Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 16 July 2011 09:59

ኦባማና ግራ የተጋባው የአፍሪካ ፖሊሲያቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

obamaፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት፣ በአፍሪካ የፖለቲካና    የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ለመደገፍ ከአፍሪካ ጐን እንደሚቆሙ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በርካታ አፍሪካዊያንም በኦባማ የአስተዳደር ዘመን፣ በአሜሪካ ከእርሳቸው በፊት ከነበሩት መሪዎች በተሻለ ጠንካራ ግንኙነት እንደሚኖር ጠብቀው ነበር፡፡ በተለይም የአባታቸው የትውልድ አገር ኬንያ መሆኗ አፍሪካዊያን ለዲሞክራሲ ሥርዓት በሚያደርጉት ትግል የላቀ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉም ተገምቶ ነበር፡፡


“Dream from my Father” በሚል በፃፉት መጽሐፉ ላይ ..የአፍሪካ ደም በውስጤ አለ.. በማለት መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ ኦባማ ስልጣን እንደያዙ በአፍሪካ ጉዳይ ላይ እንደተጠበቀው ሳይሆን ብዙ ቁብ ሳይሰጡ፣ በአሜሪካ የውስጥ ፖሊሲ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አመራርን በስፋት ተከትለዋል፡፡ በእርግጥ ኦባማ ስልጣን ከመያዛቸው ከአንድ ዓመት በፊት፣ የአሜሪካን ኢኮኖሚ አደጋ ላይ የወደቀበትና የሥራ አጥ ቁጥርም ያሻቀበበት በመሆኑ የኢኮኖሚ ቀውሱን ለመታደግና እንደ ጤና ፖሊሲዎች ያሉ ጉዳዮችን ለማሻሻል ረጅሙን የስልጣን ጊዜያቸውን በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ እንዲያጠፉ አስገድዷቸዋል፡፡ በሌላም በኩል አሜሪካ በኢራቅና በአፍጋኒስታን ያላትን የጦር ሠራዊት በተመለከትም የወሰዱት እርምጃ በስልጣን ዘመናቸው የገጠማቸው ተግዳሮቶች ናቸው፡፡
ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ችግሮች ከስልጣን ዘመናቸው በፊት የተከሰቱ በመሆናቸው የሥልጣን ዘመናቸውም ፈታኝ እንደሆነ አስቀድመው ተረድተው ነበረ ወደ ስልጣን የመጡት፡፡
በአሜሪካ የውስጥና የውጭ ጉዳይ በርካታ ሥራዎችን መስራት እንደሚጠብቃቸው ከተገነዘቡ በኋላ ነበር የአሜሪካና የአፍሪካ ወዳጅነት መልካም እንደሚሆን የተመኙት፡፡
ባራክ ኦባማ ከሁለት አመት በፊት አፍሪካን ሲጐበኙ፣ የአባታቸውን የትውልድ ሀገር ሳይረግጡ፣ ጋናን ብቻ መጐብኘታቸው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡበት ወቅት፣ ከፍተኛ ደስታና ፈንጠዚያ ተሰምቷቸው የነበሩትን ኬንያዊያን ማስኮረፉ አልቀረም፡፡ ምናልባትም በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ኬንያዊ ኦባማ ሲመረጡ የነበራቸው የብሔራዊ ስሜትና ኩራት ዛሬ እልም ብሎ የጠፋና ብዙም ስሜት የማይሰማቸው ሆኗል፡፡ በእርግጥ ኬንያዊያን ምንም እንኳን በኦባማ ምክንያት የአሜሪካ ዶላር ወደ ደሃዋ ሀገራቸው እንደሚዘንብና እነርሱም እንደ¸Nb¹b¹ù ቀድሞውን ያልጠበቁት ነገር ቢሆንም፣ አንድም ጊዜ ከአብራካቸው በወጣው ልጃቸው የመጐብኘት ዕድል አለማግኘታቸው እንዲከፉ አድርጓቸዋል፡፡ በይበልጥም የኦባማን አርአያ ለመከተል የተነሳሱት አያሌ ወጣት ኬንያዊያን ኦባማን የመከተል ሕልማቸው ብዙ ሊያስጉዛቸው አልቻለም፡፡
