Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 12:14

“ባክስትሪት ቦይስ” በአዲስ አልበም ይመለሳሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ባክስትሪት ቦይስ ከሰባት ዓመታት መራራቅ በኋላ በድጋሚ የሙዚቃ ቡድናቸውን በማቀናጀት መስራት ጀመሩ፡፡ ለ20 ዓመታት አብረው የሰሩት “ባክስትሪት ቦይስ” ሰባተኛ አልበማቸውን በመስራት ላይ ሲሆኑ በ2013 ለገበያ እንደሚበቃ አስታውቀዋል፡፡ በ1990ዎቹ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ እውቅና የነበራቸው “ዘ ባክስትሪት ቦይስ” ሰሞኑን “ክሪስማስ ታይም ኤጌን” የተባለ አዲስ ነጠላ ዜማቸውን ለቅቀዋል፡፡ የሙዚቃ ቡድን አባላቱ ለአዲሱ አልበም ስራ በለንደን በሚገኝ መኖርያቸው መሰባሰባቸውን የገለፀው “ዲጂታል ስፓይ” የሚሰሯቸው ሙዚቃዎች ልዩ የሙዚቃ ስልቶችን በማቀናበር እንደሚሆን እንደተናገሩ እና የራፕ እና የሮክ ስልት እንዳልሆኑ ማስታወቃቸውን አትቷል፡፡

አምስቱ የሙዚቃ ቡድን አባላት ኬቨን ሪቻርድሰን፣ ኤጄ ማክሊን፣ ሆዊ ዶሩው፡ ብራያን ሊትሬል እና ኒክ ካርተር ናቸው፡፡ በ2009 እ.ኤ.አ ላይ “ዚስ ኢዝ አስ” የተባለ አልበማቸውን ለመጨረሻ ጊዜ የሰሩት “ዘ ባክስትሪት ቦይስ” ከስድስት አልበሞቻቸው 130 ሚሊዮን ቅጂዎችን በመላው አለም በመሸጥ በሙዚቃ ታሪክ ከፍተኛውን ሽያጭ ያስመዘገቡ የወንድ ሙዚቀኞች ቡድን ሆነው ክብረወሰን ተመዝግቦላቸዋል፡፡

 

Read 3695 times Last modified on Saturday, 17 November 2012 12:16