19ኛው የዓለምን ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኮንፍረንስ በ2013 ዓ.ም የምታዘጋጀው ደቡብ አፍሪካ እንደሆነች ታውቋል፡፡የ “ወርልድ ውሜን ትሬድ ፌር አፍሪካ” ዳይሬክተር ወይዘሮ መቅደስ መኩርያ በጋናው ኮንፍረንስ ላይ ልዩ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን “አንድ ቀን በአገሬ እንደምሸለም አልጠራጠርም” ብለዋል፡፡ በጋናው ኮንፍረንስ የኢትዮጵያ ልዑካን በድል መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው የገለፁት ዳይሬክተሯ፤ “ውሜን አት 50’s (Women at 50’s) የተሰኘው የሃምሳዎቹ ዕድሜ ሴቶች ክብር የሆነው ፕሮግራም በኮንፍረንሱ ላይ በኢትዮጵያ ስም በይፋ መመረቁ አንዱ ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል፡፡
በመጪው መጋቢት ወር ላይ የመጀመሪያው “ውሜን አት 50’s” መድረክ በኢትዮጵያ እንደሚዘጋጅ የተናገሩት ወይዘሮ መቅደስ፤ አሸናፊው አገር ሁለተኛውን “ውሜን አት 50’s” ያዘጋጃል፤ ከዚያም በየዓመቱ ፕሮግራሙ በዓለም ይዞራል ብለዋል፡፡