Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 12:19

“ፊኒክሷ ሞታ ትነሳለች” ውይይት ይካሄድበታል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

በወይዘሮ የውብማር አስፋው የተፃፈውና በሴቶች የትጥቅ ትግል ሚና ላይ የሚያተኩረው “ፊኒክሷ ሞታ ትነሳለች” መፅሐፍ በሚዩዚክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ የመፃሕፍት ንባብና የውይይት ክበብ ለውይይት ይቀርባል ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በአምስት ኪሎው ብሔራዊ ቤተመዘክር የሚካሄደውን የሦስት ሠዓት ውይይት የሚመሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ምሁር ዶር ዳኛቸው አሰፋ ናቸው፡፡

ወ/ሮ የውብማር ከታቃዋሚ ፓርቲዎች አመራር አባላት አንዱ የሆኑትና የቀድሞው የሕወሓት ታጋይ አቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ናቸው፡፡

========================================

ሀ-ግዕዝ” ፊልም ሰኞ ይመረቃል

በሀሁ ፊልም ፕሮዳክሽን ተሰርቶ በሪች ፊልም ፕሮዳክሽን የሚቀርበው “ሀ-ግዕዝ” የ92 ደቂቃ ፊልም የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በዚህ በማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ በሚያጠነጥን ፊልም ላይ ገነት ንጋቱ፣ ፍቃዱ ከበደ ማሞ፣ ሔለን በድሉ፣ ተረፈ ለማ፣ መኮንን ላእከ፣ ባህሬን ከድር፣ ያሬድ ዘኪሮስ፣ በሱፍቃድ ታዬ፣ ራሄል ዳሩንዳ ዘላለም ካሳዬ፣ አበበ ባልቻና ሌሎችም ይተውናሉ፡፡ ፊልሙን ለመስራት ሰባት ወራት የፈጀ ሲሆን ነገ ከ8 እስከ 12 ሰዓት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እንደሚታይና ሰኖ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2976 times