Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:56

የ”ትዋይላይት” የመጨረሻው ፊልም፣ ቀዳሚዎቹን አስከነዳ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የቫንፓየር አፈታሪክን ከዘመናችን ጋር ያስተሳሰረ፣ የፍቅርና የጀብድ ታሪክ ላይ የሚያተኩረው “ትዋይላይት”፣ በፊልም ተሰርቶ የቀረበው ከአራት አመት በፊት ነው - በመላው አለምም 390 ሚ. ዶላር ገቢ አስገኝቷል። በየአመቱ በፊልም ለእይታ የበቁት የታሪኩ ቀጣይ ክፍሎችም፤ ይበልጥ ተወዳጅነታቸው ጨመረ እንጂ አልቀነሰም። ዘንድሮም የታሪኩ አምስተኛና የመጨረሻ ክፍል ባለፈው ሳምንት አርብ በተለያዩ አገራት ሲኒማ ቤቶችን አጥለቅልቋል። በመክፈቻው እለት ገብተው ለማየት የጓጉ በርካታ ፊልም አፍቃሪዎች ሌሊቱን ወረፋ ሲጠብቁ አድረዋል።

The Twilight Saga: Breaking Dawn Part 2 እንደተጠበቀው በተለይ የብዙ ሴቶችን ትኩረት የሳበ ሲሆን፤ ከመክፈቻው እለት ከአርብ እስከ እሁድ በመላው አለም 431 ሚ. ዶላር ገቢ በማስገኘት የቀዳሚዎቹን አራት ፊልሞች ሪከርድ ሰብሯል።አራቱ ፊልሞች 2.5 ቢሊዮን ዶላር ማስገኘታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ እስከ 750 ሚ. ዶላር የሚደርስ ገቢ ይኖረዋል ተብሎ የሚገመተው የዘንድሮው ፊልም ሲጨመርበት፤ የፊልሞቹ ጠቅላላ ገቢ ከሶስት ቢሊዮን በላይ ይሆናል ተብሏል። በተያያዘ ዜና፤ ከፍተኛ ተወዳጅነት ባገኙ ፊልሞች አማካኝነት የፊልም አምራቾች ከአምናው የተሻለ ገቢ ማግኘታቸው ተዘግቧል። ሰሞነኞቹ “ስካይፎል” እና “ትዋይላይት”ን ጨምሮ የአመቱ ስኬታማ ፊልም “ዘ አቨንጀርስ”፤ እንዲሁም “ዳርክ ናይት ራይዝስ” የተሰኘው የባትማን ፊልም፤ “ዘ ሃንገር ጌምስ” እና “ዘ አሜዚንግ ስፓይደርማን” በተሰኙ ፊልሞች ገበያውን አሟሙቀውታል። ደርዘን የሚሆኑ ዋና ዋና የአሜሪካ ፊልም አምራች ኩባንያዎች፤ በአሜሪካ ውስጥ ከአምናው በግማሽ ቢሊዮን የሚበልጥ የ9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኙ ፊልሞችን አቅርበዋል።

Read 4839 times