Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 02 July 2011 13:16

1የቤተክህነትና የገዳሙ ውዝግብ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የዛሬ አርባ ዓመት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ ልዕልት ሂሩት ደስታ ለቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አስተዳዳሪዎች የሚያስደስት መልዕክት ያዘለ ደብዳቤ ላኩ፡፡ደብዳቤው ልዕልቷ በደብሩ አውደምህረት ሥር ባሉት ቤተ አማኑኤል እና መድሐኒያለም ቤተKRStEÃN መካከል በ1956 ዓ.ም ያሠሩትን ..ሰባት ወይራ ሆቴል.. ላሊበላ ቤተKRStEÃN በስጦታነት ማበርከታቸውን የሚያበስር ነበር፡፡ገዳሙ ስጦታውን ከተቀበለ አራት ድፍን ዓመታትን እንኳን በቅጡ ሳይቆጠር በደርግ ከተወረሱት በርካታ ቤቶች መካከል አንዱ ሆነና በጊዮን ሆቴሎች አስተዳደር ድርጅት እጅ ወደቀ፡፡

ገዳሙ ስጦታውን ከተቀበለ አራት ድፍን ዓመታትን እንኳን በቅጡ ሳይቆጠር በደርግ ከተወረሱት በርካታ ቤቶች መካከል አንዱ ሆነና በጊዮን ሆቴሎች አስተዳደር ድርጅት እጅ ወደቀ፡፡
የደብሩ ዋና ሐፊ ቀሲስ መንግሥቴ ወርቁ እንደሚሉት፤ ኢሕአዴግ የመንግሥትነቱን ሥልጣን ከተረከበ በኋላ በ1991 ዓ.ም ፕራይቬታይዜሽን ለጠቅላይ ቤተክነት ..ሰባት ወይራ.. የተባለው ሆቴል ንብረትነቱ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ እንዲረከቡ የሚጠይቅ ደብዳቤ መጻፉን እና ቤተክህነቱም ደብዳቤውን መነሻ በማድረግ ገዳሙ ሆቴሉን ለመረከብ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ የሚያስታውቅ ደብዳቤ እንደተጻፈላቸው ይገልፃሉ፡፡
የሆቴሉ ርክክብ የተደረገው ግን እነዚህ ደብዳቤዎች ከተጻጻፉ ከሰባት ዓመት በኋላ፣ በ1997 ዓ.ም ሲሆን ርክክቡም የተፈፀመው ከገዳሙ እውቅና ውጪ በግዮን ሆቴሎች እና በጠቅላይ ቤተክህነቱ መካከል መሆኑን ቀሲስ መንግሥቱ ያስታውሳሉ፡፡
ጉዳዩ በወቅቱ የገዳሙን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አባላት በማስቆጣቱ ሆቴሉ ለገዳሙ የተበረከተ ስጦታ መሆኑን በመግለ እንዲመለስላቸው መጠየቃቸውን እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሆቴሉን እንደ ሌሎቹ የተወረሱ yቤተKRStEÃnþtÜ ቤቶች ከመንግሥት ጋር በተደረገ ልዩ ስምምነት ያስመለሰችው በመሆኑ፣ ንብረትነቱ የእርሷ እንጂ የገዳሙ ሊሆን ስለማይገባ ሆቴሉ በየወሩ ከሚያስገባው 25 ሺህ ብር ኪራይ ላይ 2500 ብር እንዲሰጣቸው ተወስኖላቸው እንደነበር፣ በመካከሉም ይኸው ገንዘብ በአግባቡ እንዳልተከፈላቸው እና አነስተኛ በመሆኑ ላይ ቅሬታ በማሰማታቸው፣ ካለፈው ታኅሣሥ ጀምሮ 5ሺህ ብር እንደተደረገላቸው ቀሲስ መንግሥቴ ያብራራሉ፡፡
