Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 12:17

..ተጨማሪ የምግብ እርዳታ የሚባለው ምን ተበልቶ ነው..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፤ የመኢአድ ዋና ፀሐፊ
4.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው በመንግስት ቢነገርም፤ ቁጥሩ ይህ ብቻ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በብልሹ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በሙስናና በአላስፈላጊ ወጪዎች ለችግር ተዳርጓል፡፡ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ የሚባለው መጀመሪያ ምን ተገኝቶ፣ ምን ተበልቶ ነው? አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ጉርስ አጥቶ፤ በሃገሪቱ ታሪክ እጅግ የከፋ ድህነት ላይ ደርሷል፡፡

መንግሥትና ህዝብ ሆድና ጀርባ በሆነበት፣ ሙስና በተንሰራፋበት፣ በዚች ሀገር ጉዳይ የሚመለከታቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆኑ ምሁራን በአስተሳሰብ ሳይሳተፉ በጥቂት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በተዘጋጀ ኮንትራት በተአምር ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያንም ማሳደግ አይችልም፡፡ ከገጠመን የረሃብ ማጥ ሊያወጣን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ ልትወጣ የምትችለው፤ የተረጋጋ የፖለቲካ አካሄድና ሰላም ሲኖር፤ እንዲሁም ከምንም በላይ ሙስና ከዚች ሀገር ሲወገድ ነው፡፡
ገዢው ፓርቲ የዚችን ሀገር ችግር ይፈታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ በሥልጣን ላይ እንዴት እቆያለሁ የሚል ነው ሃሳቡ፡፡
የህይወት ዘመን ተረጂ ተሁኖ፣ በልመና ሀገር አያድግም፡፡ ሀገራዊ በሆነው ጉዳይ ብሔራዊ ጥሪ ተደርጎ፤ አገር እና ትውልድን ለማዳን፤ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር ለማውጣት ርብርብ ካልተደረገ በስተቀር መፍትሔ አይመጣም፡፡ በከተማ ውስጥም የኑሮ ውድነቱን የፈጠረው ሙስና ነው፡፡ykt¥WS ገመናውን ሸፍኖት እንጂ ሁሉም ችግረኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በቀን ሁለት ጊዜ አይደለም አንድ ጊዜ ጠግቦ እንኳ የሚያድር የለም፡፡  
በዚህች አገር ላይ የተፈጠረውን ችግር እኛ ኢትዮጵያWÃNM\ አለም አቀፉም ኅብረተሰብ ተረባርቦ መፍታት ካልቻለ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቀውስ ይፈጠራል፡፡

Read 5994 times