ኦባማ ጋናን በጐበኙበት ወቅት አገራቸው በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ እንደከዚህ በፊቱ ጣልቃ እንደማትገባና የአፍሪካ ችግር በአፍሪካዊያን በራሳቸው መፈታት እንዳለበት አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ የሚኖራት ሚና ጣልቃገብነት ሳይሆን፣ አፍሪካዊያን የራሳቸውን ዕድል መወሰን የሚችሉበትን አቅጣጫ ማሳየትና ማስተማር ነው በማለት ገልፀዋል፡፡ የኦባማ ንግግር ቀደምት ለአፍሪካ ነፃነት እና ዲሞክራሲ ይታገሉ ከነበሩት ከእነ ማርከስ ጋርቬ፣ ክዋሚ ንኩሩማ፣ አህመድ ሴኩ ቱሪ እና ኒልሰን ማንዴላ የተወሰደ እንደሆነ “Obama’s Non –Doctrine in Africa” በሚለው ጽሑፉ ጂ.ፓስካል ዘካሪያ ገልጿል፡፡ ምንም እንኳን የኦባማ ንግግር፣ አፍሪካዊያን የተሻለ ነፃነትና ዲሞክራሲÃêE መብቶችን እንዲጠቀሙ በር የሚከፍት ቢሆንም በአፍሪካ በተጨባጭ ያለው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የውጭ እርዳታና ድጋፍ የማያስፈልገው አይደለም፡፡      
በአፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት መታየት፣ የማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት እና የተማረ የሰው ኃይል ቁጥር እየጨመረ መምጣት ሲታይ አፍሪካዊያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው የመቅረፍ አቅሙም እንዳላቸው የሚያመለክት ነው፡፡
ነገር ግን በአፍሪካ በየጊዜው የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ትክክለኛ የፍትህ ሥርዓት አለመኖር እንዲሁም ሌሎች ዲሞክራሲÃêE መብቶችን ለመጠቀም የሚያስችሉ ዕድሎች አለመኖር ሲታይ አፍሪካዊያን የግድ የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደ¸ÃSfLUcW የሚጠቁም ነው፡፡ በሌላ በኩል አፍሪካ ከሌሎች አህጉሮች አንፃር ስትታይ ከፍተኛ የበሽታ ሥርጭት ያለባት አህጉር እንደመሆኗ እና የአህጉሪቱ ኢኮኖሚም በጤና መስክ ያለውን ችግር ሊቀርፍ የሚችል ባለመሆኑ የምዕራባዊያን የዕርዳታ ተቋማት በአህጉሪቱ የጤና ችግር ላይ አይነተኛ ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
የኦባማ ስጋት አሜሪካ ከዚህ በፊት ጣልቃ በገባችባቸው አገራት ሠላምና መረጋጋትን ከማምጣት ይልቅ ጥላቻና ቂምን በማትረፍ አሁንም በአፍሪካ ጣልቃ በመግባት ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም እንደሆነ የሚገልፀው ጄ.ፓስካል ዘካሪያ፤ የአፍጋኒስታን ወይም የኢራቅ ጉዳይ የአፍሪካ ሊሆን አይችልም ይላል፡፡ ለምሣሌ ኦባማ ሙስሊም ናቸው የሚለውን የአንዳንድ አክራሪ ነጮች ትችት ለማሳመን ለአሜሪካ ሕዝብ ቀንና ለሊት በመስራት አስመስክረዋል፡፡
ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በሙስሊም አሸባሪዎች ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በመክፈትም ማንነታቸውን ያስመሰከሩ ሲሆን፣ እንዲያውም በለስ ቀንቷቸው ቢን ላደንን የሚያክል ቀንደኛ አሸባሪ ለማስገደል በቅተዋል፡፡
የቢን ላደን መገደል ለእርሳቸው የፖለቲካ ትርፍን (Political benefit) ሲያስገኝላቸው፣ የሙስሊም አሸባሪዎችን ለማጥፋት ጠንካራ አቋም የላቸውም ለሚሏቸው ደግሞ አንገታቸውን አስደፍተዋቸዋል፡፡ የተቀረው ብዙሃኑ ነጭና ጥቁር አሜሪካዊያን አንጀታቸውን ያራሱ ከመሆናቸው በላይ አድናቆትና ውዳሴ ቸረዋቸዋል፡፡
