Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 16 July 2011 11:37

ዛሬ ደራሲ አዳም ረታ ከአንባቢዎቹ ጋር ይወያያል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዛሬ በሀገር ፍቅር ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 3 ሰዓት አንስቶ ደራሲ አዳም ረታ ከአንባቢዎቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ የማህሌት አሳታሚ ድርጅት ባስተባበረው በዚህ ዝግጅት ላይ ደራሲው ከሚያደርገው ውይይት በተጨማሪ ሁለት ምሁራን በአዳም ረታ ሥራዎች ላይ ጥናት ያቀርባሉ፡፡

የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ መምህር የሆኑት የሻው ተሰማና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህሯ ወይዘሪት ፀደይ ወንድሙ ጥናታቸውን ካቀረቡ በኋላ ከታዳሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡    
በዚህ ፕሮግራም ላይ አርቲስት ተፈሪ አለሙ ከደራሲው ሥራዎች ቀንጭቦ በንባብ ከማሰማቱ በተጨማሪ ገጣሚ ነብይ መኮንን ግጥም ያቀርባል፡፡ ደራሲ አዳም ረታ ለሀያ አመታት ከቆየበት የውጭ አገር ኑሮ በቅርቡ መመለሱ የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ ስድስት የልቦለድ፣ የአጭር ልቦለድና የቤሳ ልቦለዶች መጽሐፍትን አሳትሟል፡፡

Read 4987 times

Latest from