Saturday, 17 November 2012 10:30

ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ዛሬ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ይሸለማሉ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(4 votes)

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) ፕሬዚዳንት ለክቡር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ የክብር ዶክትሬቱን የምንሰጣቸው ለአገሪቷ የአካባቢ ጥበቃ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው ያሉት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ምትኩ ቴሶ፤ ፕሬዚዳንት ግርማ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት የደን አዋጅ እንዲወጣ ያደረጉ ታላቅ ሰው ናቸው ብለዋል፡፡ አዋጁ ሲወጣ 30 በመቶ ያህል የነበረው የአገሪቷ የደን ሽፋን እየተመናመነ ሄዶ 2 እና 3 በመቶ ያህል ወርዶ እንደነበር የጠቀሱት ዶ/ር ምትኩ፤ ለኅብረተቡ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጥ ትምህርት አሁን እያንሰራራ ያለው የደን ሽፋን፣ ሕጉ ባይወጣ ኖሮ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ መገመት ይቻላል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ግርማ የአገሪቷ ርዕሰ-ብሔር ከመሆናቸው በፊት የ “ለም ኢትዮጵያ” ም/ፕሬዚዳንት ሆነው ድርጅቱን በማስተባበር በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ድንበር ግራና ቀኝ በተከሉት ደን ተማሪዎቻችንን በተግባር እያስተማርንበት ነው ያሉት ዶ/ር ምትኩ፣ የአገሪቷ እስትንፋስ ለሆነው የደን ሀብት ልማት ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የክብር ዶክትሬት ያሰጣቸዋል ብለዋል፡፡

 

Read 3619 times Last modified on Saturday, 17 November 2012 10:58