ነገር ግን ኦባማ አሸባሪዎችን ለማደን ያደረጉትን እንቅስቃሴ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ያልፈለጉት በአፍሪካ ጣልቃ ገብነት የሚያገኙትን የፖለቲካ ትርፍ ከግምት ውስጥ አስገብተው ነው በማለት ጄ ፓስካል ዘካሪያ ይናገራል፡፡ ፀሐፊው ሲቀጥል፣ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ አፍሪካዊያንን የሚጠቅም ቢሆንም እንኳን ለእርሳቸው የፖለቲካ ትርፍ የማያስገኝ ከሆነ ገንዘብንና ጊዜን እንደማባከን አድርገው ነው የሚመለከቱት፡፡ በመሆኑም bxYìlÖጂÃcW ራሳቸውንም ሆነ እኛንም ለማሳመን ይሞክራሉ በማለት ይገልፃል፡፡ ይሁን እንጂ ኦባማ መረዳት ያለባቸው ነገር ወደ ምርጫ ሲመጡ፣ ከፍተኛ ድምጽ በመስጠትና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሙጋቤ አስተዳደር ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በሕዝቡ ላይ በፈመበት ወቅት አሜሪካ ጠንካራ ተቃውሞና ጣልቃ ገብነት ከማድረግ ይልቅ እጇን አጣጥፋ ተቀምጣለች፡፡ ይህም የአሜሪካ የተለሳለሰ አቋም አምባገነኖች ያለገደብ በሥልጣን እንዲቆዩ እያደረጋቸው ነው፡፡
በጊኒም ያለው ሁኔታ ሲታይ የኦባማ አስተዳደር የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያስቀድም ይመስላል፡፡ በጊኒ በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግሥት በኦባማ አስተዳደር መወገዝ ሲገባው፣ ጊኒ ለአሜሪካ በምትሽጠው ከፍተኛ ነዳጅ የተነሳ ከኦባማ አስተዳደር ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መስርታለች፡፡
የኦባማ አስተዳደር በአፍሪካ እስካሁን የተለሳለሰና በጣም ደካማ አካሄድ ከመሄድ ውጪ ጠንካራ ሚና እንዳልተጫወተ የሚተቹት ታዛቢዎች፤ ምናልባት የተሻለ ሥራ ሠርቷል ከተባለ በሱማሊያ ለሚገኙ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በተባበሩት መንግሥታት በኩል እውቅና መስጠቱ እና በሱዳን ለተቀሰቀሰው ግጭት ደግሞ የሱዳን መንግሥት ግጭቱን በአፋጣኝ እንዲያስቆም መጠየቁ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ይሁን እንጂ ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ተቀባይነትና ተሰሚነት እንዲኖራቸው ባለቤታቸው ሚሸል ኦባማ ትልቅ እገዛ እያደረጉላቸው ይገኛሉ፡፡ ሚሸል ኦባማ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ በደቡብ አፍሪካ በመገኘት ባራክ ኦባማ ስለ አፍሪካ ያላቸውን አቋም አሳውቀው ነበር፡፡ ሚሸል ኦባማ በንግግራቸው ሲገል፣ አሁን ባለንበት ዓለም በርካታ ችግሮች የተጋረጡብን መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር፣ የዲሞክራሲÃêE አስተዳደር እጦት፣ የአየር ጠባይ መለወጥና ሌሎችም በርካታ ችግሮች ተደቅነውብናል፡፡ ዓለም አሁን ፊቱን ወደ አፍሪካ በማዞሩ፣ አፍሪካ እነዚህን ችግሮች ለመታደግ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይኖርባታል፡፡ አፍሪካ የምታሳየውን እንቅስቃሴ አለም በአድናቆት የሚመለከተው ነው ብለዋል፡፡
