ተቅበጥባጭ (Oscillatory) ባህሪ ማንም እንዳሻው እንዳይደነፋ ምክንያት ናቸው፡፡
ያም ሆነ ይህ ..የሃምሌ ዘጠኙ ሁፍ መጨረሻ ምንድነው?.. ቢባል ..እግዚአብሔር የለምና አትፃፍ.. ልክ የእግዚአብሔርN መኖር በሳይንሳዊ መንገድ ለማረጋገጥ እየሞከርኩ እንደነበርኩ አይነት አድርጎ ያችን ..ኮሽ ኳሻ.. ሳይንሳቸውን በመከታነት እየጠቀሱ ..ማንነቴን አሳየሁህ ገና ደግሞ አሳይሃለሁ.. አይነት ፉከራ ነው፡፡ ብጽፍም ባልጽፍም፣ ሳይንስ ባይደርስበትም እግዚአብሔር ካለ እኔ ባልለውም ይኖራል፣ ከሌለ ደግሞ እኔና መሰሎቼ አለ ስላልነው ለእኛ ሲል አይኖርም፡፡
ለአለመኖሩ ..ሳይንሳዊ.. ተመክሮን መሰረቱ ያደርጋል፣ እኔ ደግሞ አለ ስል ቃሉን መሰረቴ አደርጋለሁ፤ እግዚአብሔር የሌለ ቢሆን እንኳ ተጠያቂው እኔ አይደለሁም፤ ቃሉ እንጂ ምክንያቱም መነሻዬም መድረሻዬም ቃሉ ነውና፡፡ ሁሉንም በቃሉ እመዝናለሁ፣ ቃሉ ልክ የሚለውን ልክ ብዬ እቀበላለሁ፤ ቃሉ ልክ ያላለውን ልክ አይደለም እላለሁ፤ የምተማመነው በራሴ አይደለም፤ በቃሉ እንጂ፣ ለማያምን እንቆቅልሽ የሚሆንበትም ይህ ነው፡፡ እስከአሁን ግን ቃሉ ሲጠቀልል እንጂ ሲጠቀለል አላየሁም፡፡ ስለዚህ እኔ አለ የምለው እግዚአብሔር በሳይንስ አይረጋገጥም፡፡ ምክንያቱም ..አለም በጥበቧ እግዚአብሔርN አላወቀችም.. ተብሎ ተጽፎአልና፡፡
ብዙ ሳይንሳዊ መላ ምቶች አሉ፡፡ አንዱን መላምት ጥሎ ሌላውን የመቀበል ውሳኔ ላይ የሚያደርሰን ከየአቅጣጫው የሚወረወረው ..ሳይንሳዊ.. ትንታኔ አይደለም፤ ነገር ግን አስቀድመን የተቀበልነው ጥቅል የአስተሳሰብ መነሻ ነው፡፡ ያ ጥቅል ያስተሳሰብ መነሻ ደግሞ ..አለማመን.. ወይም ..ማመን.. ይባላል፡፡ የማያምን ወይም አምኘዋለሁ የሚለውን መጽሐፍ ለማያምኑት ሲል የሚያመቻችም ..ያለሳይንስ.. አለቀልን የሚል ሰው፤ ፍጥረት በዝግመት ተገኘ ብሎ ያምናል፡፡
የሚያምን ደግሞ አምኘዋለሁ የሚለው መጽሐፍ ..ፍጥረታት በእግዚአብሔር መሻትና ውሳኔ በእግዚአብሔር ተጠርተው ተከሰቱ.. ይላል፡፡ የምርምሮቹና የምርምር ውጤቶቹ ብዛትና ልፍላፌ አጨናባሪ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ነው፡፡ ምክንያቱም ሳይንስ የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ስላልሆነና መቶ በመቶ የማወቅ አቅም ስለሚያጥረው የመሻሻል እና የመለወጥ ብቻ ሳይሆን የመደምሰስ እድሉ ግልጽ ነው ስለዚህ ይመዘናል እንጂ አይመዝንም፡፡
ከእየስፍራው የሚረጩ ..ሳይንሳዊ.. መረጃዎችን መቀበል አለመቀበል የሚወሰነው አለምን በምንመለከትበት የአስተሳሰብ ወይም የእምነት አይነት እየለካን ነው፡፡
ስለዚህ እኔ የምቀበለው ሳይንሳዊ ትንታኔ ሁሉ ከእምነቴ አንፃር ልክ የሆነውን ነው፣ ያኛውም እንደዚያው ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሳይንስ የማያስተማምን መሳሪያነቱ፡፡ እኛ ግን ..በሐዋርያትና በነብያት መሰረት ላይ ተመስርተናል የማእዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ነው.. ተብሎ እንደተጻፈ መሰረታችን ቃል እንጂ ተገለባባጭ ሳይንስ እንዲሆን አንፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር የቃሉን በረከት አብዝቶ ያፍስስልን እያልኩ የዛሬን ልሰናበት፡፡

 

Read 4614 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:26