በቅርቡም የከተማው አስተዳደር፤ የሆቴሉ ባለቤት ነኝ ያለ አካል የቦታውን ግብር 216 ሺህ ብር  እንዲከፍል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በአድራሻው፤ በግልባ ጩ ደግሞ ለላሊበላ ገዳም በመጻፉ በገዳሙ እና በጠቅላይ ቤተክህነቱ መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ምክኒያት ሆኗል፡፡
ግብሩን ከፍለው የባለቤትነት ደብተሩን መውሰድ የፈለጉት ሁለቱም አካላት ሲሆኑ ጠቅላይ ቤተክህነት ይህንኑ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ፣ በእግድ መያዙን ቀሲስ መንግሥቴ ይናገራሉ፡፡
ከአምስት ዓመታት በፊት ሆቴሉን ለሚያስተዳድር አካል ጨረታ ሲወጣ በወቅቱ በ32 ሺህ ብር ያሸነፈ ሰው እያለ፣ በ25 ሺህ ብር ለሌላ ሰው መከራየቱን፣ የተከራየውም ግለሰብ ኪራዩን በወቅቱ ይከፍል እንዳልነበረ፣ በቅርቡም ሆቴሉን ለማስተዳደር የተረከቡት የባለንብረቱ ተቀጣሪዎች በሆቴሉ ውስጥ የሚገኙትን ጥንታዊ እቃዎች በመኪና ጭነው ሲወስዱ በገዳሙ አባቶች አማካኝነት በፖሊስ መያዛቸውን በመዘርዘር፣ ገዳሙ አጠቃላይ በሆቴሉ አስተዳደር ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል፡፡
ሆቴሉም ከልዕልቷ ለገዳሙ በስጦታ የተሰጠ በመሆኑ የባለቤትነት ደብተሩ ለገዳሙ እንጂ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊሰጥ አይገባም በሚል አጥብቆ ይከራከራል፡፡ በጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊሊጶስ ፊርማ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ አባ ገብረየሱስ ጠቅላይ ቤተክህነት ቀርበው በትናንትናው ዕለት እንዲነጋገሩ ደብዳቤ ስለደረሳቸው፣ የስብሰባውን ውጤት የሰበካ ጉባኤው ጽ/ቤት እና ምዕመናኑ እየጠበቁ መሆኑን ቀሲስ መንግሥቴ ገልፀውልናል፡፡
በጠቅላይ ቤተክህነት የቤቶች አስተዳደር ልማት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት፤ ቅሬታውን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፤ በደርግ መንግሥት በነበረው ሥርዓት የኢትዮጵያ ቤተKRStEÃN በርካታ ንብረቶች ከተወረሱባት በኋላ መንግሥት በሚሰጣት በጀት ትተዳደር እንደነበር አስታውሰው፣ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ እና ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላ መንግሥት እና ቤተKRStEÃN ሊለያዩ እንደሚገባ በመወሰኑ፣ በአዋጅ 47/67 የተወረሱ ቤቶችንም ጨምሮ በልዩ ሁኔታ በየደብሩ kቤተKRStEÃnþtÜ ላይ የተወረሱ ንብረቶችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክነት ማስመለሷን ገልፀዋል፡፡
በላሊበላ ገዳም የሚገኘውም ..ሰባት ወይራ.. ሆቴልም ከእነዚህ አንዱ መሆኑን እና በወቅቱ ሆቴሉ ለቤተክህነቷ ሲመለስም፣ ጊዮን ሆቴሎች አስተዳደር ለተለያዩ እድሳት ያወጣውን 181 ሺህ ብር ወጪ በመክፈል ሆቴሉን ተረክቦ በጨረታ ማከራየቱን ተናግረዋል፡፡
