Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:27

..የእኔ ጀግኖች.. የስዕል አውደ-ርዕይ አርብ ይከፈታል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በሰዓሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ የተዘጋጁ ከ60 በላይ ስዕሎች የሚቀርቡበት ..የእኔ ጀግኖች.. የስዕል አውደ ርዕይ በመጪው አርብ 5 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዘክር አዳራሽ ይከፈታል፡፡ k3000-50,000 ብር የሚያወጡ ስዕሎች ለገበያው የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ፤ እስከ ሐምሌ 22 በነጻ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በግልና በቡድን መሰል አውደ ርዕይ ሲያቀርብ 11ኛው የሆነው ሰዓሊ ሀይሌ ክፍሌ፤ በእንጦጦ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ የሥነ ጥበብ መምህር ነው፡፡ ስዕሎቹ ወረቀት በመላጥ፣ በድብልቅ ሚዲያ፣ ኮላዥ እና ፐርፎርማንስ አርት ቴክኒኮች እንደተሳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
..ወደ መጣሁበት.. ፊልም ሰኞ ይመረቃል
በጌታቸው አያልቄ የተፃፈው እና ፕሮዲዩስ የተደረገው እንዲሁም በስንታየሁ ሲሳይ ዳይሬክተርነት የተሠራው ..ወደ መጣሁበት.. የተሰኘ ፊልም የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ሲመረቅ ሐምሌ 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ እንደሚመረቅ ተገለ፡፡ የ1፡45 ደቂቃ ርዝመት ያለውን ይህን ፊልም ለመስራት ሁለት አመት የፈጀ ሲሆን ድምፃዊት አቢ ላቀው፣ ሳሚ በየነ እና አልማዝ ሀይሌን ጨምሮ ሌለች አርቲስቶች የተሳተፉበት መሆኑን የዝግጅቱ አስተባባሪ ለታሪክ አድቨርታይዚንግ ገልጿል፡፡

Read 6194 times