የባለቤቴ አስተዳደር፣ አፍሪካን እንደከዚህ በፊቱ በቀጥታ በመርዳት ላይ ያተኰረ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት በመመስረት አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ የሚያበረታታ ነው፡፡ አፍሪካውያን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና ሙስናን ለመቅረፍ ጠንካራ የዲሞክራሲ ምሰሶዎችን መገንባት እንዲችሉ መነሳሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይም አህጉሪቱ ያለባትን በቂ ምግብ ያለማግኘት ችግር ለመቅረፍ የግብርናውን ዘርፍ በሰፊው ማጠናከርና አዳዲስ ሰብሎችን ማብቀል እንዲሁም፤ አፍሪካውያን እርስ በርስ መደጋገፍና መረዳዳት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ላይ ትልቁን ሚና ሊጫወቱ የሚገባቸው ደግሞ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው ወጣቱ ትውልድ ነው በማለት ገልዋል፡፡

 

ሚሸል ኦባማ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ፣ በአፍሪካ አያሌ ወጣቶች በችግርና በሰቆቃ ኑሯቸውን እየገፉ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ፕሬዝዳንት እጅግ የተንደላቀቀና የቅንጦት ኑሮ የሚኖሩበት መሆን የለበትም፡፡ ብዙ አፍሪካውያን መሪ ሲባል የአገሪቱን ሕግ የሚያረቅ፣ የጦር ኃይሉን በሙሉ ሥልጣን የሚያዝና ከሕግ የበላይ የሆነ አድርገው መመልከታቸው ፍም ስህተት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት እንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦችን ቁጭ ብለን የምንመለከትበት ወይም እንዲቀጥሉ የምንፈቅድበት መሆን የለበትም፡፡ እውነተኛ መሪ ለአፍሪካ ያስፈልጋል፡፡ እውነተኛ መሪ ምንድነው? እውተኛ መሪ ሊሆን የሚችለው በመጀመሪያ ቤተሰቡን በአግባቡ ሊመራ የሚችል፣ ከዚያም የአካባቢውን ማኅበረሰብ በጥሩ ሁኔታ በመምራት የሚታወቅ ሲሆን ኋላ ላይ አገርንና ሕዝብን መምራት ይችላል፡፡
መሪነት በቤተ መንግሥት ወይም በፓርላማ የሚጀምር አይደለም፡፡ መሪነት የሚጀምረው ከታች ነው፡፡ በአንዴ ላይ ወጥቶ ታሪክን መቀየር አይችልም፡፡ በመጀመሪያ መሪው ከመምራቱ በፊት ራሱ የተለወጠ መሆን አለበት፡፡ መሪነት ጥቂት ግለሰቦችን በመምራት እያደገ የሚሄድ ነው በማለት ገልዋል፡፡
እናንተ ወጣት አፍሪካውያን ከእናንተ ብዙ ይጠበቃል፡፡ መሪዎች በሠሩት ሥራ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ በየትኛውም ሁኔታ ታማኝ መንግሥት እንዲኖር፣ መንግሥት ሙስናን እንዲቆጣጠር፣ ሁሉም ዜጋ የመናገር፣ በነጻነት የማምለክና የፈለገውን የማፍቀር መብት እንዲኖረው ለማድረግ ወጣቶች ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ መንቀሳቀስ ይኖርባችኋል፡፡
አሁን የምናታደርጉት ጥረት ምናልባት የዓለምን ትኩረት ላይስብ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለውጥ የሚመጣው ቀስ በቀስ እንደሆነ ልታውቁ ይገባል፡፡ ለውጥ ሕግ በመለወጡ የሚመጣ ሳይሆን በሰዎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ዕድገት የሚመጣ ነገር ነው በማለት ሚሸል ኦባማ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሚሸል ኦባማ የባለቤታቸውን አስተዳደር ምንም እንኳ ባማሩና ጣፋጭ በሆኑ ቃላት ቢናገሩም አሜሪካ በአፍሪካ ላይ ያላት ፖሊሲ የማይዋጥላቸው በርካታ ፖለቲከኞች አሉ፡፡ በአፍሪካ አሁንም የብዙሃኑን ድምጽ በመውሰድ ሥልጣንን የሙጥኝ ያሉ አያሌ መሪዎች ይገኛሉ፡፡ ሥልጣን በአፍሪካ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እሴቶች ማሳደግ ሳይሆን ከተራው ሕዝብ ልቆና ተፈርቶ የሚኖርበት ነው፡፡ በአፍሪካ ምንም እንኳን ከ20 