Saturday, 17 November 2012 10:27

የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎችን የዘረፉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(3 votes)

መብራት ሃይል 52 ሚ. ብር ከሰርኩ አለ
በምስራቅ ኢትዮጵያ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ አምስት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ማማዎች ወድቀው 16 ከተሞች ለአንድ ሳምንት በጨለማ ውስጥ የሰነበቱ ሲሆን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎቹን የዘረፉ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው ፖሊስ ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሽን ለ52 ሚሊዮን ብር ኪሣራ መዳረጉን አስታውቋል፡፡

የሃይል ማስተላለፊያ ብረቶችን፣ ትራንስፎርመሮችና መወጠሪያ ብረቶችን ቆራርጠው በመውሰድ ህብረተሰቡን ለጨለማ፣ መብራት ሃይልን ለኪሳራ ዳርገዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች፤ በወለጪንቲ፣ በአዳማና ወንጂ አካባቢ ብረታ ብረቶች ቆራርጠው ለማጓጓዝ በዝግጅት ላይ ሳሉ እንደተያዙ ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ችሎት፣ ክስ እየተሰማባቸው ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በአጠቃላይ የ52 ሚሊዮን ብር ኪሣራ እንዳደረሰበት ታውቋል፡፡

Read 3490 times