ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማጠናከር ከ147 የውጭ ባንኮች ጋር ግንኙነት መስርቶ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ሊቀመንበሩ፤ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ እውቅና ካላቸው ሰባት ባንኮች ጋር የሂሳብ ግንኙነት በመፍጠር በአራት የተለያዩ አገራት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ባንኩ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ ምቾት ያለው ፈጣን የኤቲ ኤም፣ የፖይንት ኤፍ ሴል፣ የሞባይል ባንኪንግና ኢ-ኮሜርስ የክፍያ አገልግሎቶች ለመስጠት መሠረት መጣሉን ጠቁመው፤ ከአዋሽና ከንብ ኢንተርናሽናል ባንኮች ጋር ያቋቋሙት ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽን የተባለው ኩባንያ በዚህ ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
በዓመት ውስጥ 15 ቅርንጫፎች በመክፈት የቅርንጫፎቹን ብዛት 63 ያደረሰ ሲሆን፣ የሰው ኃይሉም 1,975 መሆኑ ታውቋል፡፡