እና ከ30 ዓመት በፊት አምባገነኖችን ለመጣል የተለያዩ የለውጥ ኃይሎች በመነሳት ሥልጣን ቢይዙም ራሳቸው እንደገና ሌላ አምባገነን ከመሆን ውጪ ዲሞክራሲÃêE መብቶችን ሲያሰፍኑ አልተስተዋለም፡፡ ዛሬም ድረስ አብዛኞቹ አፍሪካውያን በአገራቸው ተሳቀውና ተሸማቀው የችግር ገፈት ቀማሽ ሆነው ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ አገራቸውን ጥለው በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በአረቡ ዓለም ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በተቃራኒው አፍሪካውያን መሪዎች የሕዝቡን ስቃይ ከማየት ይልቅ የራሳቸውን የሥልጣን ዘመን ለማስረዘም ደፋ ቀና የሚሉ ናቸው፡፡ በመሆኑም ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ነጻና ዲሞክራሲÃêE መብቶች ባልሰፈነበት ሁኔታ አፍሪካውያን የራሳቸውን መብት በራሳቸው እንዲፈቱ መግለጻቸው፣ አምባገነኖች በሕዝቡ ላይ የአገዛዝ ቀንበራቸውን እንዲያጠብቁ መፍቀድ ነው በማለት የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡
ሌላው የኦባማ አስተዳደር አፍሪካውያን የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸውን ሲፈቅድ የመገንጠል ጥያቄም በሰፊው መቀጣጠሉ አይቀርም በማለት የሚገልው ጂ. ፓስካል ዘካሪያ፤ ይህ ደግሞ በአፍሪካ ቀድሞ የነበሩ ችግሮች በአዳዲስ ችግሮች እንዲተኩ መፍቀድ ነው በማለት ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ቅዳሜ ነጻ ግዛት የሆነችውን ደቡብ ሱዳንን ተከትሎ ሌሎችም በተመሳሳይ የመገንጠል ጥያቄ እንዲያነሱ ያደርጋቸዋል የሚል ስጋት አረብቧል፡፡
የቡሽ አስተዳደር በሰሜኑና በደቡብ ሱዳን መካከል ለሦስት አስርት ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆም በማስቻል በሁለቱም ወገኖች መካከል የሰላም ድርድር እንዲካሄድ አይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይህ ደግሞ ሁለቱም ሱዳኖች ተከባብረውና ተቻችለው አገራቸውን በአንድ ላይ ለማሳደግ ትልቅ መሠረት የጣለ ነበር፡፡ ነገር ግን ደቡብ ሱዳን በሕዝብ ውሳኔ ድምጽ መገንጠሏ ቢታወቅም አሁንም ከሰሜኑ ጋር ያለው ቁርሾ ገና አልበረደም፡፡ በተለይ የነዳጅ ቦታ እንደሆነች በሚታወቀው የአብዬ ግዛት ምክንያት ሰሜኑና ደቡቡ በቅርቡ ጦርነት ማካሄዳቸው ይታወቃል፡፡ ካርቱም ቁልፍ የሆነውን የነዳጅ ቦታ በማጣቷ ምክንያት ሊኖራት የሚችለውን የኢኮኖሚ ጥቅም ስለሚያሳጣት በደቡብ ሱዳን ላይ ቀጣይ ጦርነት መክፈቷ የማይቀር እንደሆነ YglÚL””ኦባማ የደቡብ ሱዳን መገንጠልን ተከትሎ በሱዳን ጠንካራ ፈተና እንደሚገጥማቸው የተገለ ሲሆን፣ ይህም ሱዳንን ለሁለት ብቻ በመክፈል የሚያበቃ አይሆንም፡፡ በመሆኑም ኦባማ ከደቡብ ሱዳን መገንጠል በኋላ ሌላ ግጭት እንዳይፈጠርና መከፋፈሉ እየተስፋፋ እንዳይሄድ በአልበሽር አስተዳደር ላይ ተገቢ ተጽዕኖ ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለበለዚያ ግን ወደ ሥልጣን ሲመጡ ‘yes we can’ በማለት የተናገሩት በአፍሪካውያን ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደሚሆን ማወቅ አለባቸው በማለት የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡

Read 8541 times Last modified on Tuesday, 19 July 2011 13:53

Latest from