በጨረታው 32 ሺህ ብር ለመክፈል ያሸነፈ አካል እያለ፣ በ25 ሺህ ብር ስለመከራየቱ በወቅቱ ቦታው ላይ ስላልነበሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀው፣ ተዘረፈ የተባለውን ንብረት በሚመለከት ንብረቱ እንዲያዝ ያደረጉትን የገዳሙን አስተዳዳሪዎች አመስግነው፣ ጉዳዩን ፖሊስ በያዘው መንገድ ማጣራቱን እንዲቀጥልበት መወሰኑን ገልፀዋል፡፡ የተያዙት ንብረቶችም እንደ ማንኪያ፣ ሹካ፣ አልጋ እና የመሳሰሉት የሆቴል ዕቃዎች እንጂ በቅርስነት የሚጠሩ ንብረቶች እንዳልሆኑ አብራርተዋል፡፡
በአጠቃላይ ገዳሙም ሆነ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት አንድ አካል በመሆናቸው ጉዳዩን እንደ ችግር እንደማይቆጥሩት የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ ሆቴሎ የተመለሰው lቤተKRStEÃnù በመሆኑ ንብረትነቱ የጠቅላይ ቤተክህነቱ መሆኑን እና ከመንግሥት የተጠየቀውን ግብር ከፍሎ yባለቤትntÜN ደብተር መረከብ ያለበት ጠቅላይ ቤተ ክህነት መሆኑን አበክረው ይናገራሉ፡፡
ለገዳሙ በየወሩ የሚከፈለው 5 ሺህ ብርም ገዳሙ የሆቴሉ ባለቤት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሳይሆን ለሌሎቹ ደብሮች በየወሩ እንደሚሰጠው ድጐማ ሁሉ ለላሊበላም የሚሰጥ ድጐማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከጠቅላይ ቤተክህነት የተላኩ ሰዎች፤ ላሊበላ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የደብሩ አስተዳዳሪ አዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተገኝተው፣ በሥራ አስኪያጁ በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ሰብሳቢነት በተደረገ ውይይት፤ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ እና አባላት በተደረገላቸው ገለፃ፣ ሆቴሉ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ንብረት መሆኑን አምነው፣ ነገር ግን ሌላ አካል በኪራይ ከሚያስተዳድረው ይልቅ ገዳሙ እንዲያስተዳድረው በመጠየቃቸው፣ ኪራዩን በሚመለከት በጥናት ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተገልፆላቸው መለያየታቸውን አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ መንግሥቴ በበኩላቸው፤ ከስብሰባው የተገኘውን ውጤት በሚመለከት የሰሙት ነገር እንደሌለ ገልፀው፣ ተደረሰ ስለተባለው ስምምነት በሚመለከት፤ ውሳኔው ምንም ሆነ ምን በመጨረሻ የሚፀድቀው በአጠቃላይ በቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አባላት እና ምዕመናን በመሆኑ የደበሩን አስተዳዳሪ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀውልናል፡፡

