Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:18

“የሚያቃጥል ፍቅር” ከ40 ዓመት በኋላ እንደገና ታተመ

Written by 
Rate this item
(9 votes)

“አፄ ቴዎድሮስ አጫጭር ታሪኮች” እየተነበበ ነው
የዛሬ 40 ዓመት ሲታተም ከፍተኛ “የሚያቃጥል ፍቅር” ልብወለድ መጽሐፍ እንደገና ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ “እግረ ፀሐይ ከዶክተርነት ወደ ሴተኛ አዳሪነት ለምን ተዛወረች” የሚል ጥያቄ በማንሳት የሚተርከው መፅሐፍ እድሜአቸው ከ18 አመት በታች ላሉ ሕፃናትና ነፍሰ ጡሮች ማንበብ የተከለከለ ሲሆን፣ 212 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በ35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በኃይለስላሴ ደስታ በ1960ዎቹ መጀመርያ የተፃፈው መፅሐፍ የቅጂ መብትን አስመልክቶ ደራሲው ባሰፈሩት ማስታወሻ “ይህ መፅሐፍ ከታተመ ከስድስት ወር በኋላ ማንኛውም ሰው ሳይቀንስ አሳትሞ ቢጠቀም እኔም ሆንኩ ወራሾቼ አንከራከርም” ብለዋል፡፡

በፎቶግራፎቹ የተደገፈው የአሁኑ መፅሐፍ በድጋሚ የታተመው በነጭ ሳር ማተሚያ ቤት ነው፡፡በሌላም በኩል “አፄ ቴዎድሮስ የሺህ አመቱ ጀግና አጫጭር ታሪኮች” ከሳምንት በፊት ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ 152 ገፆች ያሉትን የታሪክ መፅሐፍ ያዘጋጀው ማርቆስ የሻነው ሲሆን መፅሐፉ 35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

 

Read 6298 times