ዝግጅቱ ነገ በተመሳሳይ ስፍራ “Beneath Her Window” የተሰኘ የስሎቬንያ ፊልም፣ ሰኞ የፖርቱጋል ፊልም በጎተ፣ ማክሰኞ የቼክ ፊልም በአሊያንስ፣ ረቡዕ የቤልጂየም ፊልም በጎተ፣ ሐሙስ የስፔን ፊልም በአሊያንስ፣ ረቡዕ የቤልጂየም ፊልም በጎተ፣ ሐሙስ የስፔን ፊልም በአሊያንስ፣ አርብ የቡልጋሪያ ፊልም በጣሊያን የባህል ተቋም እና ቅዳሜ የጀርመን ፊልም በጎተ ያሳያል፡፡ ፌስቲቫሉ የሚዘጋው የነገ ሳምንት እሁድ “The Deep Blue Sea” በተሰኘ የእንግሊዝ ፊልም በጣሊያን የባህል ተቋም ነው፡፡
=====================================
“ስኬታማ የጥናት ዘዴዎች” ለንባብ በቃ
በፈተና ዝግጅት፣ በአጠናን እና ተመሳሳይ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው “ስኬታማ የጥናት ዘዴዎች” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በብሩክ ሙሉነህ የተዘጋጀው መጽሐፍ ማጣቀሻዎቹን ሙሉ ለሙሉ በድረገፅ መረጃዎች ላይ መስርቷል፡፡ 108 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በበረከት ማተሚያ የታተመ ሲሆን ዋጋው 30.50 ብር ነው፡፡ በተያያዘም