 

የደብሩ ዋና ሐፊ ቀሲስ መንግሥቴ ወርቁ እንደሚሉት፤ ኢሕአዴግ የመንግሥትነቱን ሥልጣን ከተረከበ በኋላ በ1991 ዓ.ም ፕራይቬታይዜሽን ለጠቅላይ ቤተክነት ..ሰባት ወይራ.. የተባለው ሆቴል ንብረትነቱ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ እንዲረከቡ የሚጠይቅ ደብዳቤ መጻፉን እና ቤተክህነቱም ደብዳቤውን መነሻ በማድረግ ገዳሙ ሆቴሉን ለመረከብ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ የሚያስታውቅ ደብዳቤ እንደተጻፈላቸው ይገልፃሉ፡፡ የሆቴሉ ርክክብ የተደረገው ግን እነዚህ ደብዳቤዎች ከተጻጻፉ ከሰባት ዓመት በኋላ፣ በ1997 ዓ.ም ሲሆን ርክክቡም የተፈፀመው ከገዳሙ እውቅና ውጪ በግዮን ሆቴሎች እና በጠቅላይ ቤተክህነቱ መካከል መሆኑን ቀሲስ መንግሥቱ ያስታውሳሉ፡፡ ጉዳዩ በወቅቱ የገዳሙን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አባላት በማስቆጣቱ ሆቴሉ ለገዳሙ የተበረከተ ስጦታ መሆኑን በመግለ እንዲመለስላቸው መጠየቃቸውን እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሆቴሉን እንደ ሌሎቹ የተወረሱ yቤተKRStEÃnþtÜ ቤቶች ከመንግሥት ጋር በተደረገ ልዩ ስምምነት ያስመለሰችው በመሆኑ፣ ንብረትነቱ የእርሷ እንጂ የገዳሙ ሊሆን ስለማይገባ ሆቴሉ በየወሩ ከሚያስገባው 25 ሺህ ብር ኪራይ ላይ 2500 ብር እንዲሰጣቸው ተወስኖላቸው እንደነበር፣ በመካከሉም ይኸው ገንዘብ በአግባቡ እንዳልተከፈላቸው እና አነስተኛ በመሆኑ ላይ ቅሬታ በማሰማታቸው፣ ካለፈው ታኅሣሥ ጀምሮ 5ሺህ ብር እንደተደረገላቸው ቀሲስ መንግሥቴ ያብራራሉ፡፡በቅርቡም የከተማው አስተዳደር፤ የሆቴሉ ባለቤት ነኝ ያለ አካል የቦታውን ግብር 216 ሺህ ብር  እንዲከፍል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በአድራሻው፤ በግልባ ጩ ደግሞ ለላሊበላ ገዳም በመጻፉ በገዳሙ እና በጠቅላይ ቤተክህነቱ መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ምክኒያት ሆኗል፡፡ግብሩን ከፍለው የባለቤትነት ደብተሩን መውሰድ የፈለጉት ሁለቱም አካላት ሲሆኑ ጠቅላይ ቤተክህነት ይህንኑ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ፣ በእግድ መያዙን ቀሲስ መንግሥቴ ይናገራሉ፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት ሆቴሉን ለሚያስተዳድር አካል ጨረታ ሲወጣ በወቅቱ በ32 ሺህ ብር ያሸነፈ ሰው እያለ፣ በ25 ሺህ ብር ለሌላ ሰው መከራየቱን፣ የተከራየውም ግለሰብ ኪራዩን በወቅቱ ይከፍል እንዳልነበረ፣ በቅርቡም ሆቴሉን ለማስተዳደር የተረከቡት የባለንብረቱ ተቀጣሪዎች በሆቴሉ ውስጥ የሚገኙትን ጥንታዊ እቃዎች በመኪና ጭነው ሲወስዱ በገዳሙ አባቶች አማካኝነት በፖሊስ መያዛቸውን በመዘርዘር፣ ገዳሙ አጠቃላይ በሆቴሉ አስተዳደር ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል፡፡ሆቴሉም ከልዕልቷ ለገዳሙ በስጦታ የተሰጠ በመሆኑ የባለቤትነት ደብተሩ ለገዳሙ እንጂ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊሰጥ አይገባም በሚል አጥብቆ ይከራከራል፡፡ በጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊሊጶስ ፊርማ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ አባ ገብረየሱስ ጠቅላይ ቤተክህነት ቀርበው በትናንትናው ዕለት እንዲነጋገሩ ደብዳቤ ስለደረሳቸው፣ የስብሰባውን ውጤት የሰበካ ጉባኤው ጽ/ቤት እና ምዕመናኑ እየጠበቁ መሆኑን ቀሲስ መንግሥቴ ገልፀውልናል፡፡በጠቅላይ ቤተክህነት የቤቶች አስተዳደር ልማት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት፤ ቅሬታውን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፤ በደርግ መንግሥት በነበረው ሥርዓት የኢትዮጵያ ቤተKRStEÃN በርካታ ንብረቶች ከተወረሱባት በኋላ መንግሥት በሚሰጣት በጀት ትተዳደር እንደነበር አስታውሰው፣ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ እና ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላ መንግሥት እና ቤተKRStEÃN ሊለያዩ እንደሚገባ በመወሰኑ፣ በአዋጅ 47/67 የተወረሱ ቤቶችንም ጨምሮ በልዩ ሁኔታ በየደብሩ kቤተKRStEÃnþtÜ ላይ የተወረሱ ንብረቶችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክነት ማስመለሷን ገልፀዋል፡፡ በላሊበላ ገዳም የሚገኘውም ..ሰባት ወይራ.. ሆቴልም ከእነዚህ አንዱ መሆኑን እና በወቅቱ ሆቴሉ ለቤተክህነቷ ሲመለስም፣ ጊዮን ሆቴሎች አስተዳደር ለተለያዩ እድሳት ያወጣውን 181 ሺህ ብር ወጪ በመክፈል ሆቴሉን ተረክቦ በጨረታ ማከራየቱን ተናግረዋል፡፡በጨረታው 32 ሺህ ብር ለመክፈል ያሸነፈ አካል እያለ፣ በ25 ሺህ ብር ስለመከራየቱ በወቅቱ ቦታው ላይ ስላልነበሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀው፣ ተዘረፈ የተባለውን ንብረት በሚመለከት ንብረቱ እንዲያዝ ያደረጉትን የገዳሙን አስተዳዳሪዎች አመስግነው፣ ጉዳዩን ፖሊስ በያዘው መንገድ ማጣራቱን እንዲቀጥልበት መወሰኑን ገልፀዋል፡፡ የተያዙት ንብረቶችም እንደ ማንኪያ፣ ሹካ፣ አልጋ እና የመሳሰሉት የሆቴል ዕቃዎች እንጂ በቅርስነት የሚጠሩ ንብረቶች እንዳልሆኑ አብራርተዋል፡፡ በአጠቃላይ ገዳሙም ሆነ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት አንድ አካል በመሆናቸው ጉዳዩን እንደ ችግር እንደማይቆጥሩት የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ ሆቴሎ የተመለሰው lቤተKRStEÃnù በመሆኑ ንብረትነቱ የጠቅላይ ቤተክህነቱ መሆኑን እና ከመንግሥት የተጠየቀውን ግብር ከፍሎ yባለቤትntÜN ደብተር መረከብ ያለበት ጠቅላይ ቤተ ክህነት መሆኑን አበክረው ይናገራሉ፡፡ለገዳሙ በየወሩ የሚከፈለው 5 ሺህ ብርም ገዳሙ የሆቴሉ ባለቤት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሳይሆን ለሌሎቹ ደብሮች በየወሩ እንደሚሰጠው ድጐማ ሁሉ ለላሊበላም የሚሰጥ ድጐማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በጉዳዩ ዙሪያ ከጠቅላይ ቤተክህነት የተላኩ ሰዎች፤ ላሊበላ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የደብሩ አስተዳዳሪ አዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተገኝተው፣ በሥራ አስኪያጁ በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ሰብሳቢነት በተደረገ ውይይት፤ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ እና አባላት በተደረገላቸው ገለፃ፣ ሆቴሉ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ንብረት መሆኑን አምነው፣ ነገር ግን ሌላ አካል በኪራይ ከሚያስተዳድረው ይልቅ ገዳሙ እንዲያስተዳድረው በመጠየቃቸው፣ ኪራዩን በሚመለከት በጥናት ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተገልፆላቸው መለያየታቸውን አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ መንግሥቴ በበኩላቸው፤ ከስብሰባው የተገኘውን ውጤት በሚመለከት የሰሙት ነገር እንደሌለ ገልፀው፣ ተደረሰ ስለተባለው ስምምነት በሚመለከት፤ ውሳኔው ምንም ሆነ ምን በመጨረሻ የሚፀድቀው በአጠቃላይ በቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አባላት እና ምዕመናን በመሆኑ የደበሩን አስተዳዳሪ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀውልናል፡፡

 

 

 

 

Read 7950 times Last modified on Saturday, 02 July 2011 13:28